◈ ━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━ ◈ ¤ የቀበሮ ፀሎት ¤ (ታገል ሰይፉ) ------ እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡ * አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡ * አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ * ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡ ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ * አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡ * ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡ * አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡ *** የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡ Only 🇯 🇴 🇮 🇳 ባለቅኔው https://t.me/ytebeb https://t.me/ytebebዐ https://t.me/ytebeb #ለመቀላቀል ይጫኑ #ለተጨማሪም_አስተያየቶ_እና_ልምዶን_ለማካፈል @Yehudaw ☜ 21 viewsyhuda መኖራችን ያለመኖራች ፍልስፍና ነው ሂዎት ፍልስፍና ናት ተጠቀምባት!!!, 08:55