Get Mystery Box with random crypto!

ስህተት ለትምህርት ነዉ ስንት ጊዜ ይቅር ትላለህ?፤ም | ይሁዳ የጥበብ ልጅ ፩

ስህተት ለትምህርት ነዉ



ስንት ጊዜ ይቅር ትላለህ?፤ምን ያህል ጊዜ ትታገሳለህ?፤ ድል ላንተ አሸናፊነት ባንተ ላይ መች ይዉላል?፤ስንት ጊዜ ሮጠህ ስንት ሜዳልያ ታጠልቃለህ?፤ምን ያህል ቡጢ ሰንዘረህ ተጋጣሚህን በዝረራ ትጥላለህ?
አንድን ዉድድር እኩል ጀምረን አንተ በአሸናፊነት ስምህ ከፍ ስላለ እኔ ደካማ ነኝ ወይ? ያንተን የስኬት በር ከእኔ የትግል መስኮት ጋር እያወዳደርክ ትንሽ አታድርገኝ እንጂ!

እልፍ ጊዜ ብሳሳት ሺህ ጊዜ ብወድቅ የዉድቀቴ ተግሳፅ በእኔ ጫንቃ እንጂ ባንተ ላይ አይወድቅምና በስህተቴ አትገረም!!

በእኔ የህይወት መርህ በአኗኗሬ ፍልስፍና ብመዝንህ እመነኝ ትወድቃለህ! ባንተ የህይወት ፈጣን ጉዞ ላይ የተሳፈረ ህልሜን በስህተት አትመልከትብኝ! በስህተቴ ለምደነግጥና አብዝቼ ለምፀፀት እኔ ስህተቴ ለትምህርት ነዉና!

Only ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌🇯 🇴 🇮 🇳

ባለቅኔው

https://t.me/ytebeb
https://t.me/ytebeb
https://t.me/ytebeb

#ለመቀላቀል ይጫኑ

#ለተጨማሪም_አስተያየቶ_እና_ልምዶን_ለማካፈል @Yehudaw ☜