Get Mystery Box with random crypto!

አንድ መጠጥ ቤት አንድ ፀይም ወጣት ቁጭ ብሎ እየጠጣ ይዝናናል ።ከዳንሱ መድረክ ላይ የአፍሪካዊ ጥ | #ቁርጥራጭ ሀሳቦች በየቲ

አንድ መጠጥ ቤት አንድ ፀይም ወጣት ቁጭ ብሎ እየጠጣ ይዝናናል ።ከዳንሱ መድረክ ላይ የአፍሪካዊ ጥቁር ገፅታ ያላቸው ጥንዶች ይደንሳሉ ድንገት አንድ ነጭ መጣና እንስቷን ከአጋሯ በሀይል አላቆ መደነስ ይጀምራል ። የተቀማው ወጣት ቃል ሳይተነፍስ ወደ ወንበሩ ይመለሳል ጠይሙ ወጣት ግን ወደ መደነሻው ተንደርድሮ ነጩን በቦክስ ያጓነዋል ይሄን ነጩ ያወጣው ቃል አንዲት ነበር " ኢትዮጵያዊ ነህ?" (በውቀቱ ስዮም ፕሮፌሰርን መስፍን የህይወት ታሪክ ሲቀነጭብ ከሰማሁት ።)

ኢትዮጵያዊነት አልበገር ባይነት ለነጭ አለማጓብደድ እንደሆነ ለአለም ያሳዩን ከኛ አልፎ ጥቁር ህዝቦችን ሁላ የሚኮራ ታላቅ ተጋድሎ ያደረጉ ጀግኖች አባቶቻችን ያቆዩልን የነፃነት ችቦ ስሙ "ዓድዋ " ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን ፣ክብር ህይወታቸውን ሰጥተው ላስከበሩን አባቶች ፣ክብር ለመሪው አፄ ሚኒልክ ፣ክብር ከስንቅ እስከ ወኔ ያስታጥቁ ለነበሩ እናቶች --- ሞታችሁ ኩራት ሆኖናልና ስንዘክራችሁ እንኖራለን!!!!!



#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_126
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia