Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉን ጠርጣሪ የስብዕና ህመም (Paranoid Personality Disorder) =========== | #ቁርጥራጭ ሀሳቦች በየቲ

ሁሉን ጠርጣሪ የስብዕና ህመም
(Paranoid Personality Disorder)
==========================
የፓራኖይድ ስብዕና ህመም ( ሁሉን ሰው የመጠራጠርና ያለማመን) የስብዕና ህመም በስብዕና ህመሞች ስር ከመጀመርያው ምድብ የሚመደብ ሲሆን ታማሚዎቹ ላይ በዋነኝነትም የሚታየው ሰዎች እንደሚበዘብዙአቸው እንደሚጎዷቸውና እንደሚያተልሏቸው የሚያስቡና በዚህም ምክንያት ማንንም ሰው ያለማመንና መጠራጠር ነው።

ምን አይነት ምልክት ያሳያሉ?
==================
-እነዚህ ሰዎች ሌሎችን ሲጠራጠሩና ታማኝ እንዳልሆኑ ሲናገሩ ጥቂት ወይም ምንም ማስረጃ አይኖራቸውም።
-ብዙ ጊዜም የሚሰማቸው ጥልቅ የሆነና ሊቃና በማይችል ሁናቴ በሌሎች ሰዎች እንደተጎዱ የሚያስቡ ሲሆን ለዚህም ምንም ዓይነት ማስረጃ አይኖራቸውም።
ከዚህ በተጨማሪ የሚከተሉት ምልክቶች ይኖሯቸዋል
-በጓደኞቻቸው/ባልደረባዎቻቸው ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ጥርጣሬ
-ሌሎች ሰዎች ዕምነት ሲያሳዩአቸው የሚደነቁ ቢሆንም ሊያምኗቸው አይችሉም
-የሆነ ችግር ውስጥ ሲገቡ በጓደኞቻቸው/በባልደረቦቻቸው
በደረሰባቸው ጉዳት/መተው እንደሆነ ያስባሉ
-ሰውን ከቀረቡ የቀረቧቸው ሰዎች የነሱን መረጃ በመውሰድ /በመጠቀም ይጎዱናል ከሚል መነሾ መቅረብ አይፈልጉም
-ስለራሳቸው ጥያቄ ከሰዎች ቢነሳላቸው "ይሄ የማንም ጉዳይ" አይደለም ከሚል እሳቤ ምንም አይነት መረጃ አያወጡም
-እነዚህ ሰዎች ቂመኞች ሲሆኑ የሰደባቸውን: የጎዳቸውንና የናቃቸው የመሰላቸውን ሰው ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አይሆኑም
-የትዳር አጋራቸውን/የፍቅር ጓደኛቸውን ያለምንም ማስረጃ ይጠራጠራሉ
-አንዳንድ ጊዜ ግትርነት ከሌሎች ጋር ያለመተባበርና ነቀፌታን ያለመቀበል ይታይባቸዋል
-እራሳቸው በፈጠሩት ክፍተት ሌሎቹን ሲወነጅሉ ይታያሉ
አጋላጭ ሁኔታዎች
============
በቤተሰብ የስኪዞፍሬኒያ ህመም/Schizophrenia/
Delusional disorder/persecutory type ያለበት ቤተሰብ ያላቸው ልጆችበተለዬ ሁኔታ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ

ህክምና ይኖረዋል?
============
ይሄ ህመም ያላቸው ሰዎች ባብዛኛው የህክምና እርዳታ ሲፈልጉ አይታይም። ነገር ግን የትዳር አጋሮቻቸውና ቀጣሪዎቻቸው ወደ ህክምና ሲያመጧቸው ይስተዋላል።
1. ሳይኮቴራፒ (psychotherapy)
ለዚህ ህመም በግለሰብ ደረጃ የሚሰጥ (ታካሚውና የስነ-ልቦና/ስነ-ዓዕምሮ ባለሙያው) የሚሰጥ የንግግር ህክምና
Individual psychotherapy
2. የስብዕና ህመምን በመድሃኒት ለማከም አዳጋች በመሆኑና ለስብዕና ህመም የመድሃኒት ህክምናው በዋነኝነት ያተኮረ ባይሆንም ተጓዳኝ ለሆኑ የህመም ምልክቶች ለምሳሌ ለጭንቀት ብስጭትና ተያያዥ ምልክቶች(Delusional thinking) የሚከተሉትን መድሃኒቶች ለአጭር ጊዜ ይታዘዛል።
1. Diazepam(Valium)
2. Haloperidol (Haldol)

#የዚህ ህመም ተጠቂዎች በራሳቸው ጊዜ የህክምና ዕርዳታ ሲፈልጉ ስለማይስተዋል የምታውቁት ጓደኛ/የስራ ባልደረባ ካላቸው
የስነልቦና ባለሙያዎች (Clinical psychologist) ወይም የስነ-ዓዕምሮ ባለሙያ እንዲያገኙ እንርዳቸው::
አድራሻዎች
=======
-አማኑኤል የአዕምሮ ልዩ ሆስፒታል***
-ጥቁር አንበሳ የስነ-ዓዕምሮ ህክምና ክፍል
-ቅዱስ ጳውሎስ ስነ-ዓዕምሮ ህክምና ክፍል
-ኤካ ኮተቤ ፣ሚኒሊክ፣ ዲላ፣ባህርዳር፣ጎንደር፣ ሀዋሳና ሌሎችም
የስነልቦናና የስነ-ዓዕምሮ ባለሙያዎች ታገኛላችሁ!

በክፍለሀገር ከዚህ ቀደም የተጠቀሱ የስነ-ዓዕምሮ ህክምና ሆስፒታሎችን ተጠቀሙ።

ብሩህ ጊዜ
ቃልኪዳን