Get Mystery Box with random crypto!

ለምትቃወሙን እና ለምታሳድዱን #ልዑል_እግዚአብሔር_በዮሐንስ_ወንጌል_ምንድነው_ያለው:- '' እ | የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch

ለምትቃወሙን እና ለምታሳድዱን
#ልዑል_እግዚአብሔር_በዮሐንስ_ወንጌል_ምንድነው_ያለው:-
'' እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ በአባታችሁ ዘንድ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።''
የዮሐንስ ወንጌል 8 : 38

ስለዚህ በዚህ ዘመንን በሚመዝን ሕያው ቃል መሠረት እኛ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ከአምላካችን ከአባታችን እግዚአብሔር ያየነውን እና የሰማነውን፣ ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ጻድቃን አባቶቻቸን ያስጨበጡንን እውነት እንመሰክራለን ፤ እናንተ(አሳዳጆቻችን) ደግሞ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ያያችሁትን ታደርጋላችሁ።

''እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።'' የዮሐንስ ወንጌል 8 : 44

'' እኔ ግን እውነትን የምናገር ስለ ሆንሁ አታምኑኝም።''
የዮሐንስ ወንጌል 8 : 45

''ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ እናንተ ከእግዚአብሔር አይደላችሁምና ስለዚህ አትሰሙም።''
የዮሐንስ ወንጌል 8 : 47

እግዚአብሔር ይመስገን! እመብርሃን ትክበር ትመስገን!!!