Get Mystery Box with random crypto!

ወርኅ ነሐሴ ፳፬ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አራት ጌ | የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch

ወርኅ ነሐሴ ፳፬

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አራት ጌታችን በቅዱስ አምላካዊ ቃሉ ‹‹ሐዲስ ሐዋርያ›› ብሎ የሰየማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዕረፍታቸው ነው፡፡ ምግባር ሃይማኖት፣ ገድል ትሩፋታቸው ከማር የጣፈጠ ሰማዕቱ አቡነ ቶማስ ዘመርዓስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ለ12 ዓመታት በጉድጓድ ውስጥ በተጋድሎ የኖረች እንዲሁም በጣና ባሕር ውስጥ ገብታ ሰውነቷ ተበሳስቶ የባሕር ዓሣ መመላለሻ እስከሚሆን ድረስ እንደ ተተከለ ዓምድ ሆና ከባሕሩ ሳትወጣ 12 ዓመት ቆማ ስትጸልይ የኖረችው እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዕረፍቷ ነው፡፡

❖ የቅዱስ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት አብይት በዓላት እነዚህ ናቸው፦
መጋቢት 24 ቀን 1196 ዓ.ም ፅንሰታቸው
ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ልደታቸው
ኅዳር 24 ቀን ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ሲሆን
ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም ደግሞ በጸሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት ነው (ነገር ግን የዕረፍታቸውን ቀን ይዞ በዚሁ በጥር ወር በ24 ይከበራል)
ነሐሴ 24 ቀን 1296 ዓ.ም ዕረፍታቸው
በግንቦት 12 ቀን 1353 ዓ.ም ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው፡፡

«ስማቸውን ከሚጠሩት ነፍሳት ሁሉ ጻድቅም ቢሆን ኃጥእም ቢሆን ወደ ክቡር አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሳያደርሱት ወደ ዘላለም ርስቱ ወይም ወደ ሲኦል አያገቡትም»

[አርኬ]
ሰላም ዕብል እንበለ አርምሞ በጽዋዔ፡፡ ኪያከ አበ ወኪያከ ረዳዔ፡፡ ተክለ ሃይማኖት መዋዒ እንዘ ትጸንሕ ተስፋ ትንሣኤ፡፡ አጽናዕከ ለቀዊም አእጋረ ክልኤ፡፡ ወእምስቴ ማይ አህረምከ ጕርዔ፡፡

የከበረች ቃልኪዳናቸው ኹላችንንም ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን! አሜን!
t.me/AlphaOmega930