Get Mystery Box with random crypto!

የተሰባበሩ ፊደላት

የቴሌግራም ቻናል አርማ yetesebere — የተሰባበሩ ፊደላት
የቴሌግራም ቻናል አርማ yetesebere — የተሰባበሩ ፊደላት
የሰርጥ አድራሻ: @yetesebere
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 930
የሰርጥ መግለጫ

👉ግጥም
👉ወግ
👉የተሰበረ የልብ ቃላት
👉ጠቃሚ ፅሁፎች
አናግሩኝ 👉 @Tiya67
Join አድርጉን...
ሰላማችን ይብዛ ...
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይባርካት።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-06 20:04:14 Channel photo updated
17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 18:10:00



አንዲት ደሃ ነፍሴን... ካንቺ ጋር ባ'ጣብቅ
ስጋቱ ገደለኝ ... መስሎኝ የምነጠቅ።

ከኮበለለ ዕዳ ... ትርፉ ትዝብት ብቻ፣
ወድጄሽ ወድጄሽ ... ተረፍኩኝ ለዛቻ ፣
ድሮም ፉከራ ነው
ብቸኛ ቅርስ ሃብቱ
የአፍቃሪ መባቻ።


በንጉሡ ተሰማ(ጢያ)


t.me/yetesebere
356 views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 18:27:47 ባዶ ቦታ

የሚታይ ነገር አለ...? የሚዳሰስስ...? እንቅ አድርጎ ይዞ አንገቱን ጨምድዶ ወይንም ደግሞ... እንዳይጋረፍ ፣ እንዳይጎዳን ፣ እንዳያስጨንቀን ፣....ጠቅልለን የሆነበት እንድናስቀምጠው ... ይታዘዘናል...?

ዝናብ ሲመጣ ሰው ሲሯሯጥ... ፀሀይ ስትበረታ ጥላ ጥላ ሲሸሸጉ... ጨለማ ሲመጣ ብርሃን ሲፈልጉ ... ቀልድ ይሁን ሙሾ ሳያውቁት ወይንም ሳላውቀው ሲያላዝኑ.......... ለእኔ ምኑም አይገባኝም። የማስበው.... ትናንት የነበርኩበት ቦታ ዛሬም እንዳለሁበት ይሰማኛል። ነገሮች ሁሉ ሲለዋወጡ... ለእኔ እንደነበሩ ናቸው።
አይቀዘቅዙ ፣ አያቃጥሉ ፣ አይጨልሙ ፣ አይገርሙ...አይደንቁ። ብቻ ...አላውቅም። በነጠብጣብ ባዶ ቦታ ለቅቄ ...ሰው የመሰለውን ይክተት(...........)

የድሮ አስተሳሰብ ናፍቋችሁ አያውቅም...? እንደውም ላስታውሳችሁ... የሰማይ መጨረሻ ከፊት ለፊትታችን ያለው ተራራ እንደሆነ (የዓለም ጠበብት መጡና 'ሰፊ ናችሁ' ብለው ሳይበታትኑን በፊት) የምናውቅ ፣ ሽንት ስንሸና... በክንዳችን ልክ ለክተን የምንቀመጠው ነገር (የእናታችን ጡት...) ... በእንደዚህ አይነት ስሜት ያለሁ ይመስለኛል።

ስታኮርፊ ኩርፊያሽ ... ዓለምን ያናውጠዋል(የእኔን) ። ስትቆጪ...ህይወት ከንቱ ትሆናለች(የእኔ)። ልትለዪኝ ስታስቢ... ምድርና ሰማይ ሲጋጩ... እኔ ተመልካች ሆኜ... እያንዳንዱን የሰውነቴ ክፍል ሲጨፈላለቅ ይታየኛል።
በመጨፈላለቅም ውስጥ ሆኜ ... በማይታዩ ...በማይዳሰሱ ...ይህ በማይባሉ ጥቃቅን ትዝታዎች ታጅቤ ወደቀድሞው ፍቅራችን እመለሳለሁ። ያው የድሃ ሃብቱ እንቅልፉም አይደል... ፍቅሩን ያጣ ሰው ታድያ ድሃ አይደል... ታድያ እንቅልፍ ከትዝታ በምን ይለያሉ...? አይዳሰሱ ፣ አይጨበጡ...እንደውም አገልግሉታቸውም ይመሳሰላል። ድሃ በእንቅልፉም አይደል ቅቤ የሚጠጣው..? አፍቃሪስ( ያጣ አፍቃሪ) ፍቅሩን የሚያገኘው ከትዝታው አይደል..?

ተውኝ..............መሮኛል(ባዶ ቦታውን ሙሉት!)



በንጉሡ ተሰማ(ጢያ)

@Tiya7t




t.me/yetesebere
314 views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:38:22 አፌ
ድሮ አልቃሽ ነበር... ዘንድሮ ለፍላፊ፣
ወጪና ወራጁን ... በምላስ ጠላፊ።


አይኔ
ድሮ አላሚ(ኢላማ) ነበር.... አሁን ግን ፈዛዛ፣
ማየቱ ተስኖት... ባ'ጭሩ ጠነዛ።


ጉልበቴ
መዋያው ከዱሩ... ከጫካ እንዳልነበር፣
ከወንዳ ወንዶቹ... ጎራ ስፎካከር፣
ኖርኩኝ ኖርኩኝና ... ከዘንድሮ ስደርስ፣
ያለማንገራገር
ያለመጠራጠር
አየሁ ጉልበት ሲፈስ።

ያልተረዱት ህመም... ቢታወቅም ምንጩ፣
ሊታገሉት ፈርተው... ዳር ዳር ቢያሞልጩ፣
መች ሊኖሩ ደፍረው... ዘውትር እየሸሹ
ወይ ውጣ ወይ ውረድ... እያቅለሸለሹ።

በ ንጉሡ ተሰማ(ጢያ)


t.me/yetesebere
1.4K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 18:59:19


እኔ እስቃለሁ
...አንቺ ግን አልቅሺ፣
ነገ ነው ተራዬ
...ይሄንን አትርሺ።
ሁሉም ካለቀሰ... ሳቅ አይታወቅም፣
ሁሉም ደግሞ ሲስቅ... ጤነኛ አይባልም።
_ __
_____

ጊዜ ጊዜን ወልዶ.... እስኪሰጠን ጊዜ፣
አንቺ ሙሽራዋ .....እኔ ደግሞ ሚዜ።

በንጉሡ ተሰማ(ጢያ
)


@Tiya67 ወይንም @Tiya7t አስታየት




t.me/yetesebere
1.8K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 17:23:00 ናዕት
ቴዲ አፍሮ

ግርም ያለ ጊዜ ሆነ ሰዓቱ
በዳንኪራው ደምቆ በምቱ
ለደቂቃም አይቆይ በስልቱ
ቦግ እልም እያለ መብራቱ

ቢጋርድ ሀሳብ አርጎ ሜዳን ገደል
እም አእላፍ ስቃይ ጭንቀት ቢደረደር
የነፍስ ሕላዊ መሻት ዋዌው ሳይገባቸው
ስንቶች በዘር ተዘፍቀው ታዘብናቸው

ዘውግ ያወረው ድንበር ማላውን የረሳ
ሳር ያለመልማል ዛሬም በእልፍ አእላፍ ሬሳ
እያረረ ሆዴ ብስቅ በማሽላ ዘዴ
ና ታደም ይለኛል ደግሞ በነ ኡኡ ሬጌ

ተላላ ዝንጉ ሰብ የሙታን ሸማ ደዋሪ
ምን አለ አይል ከፊት ሆኖ ቅርብ አዳሪ
ተናገር አፌ ደፍረህ ሳትናወጥ ከቶ
ዝም አይሆንም ሜዳ ተራራ ሞት መጥቶ

ከበሮ ግም ሲል በእምቢ ነጎድጓድ ምቱ
ይናዳል የዘር ድንዛዜ ያ ድውይ ቤቱ
ገለል በል ኤሳው ነፍሴን አንቀህ አታሳሳት
ብታገስ ባሰ ባንተ የልቤ እሳት

እያመመው መጣ

ያዳፈነው እሳት ከሆዱ ሳይወጣ
ልቤ እንደካቻምናው እያመመው መጣ
የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ….እያለ ማሲንቆ
ኡ….ኡ…..

እያመመው መጣ

የተረገጠ እውነት በጊዜ ውስጥ እግር
ታፍኖ የቆየ በሆታ ግርግር
ትንሽ ጋብ እንዳለ የጭብጨባው ጩኸት
እረጭ ሲል ውሸት ይናገራል እውነት

እያመመው መጣ

ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሐገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም

ዶፍ ዶፍ ቢዘንብ እሳት
ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት

ዳር አለው እንዴ ድንበር
ዳር አለው እንዴ
ዳር አለው እንዴ ፍቅር
የዘር ሐይማኖት ድንበር
ዳር አለው እንዴ ፍቅር
በዚህ ለፀና እውነት
የፍቅር ሐገር ከጥንት
ዘብ ያድራል ሁሉም እስከሞት
ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት
ዶፍ ዶፍ ብዘንብ እሳት
አገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት

ናዕት
316 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 11:28:09 በማያውቀው ጉዳይ... ሰው እየታረደ፣
ተሰደብኩኝ ይላል : ነፍስ እየ... ነገደ።

#በቃን
#ቀይ_አሻራ
#የዜግነት_ክብር

አይበቃም...???
የ''ሀገራችን ምድር... መላወሷ በደም
እስከመቼ ይሆን
አረንጓዴ አሻራ ... የሚፀድቀው በደም??
አይበቃም...?
በቃን...!!!
ይብቃን...!!!
አቁም.....!!!!!!



t.me/yetesebere
265 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 23:22:14 https://t.me/simeten
272 views20:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 21:25:22
አወይ ደስታ ማጣት... አዬ ጉልበት ማድከም
ስቀን ሳናባራ... ይዘፍቀናል ህመም

የቱ ነው ልኬቱ ... የሃዘኑ መጠን
መጠኑን ንገሩን... ስቀን ከምናዝን
አልቅሰን...ይውጣልን

በየጊዜው ለሚሰው ወገኖቻችን RIP
1.2K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ