Get Mystery Box with random crypto!

ሀገር ስጪኝ... (በላይ በቀለ ወያ) . . ለጠየቅሽኝ እንቆቅልሽ ፣ ሲጠፋብኝ እኔ መልሱ 'ሀገር | የተሰባበሩ ፊደላት

ሀገር ስጪኝ...
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ለጠየቅሽኝ እንቆቅልሽ ፣ ሲጠፋብኝ እኔ መልሱ
"ሀገር ስጠኝ" የምትዪኝ ፣ መልስ አታውቂም አንቺ ራሱ!
።።
ሁሉ ሀገሩን ተከፋፍሎ፣ ክልልሎችን እያጠረ
ኬ'ት አምጥቼ ሀገር ልስጥሽ ?፣ ሀገር ማለት "ሰው" ነበረ።
ሰውም በዘር ተከፋፍሎ ፣ ሀገር መሆን አቅቶታል
ገድሎ ሚኖር ተበራክቶ ፣ ሞቶ ሚያኖር ካገር ጠፍቷል!
።።።
ይህን እውነት እያወቅሽው ...
"ሀገር ስጠኝ" አትበዪኝ ፣ በእንቆቅልሽ ልትለውጭኝ
ክልልና ዘር ነው ያለኝ ፣ እሱን ወስደሽ ሀገር ስጭኝ!




t.me/yetesebere