Get Mystery Box with random crypto!

'ሞቼ እንኳን ላልረሳሽ ቃሌ ለሰማይ ነው!' ያልከኝን ሰምቼ በሞትክበት ቅፅበት ተከትዬህ መጣሁ፣ | የጥበብ ቤት

"ሞቼ እንኳን ላልረሳሽ ቃሌ ለሰማይ ነው!"
ያልከኝን ሰምቼ
በሞትክበት ቅፅበት
ተከትዬህ መጣሁ፣
ለቃልህ እንደታመንክ ላምን 'ባይኔ አይቼ ፤
ግን ነፍስህ እኔን ዘንግታ
ተላምዳለች ፃድቃን
ተሳሳትኩኝ መሰል መለየት ተስኖኝ ነፍስን ከስጋ ጋር

እባክህ አምላኬ....!
ነፍሴን ስጋ አላብሰህ ሸኘኝ ወደ ምድር
አልረሳኝ እንደሆን አካሉን ጠይቄ እድሌን ልሞክር!

ፊያሜታ

@YETBEB_BET