Get Mystery Box with random crypto!

.ለደስታዬ ያለምኳት ፡ የኔዋ አንድ ቀን ፣ ልክ እንዳ'ንድ ቀኖች ቂያማ አጠብቅም የላትም ሌላ አቻ | የጥበብ ቤት

.ለደስታዬ ያለምኳት ፡ የኔዋ አንድ ቀን ፣
ልክ እንዳ'ንድ ቀኖች
ቂያማ አጠብቅም የላትም ሌላ አቻ
ፍካት የሚወ'ርሳት ባንተ መውጣት ብቻ።

አልሃምዱሊላህ ይቺ ቀን ብሩክ ናት!

በሀሴት ታውጄ መንፈሴ እንዲረካ
ማንም ምንም ለኔ
አንተን ማየት ብቻ ይሰጣል በረካ።
አጀብ የዚህችስ ቀን!

ድንገት በቀትሩ
አጮልቃ ካየች ከእግዜር ተደብቃ፣
'እኔስ መች ተዋብኩኝ!?' ትላለች ጨረቃ።
ብርሃንም ቢሆን
የቱን ታክል በርቶ ስሙ እንደተሰጠው
አንተን ባየ ቁጥር አምርሮ አምላኩን እንደጠየቀው ነው።
እኔማ ድኩም ነኝ
ምኔንም ከምንህ ጋር ውድድር ይቻለኝ!?
ብቻ ይህቺ ቀን ትመስገን!

ለባይተዋር ልቤ
ለነፍሴ ራህመት ያቀርብኩት ዱዓ፣
እነሆ አጃኢብ!
ውብ አድርጎ ፈጥሮህ ሰቶኛል ጁምዓ። #FIYAM @YETBEB_BET