Get Mystery Box with random crypto!

የኃይሌ ስራዎች/ሊቤርታስ/

የቴሌግራም ቻናል አርማ yet1232 — የኃይሌ ስራዎች/ሊቤርታስ/
የቴሌግራም ቻናል አርማ yet1232 — የኃይሌ ስራዎች/ሊቤርታስ/
የሰርጥ አድራሻ: @yet1232
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 438
የሰርጥ መግለጫ

እስከ ብዕራችን ህቅታ ከጥበብ ጋር እንፋለማለን፡፡


ለጥበብ እንጂ ለጭብጨባ ስለማንጽፍ ጭብጨባ ቢኖርም ባይኖርም ህያው ነን፡፡
.
.
.
ግጥም፣ ወግ፣ መነባንብ፣ ልቦለድ፣ ኢ-ልቦለድ፣ ቀስቶ፣ ቴአተር፣ የፊልም ድርሰት .....ወዘተረፈ በሰፊው ይቀርባል፡፡
.
.
.
ስራዎቻችሁን ለመላክ ከታች ያሉትን ሊንኮች ተጠቀሙ፡፡
@Haileged
@Biranabook

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-26 21:04:33 ሞኝ ነኝ አይደል?!

ከተቀደደው ማስታወሻ
ሶፊ

@bestletters
100 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 15:59:08 https://vm.tiktok.com/ZML7uxkFr/?k=1
159 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 19:33:06 የሶፊ ደብዳቤ

ቁጥር አይታወቅም


"ብዙ ውብ የመሰሉኝ ቃላት ሊገልፁሽ ስላልቻሉ ሰርዣቸዋለሁ..."


"እሳት ሲሆን ኑሮሽ ወርቅ የሆንሽው አንቺ
ነጥረሽ እየወጣሽ ደክሜ እንዳልቀር የምታበረቺ
ምሰሶ ሳትሆኚው ጎጆ መች ይቆማል
ሙሉነት ያላንቺ እንዴት ይታለማል"

እናቴ

#Worth to share

@bestletters
142 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 22:04:51 ከተቀደደው ማስታወሻ
ሶፊ

Post card story by sofi

(ከ112 ሰው 61 ሰው በድምፅ ብሏል...እነሆኝ በምርጫችሁ።)

@bestletters
192 views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 21:50:57 ልነግርሽ ነበረ

ከበላይ በቀለ ወያ

"ወንዶች እብድ ሴት ይመቻቸዋል ስለተባሉ ብቻ ያበዱ ብዙ ሴቶች አሉ።"

በሶፊ

@bestletters
210 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 07:48:26

210 views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 20:32:49 እ ጠ ብ ቅ ሻ ለ ሁ !

ኤልያስ ሽታኹን

በሶፊ

@bestletters
254 views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 07:57:53

255 views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 21:46:32 "ተከራያችን"

ክፍል ፰

ደራሲ፦ሶፊ


የተከራያችን ቤት በሰፊው ተከፍቷል ውስጡም ባዶ ነው።እንደ ጨው ሐውልት ደርቄ ለደቂቃዎች ቆየው። የሆነ ነገሬ ሲሰበር ተሰማኝ።ቅስሜ ይሆን? ሐሞቴ ፈሰሰ።ስለእርሷ ምንም ማወቅም መስማትም አስጠላኝ። ምንም እንዳልተፈጠረ እናቴን እቅፍ አድርጌ ሳምኳትና።ራት እየበላን ቡና ስንጠጣ..."መቼ ነው የሄደችው ?" አልኳት።
"አልነገረችህም እንዴ" አለች እናቴ በግርምት።
"አዎ እማ " አልኳት ከእንግዲህ የምዋሽበት ምንም ምክንያት የለም።
ሁኔታዬን ስታይ እናቴም ሐዘን ገባት "እናቴ ጋር ልመለስ ነው ብላ የደወልኩልህ ቀን ነው የሄደችው።ለእኔም የዛኑ እለት የሚጭንላትን መኪና እደጅ አስቁማ፤እቃ ልታወጣ ስትል ነው የነገረችኝ።ሶፎንያስ ይሄ ነበር የእኛ እና የእርሷ ቅርበት? እንደ ልጄ ነበር የማያት ከስራ ስትመጣ አብስሎ ለመብላት ይደክማታል፤ ይርባታል እያልኩ እንጀራ እየሰደድኩላት። ብቻ ሆድ ይፍጀው ባዳ ባዳ ነው።አለች እናቴ በምሬት።"
እኔ ቃል አልተነፈስኩም እናቴ ስለእርሷ ወሬ እንዳትቀጥል ቴሌቪዥኑን የምመለከት መሰልኩ።
"የሰው ልጅ ፈፅሞ ልታውቀው የማትችለው እንቆቅልሽ ነው።" የሚል አባባል ሰምቼ አውቃለሁ።የዚች ግን ይብሳል።የእርሷ ቅኔ ሰሙ እራሱ ወርቅ ነው! ትብታቧን ለመፍታት ጫፍ እንኳን አታሲዝም። ዝም ብለህ ስትጠይቅ ትኖራለህ።
፨፨፨፨የመጨረሻው መጨረሻ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሁሉም ያልፋል ይሉ አይደል ሰዎች እውነታቸውን ነው።ሁሉም አለፈ።ትዝታዋም አልቀረ ሁሉም ተረሳ።
አመት ከመንፈቅ ሆነ
...አንድ ቅዳሜ ላይ ግን እንዲህ ሆነ።ሳምንቱን በስራ ምክንያት ሳንገናኝ የሰነበትነውን ጓደኞቼኝ አገኘዋቸው።
አንድን መፅሐፍ አንስተን እየተጨዋወትን ሳለን...አንድ ስልክ ጥሪ ተደረገልኝ...ስልኩ አውጥቼ ስመለከተው የማላውቀው ቁጥር ነው።አነሳሁት "ሶፊ" አለች ከዛኛው ጫፍ የማውቀው ድምፅ ነው ማን እንደሆነች ግን ገና አለየዋትም።"ማን ልበል?" አልኳት።
ስሟን ነገረቺኝ...እሷው ናት!
"አል...ብዬ ከአፌ መለስኩት።(አምልጦኝ አልሞትሽም? ልላት ነበር።)
ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ...እንዴት ልትደውል እንደቻለች ጠየኳት እንዲሁ ሰላም ልልህ እናም ከቻልክ ላገኝህ ነው አለቺኝ።
እንደማልችል እና አሁንም ከጓደኞቼ ጋር መሆኔን ነግሪያት...ሳልሰናበታት ስልኩን ዘጋውት።አንዳንዴ "አይሆንም"ማለትን መልመድ አለብን።የሚሆነውንም የማይሆነውንም ይሆናል እያልን ነው የተቸገርነው።
ማታ ቤት በተለመደው መልኩ ከእናቴ ጋር ካሳለፍን በኋላ ከመኝታዬ በፊት ስልኬን እየጎረጎርኩ ከአመት ከመንፈቅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮፋይሏን ልመለከት...ብሎክ ሊስት ውስጥ ገባሁ...
ፕሮፋይሏ በመንፈሳዊ ምስሎች እና በአባባሎች ተሞልቷል...ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ።
ፕሮፋይላችን ግን እኛን ይገልፃል? በጣም የውሸት አለም ውስጥ ከመዘፈቃችን የተነሳ፤የራሳችን ምስል እንኳን እኛን መግለፅ ትቷል።
እያልኩ ከደረደረቻቸው 80 ፎቶዎች ውስጥ 27ተኛው ላይ ስደርስ ያዝ አድርጌው ቆየው።የወንድ ምስል ነበር። የእኔ አለም እወድሀለሁ የሚል ተፅፎበታል።ቅናት ቢጤ አንጨረጨረኝ።ቀጥሎ ያለውንም ከፈትኩት ራሱ ፎቶ በትልቁ ተስሎ ግርግዳ ላይ ከተሰቀለ ምስል ላይ የተነሳ መሆኑ ያስታውቃል።
29 አየሁት።ራሱ ልጅ ወደ ደረቱ አስጠግቶ አቅፏት የሚያሳይ ፎቶ ነው ከፊታቸው ኬክ እና ልዩ ልዩ ዲኮር ተቀምጧል።እንዲህ የሚል መግለጫ ፅሑፍ ተፅፎበታ "ሦስት አመት በፍቅር"
ማመን አልቻልኩም።
30ኛውን ምስል ከፈትኩት አባባል ነው "መታመን ለራስ ነው" ይላል።
"ቱ ቀጣፊ !" አልኩና ስልኩን አሽቀንጥሬ ወረወርኩት።
ፍቅረኛ እያለሽ ነበር እኔን ያ ሁሉ ነገር ውስጥ የከተትሽኝ? ከእሱም ጋር ከእኔም ጋር ነበርሽ? ፍቅረኛ እያለሽ ነው ከእኔ ጋር እንደዛ ስትሆኚ የነበረው? እሺ ከነገርሽኝ ውስጥ የቱ ነበር እውነት? ሰው እንዴት በእንባ እየታጠበ ውሸት ይናገራል?

እሞታለሁ ያልሽኝም ውሸት ነበር ?

አጠገቤ እንዳለች ሁሉ በንዴት ጦፌ ጥያቄዎችን አግተለተልኩ።መልስ የሚሰጥ የለም።
እንቆቅልሹን ግን ጊዜ ፈታው።እንደራሷ ግራ የገባው አደረገቺኝ ለሰው ያለኝ አመለካከት ተዛባ።


አሁን እኔ ሰው ባላምን ይፈረድብኛል ?











?

እዚህ ድረስ ስላነበብከው/ሽው ከልብ አመሰግናለሁ።

@bestletters
288 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 20:00:16 ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለአብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ።መልካም ጾም ይሆንላችሁ ዘንድ እየተመኘው ይሄን "ኤፍራጥስ ወንዝ" ከተሰኘ የዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ መፅሐፍ ላይ የተቀነጨበ "አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?" የሚል ፅሑፍ እጋብዛችኋለሁ።
የበረከት ጾም ይሁንልን።
"አብይ ጾምንስ እንዴት ትጾማለህ?"
ሶፊ

@bestletters
202 views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ