Get Mystery Box with random crypto!

ሚዕራጅ --- የንግስናው ጉዞ -- ክፍል አንድ ረጀብ 26 ቀን ላይ ሠይዲ( ሠ.ዐ.ወ) ብቻቸውን ወ | ሁስነል ኹሉቅ

ሚዕራጅ --- የንግስናው ጉዞ -- ክፍል አንድ
ረጀብ 26 ቀን ላይ ሠይዲ( ሠ.ዐ.ወ) ብቻቸውን ወደ ካዕባ አመሩ ። የተወሠነ ሠዐታት
ከጌታቸው ጋ ለማውራት አንድ ኩርባ ላይ ተቀመጡ። በተመስጦም ጌታቸውን የልባቸውን
መሻት እየነገሩት ሳለ አቡ ጃሃል ከብዙ ተከታዮቹ ጋ መጣና እንዲህ አላቸው " ሙሃመድ
ሆይ አንተ ነብይ ነህ እንዴ ? አዎ አሉት በልበ ሙሉነት ። እርሡም እና ብቻህን እዚህ ምን
ትሠራለህ ? የታሉ ተከታዮችህ ? የታሉ ረዳቶችህ ? እንዲህ በብቸኝነት ሚቆዝም ነብይ
አይተን አናውቅም ። እኔን አታየኝም እንዴ ስንት አጀባ ስንት ተከታይ ስንት ረዳት አስከትየ
እንደምጎዝ አንተ ነህ እኔ የተላቀና የተከበረ የምንመስለው .... እያለ የትዕቢት ቃላቶችን
አዘነበባቸው ...." አቡ ጃሃል ይህን ተናግሮ እንዳበቃ ሌላ የቁረይሽ ባለባት መጦ ተመሳሳይ
አይየት መልዕክት ያለው የትዕቢት ንግግር ተናገራቸው ። በዛች ቀን ሆን ብለው ሠባት
የተለያዮ የቁረይሽ ባላባቶች የሠይዲን ቅስም ለመስበር የትዕቢት ቃላቶችን እየተለዋወጡ
አጎረፉባቸው ።
ሠይዲ ( ሠ. ዐ.ወ) ከፋቸው ። ቀልባቸው ስብር አለ።እንዲህ ሲሉም ለራሳቸው አንሾካሾኩ
" ይህን ሪሳላ ከጀመርኩ 12 አመት ሆነኝ ። እነዚህ የቁረይሽ ባላባቶች እንኳን ባመጣሁት
ዲን ሊያምኑ ይቅርና "የነብይነት " አላማና ተግባር ምን እንደሆነ እንኳን ሊረገዱ አልቻሉም
። ይህ አሳዛኝ ነገር ነው ብለው ቀልባቸው ስብር አለ። "
ቀን እንደዛ ቀልባቸው ተሠብሮ እዛው ካዕባ ላይ ውለው ማታውኑ በሶፋና መርዋ መሃል ላይ
ወደ ሚገኘው ሠኞ ለሊቱ ረጀብ 27 ወደ ዑሙ ሃኒያ --- የአቡ ጧሊብ ልጅ --- የአልይ እህት
ቤት ሄዱ ። ቀልባቸው እንደተሠበረ ዑሙ ሃኒያ ገብቶታል ። ምን ሁነው ነው ብላ
ጠየቀቻቸው ። የሆነውን ሁሉ ነገሮት። እርሶም ብልህ ሴት ስለነበረች እንዲህ አለቻቸው "
ወላሂ አንቱ እውነተኛ እንደሆኑ ሁሉም ሠደቢዎቹ ያውቃሉ። ነብይ እንደሆኑ ሁሉም
ባላንጣዎቹዎ ያውቃሉ። የአንቱን ትክክለኛነት ዛሬ አይቱን ዝቅ ለማድረግ የትዕቢት
ንግግሮችን የተናገሩት በሙሉ ያውቃሉ። ነገር ግን ምቀኝነት ነው እንዲህ ሚያረጋቸው ።
ትዕቢትና ሂስድ ነው እንዲህ ያበላሻቸው ።ውስጣቸው የቆሸሸ ስለሆነ ነው እንዲህ አንቱን
ለመዝለፍ ያነሳሳቸው .... " እያለች ዑሙ ሃኒያ አፅናናቻቸው ። በዑሙ ሃኒያ ንግግር
የተወሠነ ተረጋጉና ኢሻን ሠግደው ሙሉ ለሙሉ የተሠበረው ቀልባቸው ሳያገግም እዛው
ላይ ሸለብ አሉ ....

ይቀጥላል.....



                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ


  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡
እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄