Get Mystery Box with random crypto!

ሌሊቱ ጨልሟል ....... እንደተለመደው ከልጆችህ አሊያም ከእናትና አባትህ ጋር ተጨዋውተህና ተ | °♡•የረሱል ኡማ°♡•

ሌሊቱ ጨልሟል .......

እንደተለመደው ከልጆችህ አሊያም ከእናትና አባትህ ጋር ተጨዋውተህና ተሳስቀህ እራትህን በልተህና ጠጥተህ ወደመኝታህ ክፍል ገብተሀል፡፡
ድንገት በሩ በዝግታ ተንኳኳ አንተም የግለሰቡን ማንነት ለማረጋገጥ ወደበሩ ጠጋ ብለ በዝግታ ማነው ስትል; ውዷና ማየቷን የምትናፍቃት እናትህ ዝግ ባለ ድምፅ "እኔ ነኝ ልጄ በሩን ክፈት" ... አንተም ፈጠን ብለህ ስትከፍት አይኗን በእንባ ተሞልቶ በፍቅር አይን ወዳንተ እየተመለከተች "ልጄ አደራህን ከኔ እንዳትርቅ እሺ ጠዋት ደግሞ የትላንቱ ቦታ ሄደን የምትፈልገውን ልብስ መርጠህ እንገዛና በዛው ለቅሶ ቤት እንገባለን፡ ደስ ካላለህም ደግሞ ከነገወዲያ ይሆናል ብቻ አንተ ደስ ሁንልኝ ብላህ እቅፍ ካደረገችህ በሗላ ተሰናብታህ ሄደች አንተም ነገ ስለምትመርጠው ልብስ እያሰብክ ስለ ነገ ውሎህ እያወጣህ እያወረድክ ብርድ ልብስህ ውስጥ ገብተህ ሳለ ድንገት ስልክህ የቫይብሬት ድምፅ ያሰማል፡

ስልክህን አውጥተህ ስትመለከት ከቀኑ 10ሰዓት ላይ ቀጥሮህ የነበረው ቤስት ጓደኛህ በምን ምክኒያት ከቀጠሮ እንደቀረህ ሊጠይቅህ እየደወለ ነው። አንተም "ኡኡ አሁንማ ባላነሳ ይሻላል ካልሆነ በጠዋት እደውልለታለው" ብለህ ወደ ትንሹ ሞት አሸለብክ (ተኛህ)

ከተወሰኑ ሰአታት በሗላ ስትነቃ አስፈሪ ሁነት አካባቢውን ወሮታል በግራ በኩል እናትህ ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ነው አባትህና ልጆችህ በድንጋጤ ፈዘዋል አራት ወጣቶች አንድ አነስተኛ ቃሬዛ ተሸክመዋል ከፌት ከፌት እየሄዱ ነው። አንተም "እማዬ ምን ሆናቹ ነው ማነው የሞተው ማንን ነው የተሸከሙት" ስትል መልስ የለም "እማዬ መልሺልኝ እንጂ" ...ዝም መልስ የለም ወደቀኝ ስትዞር ትላንት ቀጠሮውን ያፈረስክበት ውዱ ጓደኛክ አቀርቅሮ እያለቀሰ ነው ..አንተም "አህመዴ አፍ በለኝ እሺ ትላንት የቀረሁት..."ብለህ ገና ንግግር ከመጀመርህ ድምፁን ከፍ አድርጐ ወይኔ ወንድሜ ብሎ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል አንተም በአግራሞት ተውጠህ "ማን ይሁን የሞተው " እያልክ በማሰላሰል ላይ ሳለክ በስተ መጨረሻ የመቀበሪያ ቦታ ደረሱ የቀብር ስነስረዓቱ ታዳሚያን ሟቹን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲሰናበቱት ፌቱ ተከፍቷል አንተም አጋጣሚውን ለመጠቀም ሮጥ ብለህ የጀናዛውን ማንነት ስትመለከተው ያ አብዝተህ የምትወደው በጣም የሳሳህለት ለሱ ስትል አሄራህን በዱንያ የለወጥክለት ማታ ብርድ እንዳያገኝው ስትል ኢሻ ሰላትን ለጠዋቱ ቅዝቃዜ ስትል ሱብሂን የሰዋህለት ለሱ ክብሩ መጠበቅ መስዋትነት የከፈልክለት በዲንህ ያፈርክበት ያንተው ገላ ነው

.....ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን.......አስተውል ምናልባትም ይህንን ሁነት በተግባር ለማየት የቀሩህ ጊዜያት ከሰዓታት ላይበልጥ ይችላልና ይህ ፅሁፍም የመጨረሻ የምትሰማው ወይም የምታነበው ፅሁፍ ሊሆን ይችላልና ለዚህ የማይቀር ጉዞ እራስህን አዘጋጅ።

ለዚህም መነቃቃትንና መዘጋጀትን ይጨምርልህ ዘንድ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይሉናል

☞"ጥፈጥና ቆራጭ የሆነው
ሞትን ማስታወስ አብዙ"




@worldmuslims