Get Mystery Box with random crypto!

* ይህ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ታላቅ ምክር ነው።* *አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ | አቡኪ||የነቢ||OFFICIAL

* ይህ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ታላቅ ምክር ነው።*

*አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋ መጣና "ለዱንያም ሆነ ለአኼራ *የሚጠቅም ንግግር ለመጠየቅ መጣው" አላቸው ።*
*እሳቸውም ደግሞ "የመጣልህን ጠይቅ"*
*አሉት።*

* "ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው?"*
*እሳቸውም "አላህን ፍራ" አሉት*

* "ከሰው ሁሉ ሀብታመ* *ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው።*
*"ባለህ ነገር ተብቃቅተ አላህን አመስግን" አሉት*

* "ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል*
*"ለራስህ የምትወደውን* *ለሰዎች ውደድ"*
*አሉት።*

* "ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል*
*"በአላህ ተወከል"አሉት*

* "በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን*
*እፈልጋለው" ሲላቸው?*
*"ዚክር አብዛ" አሉት።*

* "ከሰው ሁሉ በላጭ* *ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን*
*እፈልጋለው?" ሲል*
*"ለሰው ጠቃሚ ሁን" አሉት።*

* "የተከበረና ቸር ሰው* *ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው*
*"ችግርህን ለፍጡር አትንገር" አሉት።*

* "ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ *እፈልጋለው?" ሲል*
*"አንተም እነሱ የወደዱትን*
*ውደድ" አሉት::*

* "ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህንመገናኘት እፈልጋለው" ሲል*
*"ጀናባህን በደንብ ታጥበ* *እስቲግፋር አብዛ ማልቀስ* *መተናነስ መታመም*
*አለብህ" አሉት።*

* "ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው"*
ሲላቸውም*
*"አላህን ልክ እንደምታየው ሁነክ ተገዛው" አሉት።*

* "ኢማኔ እንዲ ሞላ*
*እፈልጋለው" ሲል*
*"ፀባይህን አሳምር" አሉት።*

* "እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው" ሲል*
*"ተዋዱዕ አዘውትር" አሉት።*

* "ዱዓዬ ሙስተጃብ እንዲሆንልኝ እፈልጋለው?" ሲላቸው*
*"ሀራም አትብላ" አሉት::*

* "አላህን ከሚታዘዙ ሰዎች ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል*
*"ግዴታዎችህን ፈፅም" አሉት።*

* "በአላህ ዘንድ ትልቁ ሀሠና ወይም ደግ ሥራ የቱ ነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው*
*"መልካም ፀባይ መተናነስ እና *በበላ ላይ ሰብር ማድረግ ነው" አሉት።*

* "በአላህ ዘንድ የትኛው ስርዓት ነው መጥፎ ሥራ?" ሲል ሲጠይቃቸው*
*"መጥፎ ፀባይና ፍላጎትን መከተል ናቸው" አሉት*

* "በዱንያም ሆነ በአኼራ የአላህን ቁጣ የሚያበርድ ምንድነው" ሲል ጠየቃቸው?
*"ድብቅ ሰደቃ እና ዘርን መቀጠል ናቸው" አሉት።*

* "የቂያማ ቀን በአላህ ኑር ለመሰብሰብ*
*እፈልጋለው?" ሲል*
*"ሰውን አትበድል" አሉት*

* "የቂያማ እለት አላህ* *እንዲያዝንልኝ እፈልጋለው?"*
*"ለአላህ ባርያዎች እዘን" አሉት።*

* "የቂያማ ቀን የጀሀነም እሳት የሚያጠፋው ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው*
*"በችግር ላይ ወይም በሙሲባ ላይ ትህግስት መሰድረግ ነው" አሉት።*

* "የቂያማ እለት ነውሬ* *እንዲሸፈንልኝ እፈልጋለው?" ሲል*
*"የወንድምህን አይብ ሸፍን" አሉት።*

* "የቂያማ ቀን ከአላህ ቁጣ ሰላም ለመሆን*
*እፈልጋለው?" ሲል*
*"በአንድም ፍጡር አትቆጣ" አሉት።*


*አሏህ ሱብሃን ወተአላህ ባወቅነው በስማነው የምንስራ ያድርገን ኣሚን!**
@yenebiywedaj
@yenebiywedaj
@yenebiywedaj