Get Mystery Box with random crypto!

~ ጉዞው የቀልብ መሆኑን እወቅ ውድድሩ የሚለካው በመልካም ስራ ብዛት ብቻ አይደለም ይልቁንም ዋነ | حيات سحبا የምርጦች ትውልድ ታሪክ

~ ጉዞው የቀልብ መሆኑን እወቅ

ውድድሩ የሚለካው በመልካም ስራ ብዛት ብቻ አይደለም ይልቁንም ዋነኛው መለኪያ የቀልብ ልስላሴና ተቅዋ እንዲሁም ከወንጀል ፅዱ መሆን ነው። የዱኒያ ጉዞ በአካል የሚደረግ ሲሆን የአኬራው ግን ~ ቀ ል ብ ነው።

አንድ ሰው ወደ ዛሂዱ ኡበይ ዐሊ አድ ደቂቅ ምክር ፍለጋ ገሠገሠ "እርስዎ ጋር ለመድረስ ረጅም ርቀት መምጣቴ ነው። አላቸው። እርሳቸውም...

ጉዳዩ ረጅም ርቀት በማቋረጥ አይደለም። በእያንዳዱ እርምጃህ ከነፍስህ መራቅህን እርግጠኛ ሁን ፤ ያኔ ወደፈለከው ግብ ትደርሳለህ። ሲሉ የቀልብን ከፍተኛ ሚና ጠቆሙት።

መቶ ነፍስ ስላጠፋው ሰው ኢማም አር ራፊዒይ ያሉትን ተመልከት።..

ይህ ሰው ወደ አላህ የተጓዘው በቀልቡ በመሆኑ አንዷ እርምጃ ይልቁንም አንዷ ስንዝር ርቀት ከፍተኛ ዋጋ ተሰጣት። እዲህ አይነት ቀልብ ሳይኖረው ዓለምን በእግሩ ቢያካልል እንኳ በስጋው ውስጥ ከተቀበረው አጥንቱ የተሻለ ስብዕና አይኖረውም። ምስራቅ ውስጥም ይሁን ምዕራብ ስጋው መቃብሩ ነው። ከመሬት ጋር የሚያመሳስላቸው አንድ እውነታ አለ፤ ያም ያ ሰው ሙት መሆኑና እርሷ ደግሞ መቃብሩ መሆኗ ነው።


የቀልብ ጉዞ ከአካል ጉዞ ይበልጥ ወሳኝ ነው፤ ስንት አለ በአካሉ የአላህ ቤት የደረሰ ነገር ግን ከአላህ የተቆረጠ!

ስንት አለ እቤቱ ፍራሽ ላይ ተቀምጦ ሰማየ ሰመያትን ያዳረሰ!