Get Mystery Box with random crypto!

የነጠፉ ብእሮች አመለካከት አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ለእያንዳንዱ ችግር መፍትሔ አላ | የማለዳ ብስራት

የነጠፉ ብእሮች

አመለካከት

አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ለእያንዳንዱ ችግር መፍትሔ አላቸው። አሉታዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ደግሞ ለእያንዳንዱ መፍትሔ ችግሮች አሏቸው። አሉታዊ አመለካከት ካለቸው ሰዎች ራቁ።
አልበርት አንስታይን

ብቸኝነት

ብቸኝነት ሌላ ሰውን የምታጡበት ሁኔታ ሲሆን፣ ለብቻ መሆን ግን ራሳችሁን የምታገኙበት ሁኔታ ነው!
ኦሾ

የ"ዛሬ" ምሥጢር

ልትኖር እየተዘጋጀህ ከሆነ፣ ጨፍነሃል ማለት ነው። ህይወት ከፊትህና ወደፊት ያለ ከመሰለህ ያኔም ጨፍንሃል፤ ምክንያቱም ወደፊት የሚባል ነገር የለም። ያለው ዛሬ ነው። አብዛኞቻችን ጊዜያችንና ህይወታችን የሚያልፈው አንድ ቀን ያልፍልኛል፤ አንድ ቀን የተሻለ እኖራለሁ ብለን ዛሬን ችላ በማለት ነው። ነገ የለም። ያሉት ተከታታይ ዛሬዎች ናቸው። ዛሬን ስትኖር ማየት ትጀምራለህ፤ ልትጨፍን አትችልም።

ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ

ነጻነት

ይህ ነጻነት ደግሞ ከሰው ልጅ ፍላጎት ውጪ የሚሆንበት አንዳች ምክንያት የለም... ከዚህ በተጨማሪ ሕይወትን ያለአንዳች የሞራልና የወግ ገደብ የሚኖራት ሰው ደስታውም እንዲሁ ሙሉ እንደሚሆንና እንዲህ ዓይነቱ ደስታ ደግሞ ለጊዜው አስደስቶ የሚሰወር ሳይሆን በምድራዊ ሕይወት እስካለ ድረስ የሚከተል ነው ።

ፍሬድሪክ ኒቼ

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat