Get Mystery Box with random crypto!

#ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ . . . . #የኔ_ታሪክ! ክፍል - ፴፪ . . . '..ተያት ይች | የልቤ ድርሰት የብዕር ጠብታ

#ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፪
.
.
.
"..ተያት ይች አለም ለሐቅ የላትም ዳኛ፣
ልክ ባንሆንም ልክ ነን እኛ!"
.
.
..ናፍቆት እንባዋ ቀስ እያለ በጉንጯ ወደ ትራሱ እየወረደ አልጋዋ ላይ ጋደም ብላለች። የናፍቆት እናት የልጃቸዉን መጎሳቆል አይተው ቢከፉም የተወሰነው ዉሳኔ ለወደፊት ህይወቷ ጥሩ እንደሚሆን በማሰብ ዝም ብለው ቁጭ ብለዋል።
.
.
.
ኮነሬል ማንያዘዋል እና አማኑኤል የነዳጅ ማደያው አካባቢ ከባጃጅ ወርደው ትንሽ ከተራመዱ በኋላ አዲስ ምሪት የተመሩ ሰዎች ወደሚሰሯቸው ቪላ ቢቶች ተጠግተው ቁጭ አሉ።

ኮነሬል ማንያዘዋል ሊሰድቡትና ሊጮሁበት አስበው የነበረዉን ናፍቆት ከተናገረቻቸው መካከል.."አፍቅረህ አታዉቅም!?" ያለቻቸው በሃሳባቸው ዉልብ አለና መንፈሳቸው ሰከን አለ።
ጉሮሯቸዉን ጠረግ ጠረግ አደረጉና 'ይሄዉልህ አንተ ገና ታዳጊ ልጅ ነህ! ካንተ እኔ ብዙ ነገርን አይቻለሁ አሳልፊያለሁ! እና ልጄ ስላተ እምትለው እዉነት ቢሆን አንተም እዉነተኛ ፍቅር ቢኖርህም የኔን ብቸኛ ልጅ ላንተ አሳልፌ መስጠት አልችልም! የወጣትነት ፍቅር ሁላችንም አልፈንበታል! ከፍ ስትልና ልጅ ስትወልድ ትረዳኛለህ../'

ወሬአቸዉን አቋርጠው አማኑኤል አዩት አንገቱን ደፍቶ እያዳመጣቸው መሆኑን አስተዋሉና ቀጠሉ..'ገና ተማሪ ነህ! ቤት የለህም! ስራ የለህም! ከገጠር እንደመጣህም ሰምቻለሁ! እና በዚህ ሁኔታ ልጄን እንዴት አድርገህ ልታኖራት አስበህ ነው!? ይህንን ብቻ መልስልኝ!?!' አሉት..አማኑኤልም ቀና ብሎ አያቸዉና 'ለዚህ ጥያቄዎ መልስ እንደሌለኝ ያዉቃሉ! የቤተሰብ ሐብት ወይ ዉርስ የለኝም ገና ተማሪ ነኝ! ግን ልጅዋትን ከነብሴ አፈቅራታለሁ ከልቤ እወዳቲለሁ እና እሷን ደስተኛ ለማድረግና እርስዎ ይገጥማታል ብለው የሰጉትን ህይወት ሳታይ እንድትኖር ለማድረግ እኖራለሁ! ይሄን ብቻ ነው ልልዋ እምችል!!' አላቸው ፈርጠም ብሎ..

ኮነሬል ማንያዘዋል በትዝታ ወደ አለፈው ህይወቱ ቃኘት አድርጎ ተመለሰና የልጁን እና የአማኑኤልን ሁኔታ አሰበ..'ይሄዉልህ ገና ወጣት ስለሆንክ ልጄን እረስተህ ሌላ ሴት ለማፍቀር ጊዜ አለህ ስለዚህ ልጄን እርሳት! ከነገ ጀምሮ በዚህ መኖርን እናቆማለን ሐገር ልንለቅ ነው! በምንሄድበት ሐገርም ለርሷ እሚሆናትን እኔ ፈልጌ አጋባታለሁ! አንተም የራስህን ፈልግ! እንዲህ ተረጋግቸ የማወራህ እኔም አፍቅሮ ማጣትን ስለማዉቅ ነው! ከዚህ በኋላ ግን ከልጄ ራቅ ዝንቧን እንኳ እሽሽ እንዳትል! ብቸኛዋ ልጄ ካንተ ጋር ስታክ ማየትን አልሻም! የተደላቀቀ ህይወትን እሚሰጣት ጋር ነው መኖር ያለባት! አይ አልሰማም ካልክ ግን ዉርድ ከራስህ መላ ህይወትህን ነው እማበላሸው ነግሬሐለው!!' አሉት የተረጋጋው መንፈሳቸው እየታወከ..

አማኑኤል ወደ ኮነሬል ማንያዘዋል ላይ አፍጥጦ 'ምን አልባት እኔ የገንዘብ ደሃ ልሆን እችላለሁ እርሶ ግን የአስተሳሰብ ደሃ ነዎት! በጭራሽ ደግሞ ከኔ ይልቅ ብዙ ነገር አላሳለፉም አላዩምም! አሳልፈዉም ከሆነ ካሳለፉት ህይወት የተማሩት ይሄን ከሆነ የባከነ የህይወት ትምርህት ነው ያሳለፉት! እኔን እንዳሻዋ ማድረግ ይችላሉ ግን ቃል እገባልዎታለሁ ልጅዋትን የትም ብትሆን ፈልጌ የራሴ አደርጋታለሁ!!' አላቸው ደሙ ፈልቶ የመጣው ይምጣ በማለት.. ኮነሬል ማን ያዘዋል ከተቀመጡበት ተነሱና በለበሱት ከስክስ ጫማ አማኑኤል ፊት ላይ አሳርፈው አሽቀነጠሩትና..'ደሃ የደሃ ልጅ እንዴት ብትደፍር ነው እንዲህ እምትናገረኝ እንዲያዉም ከልጄ መድረስ ቀርቶ እርሷ ባለችበት ሃገር ካገኘዉህ እገድልሃለው!!' አሉትና የመጡበትን መንገድ ይዘው መሄድ ጀመሩ..

አማኑኤል ከወደቀበት ተነስቶ ድምፁን ከፍ አድርጎ..'የህዝብ ደህንነት እና ህይወት ጠባቂ ሁነው የኔን የወጣቱን ህይወት እንደነጠቁኝ መቼም እንዳይረሱ!!' አላቸው..ኮነሬል ማንያዘዋል ግን ወደ ኋላ ዞር ብለው ሳያዩ ሄዱ..

አማኑኤል ጉትትት እያለ ወደ ሎዛ ማርያም ቤተክርስቲያን ገብቶ ዋናው በር ላይ በጉልበቱ ተንበርክኮ ተደፋ አይኑ እንባ ሞላ..ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ..እራሱን ጠላ..ድሃ መሆኑ ያሳጣዉን ፍቅር ሲያስብ መፈጠሩ አስጠላው በራሱ አዘነ..!! ስለናፍቆት አሰበ ምን እንዴት ሁና ይሆን ብሎ ተጨነቀ..በርሱ ድህነት ምክኒያት እርሷም ባልፈለገችው መንገድ ልትኖር መሆኗን ሲያስብ በራሱ ተናደደ ግፍ የሰራባት ያህል ተሰማው..እዚያ ከቤተክርስቲያኗ ኩርምት ብሎ ቁጭ አለ..
.
.
.
መልአክ ከማርታ እልፈት በኋላ እራሱን መሆን አልቻለም። ከቤተሰቡ ጭምር ገለል ብሏል ቅዳሜና እሁድ ለይስሙላ ግቢ ይሄዳል ይመለሳል..ከሰኞ እስከ አርብ ፀበል ይጠመቃል..ቤተክርስቲያን ዉስጥ እሚሰጡ ትምርቶችን መከታተል ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ከቀን ቀን እየተሻለው መቷል..የተለያዩ መጽሐፍትንም በማንበብ እራሱን መገንባት ጀምሯል..ህይወትን ባቆመባት መቀጠል እንዳለበት በማሰብ እንዳዲስ 'ሀ' ብሎ ጀምሯል..
.
.
.
ናፍቆት አማኑኤል ልታገኝ እምትችልበት ሁኔታ እንደሌለ ስላወቀች ወረቀትና እስክርቢቶዋን አገናኝታ አጭር ደብዳቤ ቢጤ ፅፋ በጡት ማሰሪያዋ ዉስጥ አስቀመጠች..
.
.
.
መልአክ በለሊት ቤተክርስቲያን ተሳልሞ ከእግዜር ሰላምታ በቀር መቅረቡን የነሳቸዉን ሰዎች በማሰብ ወደነ ናፍቆት ቤት አቀና..በቦታው ሲደር የናፍቆት እናት ጎረቤቶቿን እየተሰናበተች ናፍቆት አንገቷን ደፍታ ቁማ ኮነሬል ማንያዘዋል ወዳዘጋጀው መኪና እቃ እየጫነ ደረሰ..ግራ ገብቶት ወደ ናፍቆት ተጠጋና 'ትንሿ ምን ተፈጥሮ ነው የት ልትሄዱ ነው?!' አላት..ናፍቆትም በሃይል አቀፈችዉና አለቀሰችና ደብዳቤዉን ብጁ እያስጨበጠች ሁሉንም ነገር አማኑኤል ይነግርሃል ይችን ብጣሽ ወረቀትም ለርሱ ስጥልኝ አለችው.. መልአክ የመናገር እድሉን ሳያገኝ ናፍቆት ወደ መኪና ገባች..በመኪናው መስኮት እጇን እያንቀሳቀሰች "ቻው!" አለችው..መልአክ "ቻው!" እሚለዉን ቃል ሲሰማ ደነገጠ ነገሩ የከረረ መሆኑ ተረዳ..እጁን እያዉለበለበ "እንገናኛለን!" አላት..
.
.
.
አማኑኤል በርቀት ከፍ ያለ ቦታ ሁኖ ከካምፕ የወጣችዉን መኪና አየ..እየሮጠ ለመድረስ ሞከረ ግን አልቻለም..ሄደች..ከርሱ እራቀች..የመንገዱ ዳር ላይ ተዘርሮ አለቀሰ..ልቡን ቅዝቃዜ ተሰማው..ነብሱን ጨለማ ዋጣት..
.
.
.
"መለያየት ሞት ነው ለተዋደደ ሰው..!"
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23

join and share
@YelbeDrset
@YelbeDrset

inbox me @amanYTZ23