Get Mystery Box with random crypto!

#ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ . . . . #የኔ_ታሪክ! ክፍል - ፴፩ . . . ..አማኑኤል የሚ | የልቤ ድርሰት የብዕር ጠብታ

#ተከታታይ_ልብ_ወለድ_ታሪክ
.
.
.
.
#የኔ_ታሪክ!

ክፍል - ፴፩
.
.
.
..አማኑኤል የሚከራይ ቤት ባለማግኘቱ ሶስት ቀን አልጋ ለማያዝ ተገደደ.. እንደፈለገው ተንቀሳቅሶ ክራይ መፈለጉ ከባድ ስለሆነ ለደላላዩች ማስፈለጉን ቀጠለ.. ወይዘሮ መብራቴ ከወጭ አንፃር እና አሁን ስለተሻለው እራሱን እንደሚንከባከብ ነግሯት ወደ ቀየዋ እንድትሄድ አሳመናትና ሳትፈልግ ሄደች።

ወይዘሮ መብራቴ ከጎንደር በወጣች በሰልስት ቀኗ አማኑኤል ቀበሌ ፲፬ ዉስጥ ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆነች ለጭስ ቤት ታስባ የተሰራች ዶርም አጊንቶ ተከራየ..የዩኒቨርስቲ ትምርቱንም ባፃፈው የህክምና ማስረጃ በማቅረብ ዊዝድሮ ሞላ..ጎንደር ላይ ያቆመዉን ህይወት ቀጠለ..

ናፍቆት ከእጅ የወጣች አፈንጋጭ ሁናለች..ከቤት ስትወጣ ማንንም አታስፈቅድም ዝም ብላ ጥወጣለች ዝም ብላ ትገባለች..ከአማኑኤል ጋር እንዳድስ ተዋዉቀው ጓደኞች ሁነዋል በቀን አንዴ ሳታየው አትዉልም። እረሳሁሽ ቢላትም እንዲያስታዉሳት ሳትጎተጉት እንዳዲስ ፍቅር ልታሳድርበት እየጣረች ነው። አማኑኤል በበኩሉ ሁሌ እንዳዲስ ነው በፍቅሯ እሚዎድቅ..

ቀኖች ነጉደው ሳምንታት አልፈው ክረምቱ አለቀ አዲስ አመት ብቅ አለ። ወይዘሮ መብራቴ አዲስ አመትን ከልጃቸው ጋር ለማሳለፍ ጎንደር ተከሰቱ..አዲስ አበባ እያሉ ጀምረው በቀያቸው እሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ቦታዉን ሸንሽነው ሸንሽነው ለጎረቤታቸው ሽጠው ጨረሱት..ቤቱ ካረፈበት ቦታ ዉጭ መላ ግቢው በአቶ አለማየሁ ስም ሆነ..

አዲስ አመት በተርካሳዋ የቆርቆሮ ቤት በጥሩ አለፈ..ወይዘሮ መብራቴ ናፍቆት ከልጃቸው ለማራቅ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ስለተገነዘቡ ችላ አሏት። ናፍቆት ከአዘዞ አንስታ ወደ ቀበሌ ፲፬ ያለዉን መንገድ ቢያን አንዴ ትመላለስበታለች። አማኑኤልም ይሄን ሁሉ በማየት እዉነቱን ሊነግራት ቀን ቀጥሮ ምቹ ሁኔታን ይጠብቅ ጀመር።

ወይዘሮ መብራቴ ለአዲስ አመት ብለው ጎንደር ቢመጡም በዛው የስቅለትን በዓል አክብረው ወደ መጡበት ተመልሰው ሄዱ..

ጥቅምት ወር መግቢያ ቀኖች ላይ አማኑኤል ለናፍቆት ደዉሎ ወደ ዶርም እንድትመጣና እሚነግራት ትልቅ ነገር እንዳለ አሳወቃት። ናፍቆትም በደስታ ተሞልታ ተስማማች። ቀጠሯቸው ለከሰዓት ስለነበር ናፍቆት ረፋዱ ላይ ምሳዋን በልታና ልብስ ለባብሳ ትጠባበቅ ጀመር። አማኑኤልም በበኩሉ አንድ ወይን ገዝቶ የወይን መጠጫ ከአከራዮቹ ለምኖ ያችን ተርካሳ ዶርም አፀዳድቶ እየጠበቃትነው..

ሰዓቱ ልክ ሰባት ተኩል ሲል ናፍቆት ከተቀመጠችበት ተነስታ ልትወጣ በሩ ላይ ስትደርስ የት እንዴት እንደመጣ ያላየችው አባቷ ኮነሬል ማንያዘዋል ከፊቷ ድንቅር አለ።
.
.
.
አማኑኤል የእጁን ሰዓት እና የስልኩን ሰዓት እያፈራረቀ ያያል..ዘገየች..በጣም ዘገየች..የስልኩን ቁልፍ ነካክቶ ደወለ ስልኳ አይነሳም..ደጋግሞ መደወሉን ቀጠለ..አይነሳም..ጭንቀት ዉስጥ ገባ እሚያደርገው ቅጡ ጠፋው..
.
.
.
ናፍቆት እንደሞት ጣረሞት ከፊቷ የተደነቀረው አባቷ አስደንግጧት ወደ ኋላ ሸሽታ ዘፍ ብላ ቁጭ አለች..ኮነሬል ማንያዘዋል አይኑን አፍጥጦ 'ወደየትም መሄድ አትችም! ማንንም ማግኘት ሆነ ስልክ ማዉራት አትችይም አርፈሽ ቁጭ በይ!' አለና የእጅ ስልኳን ቀማት..

ናፍቆት አይጥ እንደዋጠች ድመት ዝም አለች። አባቷ ሌላ ሰው ሁኖ ታያት እጅግ ፈራችው። ኮነሬል ማን ያዘዋል ወንበር ስቦ ከናፍቆት ፊት ለፊት ቁጭ አለና ምሬት የቀላቀለ ቁጣ አወረደባት..
'እንዴት ብትበላሽ ነው ከቤተሰቦችሽ ፍቃድ እንዲህ የተንዘላዘልሽ ለዱርየ ብለሽ ስንት መከራየን አይቸ አሳድጌሽ ያዋረድሽኝ! ለነገሩ አንች ጋር ንግግር ምንም ጥቅም የለዉም! እማደርገዉን እኔ ነኝ እማውቅ! አሁን የልጁን አድራሻ ብቻ ንገሪኝ!?!' አላት..

ናፍቆትም በመንተባተብ..'አ..ባየ ይሄዉልህ እ..መጀመሪያ ተረጋጋ..ልጁ ምንም አላደረገም እኔ ነኝ ወደርሱ እየሄድኩ ካልወደድከኝ እያልኩ እማስቸግረው! እባክህ አባየ እርሱን ምንም ነገር ለማድረግ እንዳትሞክር እኔ ያልከኝን ሁሉ አደርጋለሁ!' አለችው እንባዋ ካይኗ አልፎ መሬት ላይ እየተንጠባጠበ..'ኧረ እንደዛ ነው! ጭራሽ ትከላከይለታለሽ!? ጥሩ እሽ! እስካሁን ካደረግሽው አንፃር እንዲህ እንደሚፈጠር አስቤው ነበር! ሁሉም ነገር እዚህ ላይ ያበቃል! በከረምኩበት ሃገር ቤት ገዝቻለሁ ከነገ በኋላ ወደዛ እንሄዳለን ካሁን በኋላ እዚህ ምንም አናደርግም! እናትሽም በሃሳቤ ተስማምታለች! ለኔም ከጎኔ መሆናቹህ ጥሩ ነው! አንችም ትምርትሽን ትቀጥያለሽ! አንዷ ልጄ ስትበላሽማ ዝም ብየ አላይም! በይ ማልቀስሽን አቁሚና ልብስሽን ሸካክፊ!!'
'ምን..የምርህን ነው አባ..ኧረ ተው እንዲህማ አታድርግ! በቃ እኔ ወደ እርሱ አልሄድም! ከዚህ ግን አታርቀኝ! ክባክህን አባየ ይቅርታ አድርግልኝ! ፍቅር ይዞኝ ነው! ከአቅሜ በላይ ነው! ከአማን ይሄን ያህል እርቄ መኖር አልችልም! እባክህ ተረዳኝ! በጣም ጨካኝ ነህ! አፍቅረህ አታዉቅም!!!' የልቦን ሁሉ አዉጥታ ጮኸችበት..

ኮነሬል ማንያዘዋል ለመጀመሪያ ጊዜ እጁን አንስቶ ናፍቆትን ፌንት በሚያሰራ እጁ በጥፊ መታትና..
'ኧረ ጥሩ ምላሰኛ ወቶሻል ጭራሽ ትመልሽልኛለሻ..ጥሩ በዉሳኔየ ጭራሽ እንደማልቆጭ ነው ያረጋገጥሽልኝ! ደግሞ በዚህ እድሜሽ ስለ ፍቅር ታወሪያለሽ!! ወይኔ ማንያዘዋል ከሰርኩ ተዋረድኩ!!' ብሎ ቀጥጣ የልብስ ሻንጣዋን አንስቶ ልብሶቿን ማስገባት ጀመረ..ናፍቆትም ጉንጯን ይዛ እያለቀሰች ትለምነው ጀመር..

የናፍቆት እናት ከጎረቤት ቆይታ ስትገባ አባትና ልጅ እየተጨቃጨቁ አገኘቻቸዉና..በመደናገጥ ዘለው ባለቤታቸዉን እጅ ይዘው ናፍቆት እንዳይመታት ተከላከሉት..'ምንድን ነው ምን እያደረክ ነው! ልጄ ላይ እንዴት እጅህን ታነሳለህ!' አሉት.. ኮነሬል ማንያዘዋልም..'አንች ነሽ ለዚህ ሁሉ ምክኒያት በስርዓት ያሳደኳትን ልጄን እንዲህ ያበላሸሻት!! አሁን ቀጥታ እቃቼን ሸካክፈን ነገ በጥዋት ከዚህ ለቀን እንወጣለን!!' አላትና ቀድሞ ሁሉንም አብረው ስላቀዱ ዝም አለችው እና ናፍቆትን ወደ ማረጋጋት ገባች..
.
.
.
አማኑኤል በጣም ተጨነቀ እና ተርካሳዉን ዶርም ቆልፎ ወጣ..የምስራች አካባቢ ታክሲ ጠበቀና ወደ አዘዞ ተፈተለከ..

ኮነሬል ማን ያዘዋል የናፍቆት ስልክ ላይ ደጋግሞ ሲደወል የነበረዉን ስልክ ወደራሱ ስልክ ገልብጦ ደወለ..ስልኩ ከዛኛው ጫፍ ተነሳ..
'ሄሎ?'
'ሄሎ የአማኑኤል ስልክ ነው?'
'አዎ ነው! ማን ልበል?'
'የናፍቆት አባት ነኝ! ናፍቆት ትንሽ ስላመማት እና ልታይህ ስለፈለገች ወደ አዘዞ መምጣት ከቻልክ ብየ ነበር!' አለው እንደምንም ቁጣና ንዴቱን ተቆጣጥሮ በማስመስል..አማኑኤል በጣም ግራ ቢገባዉም እና የሰማዉን ለማመን ቢከብደዉም..'እሽ እየመጣሁ ነው መንገድ ላይ ነኝ!' ብሎ ስልኩን ዘጋው..

ኮነሬል ማንያዘዋል አማኑኤልን ሲያገኘው ምን እንደሚያደርገው ሲያወጣ ሲያወርድ ቆየና አማኑኤል አዘዞ መድረሱን ደዉሎ ሲያሳዉቀው ከካምፕ ወጣና በሩ ላይ እንዲመጣ ነገረው..አማኑኤል ፈራ ተባ እያለ ኮነሬል ማንያዘዋልን አገኛቸዉ..

ኮነሬል ማንያዘዋል አይናቸው ደም መስሎ የዉሸት ፈገግታ ፊታቸው ላይ ለጥፈው አማኑኤልን ሰላምታ ሰጡትና ትከሻው ላይ እጃቸዉን ጣል አድርገው 'ናፍቆትን ከማግኘትህ በፊት እስኪ እኔ እና አንተ እናዉራ!' አሉትና ባጃጅ ይዘው ወደ 'አጣጥ' መስመር የሚወስደዉን መንገድ ይዘው ሄዱ..አማኑኤል ልቡ በፍጥነት እየመታ ፍራት እየተሰማው ነገሩ ቢጨንቀዉም ምንም ማድረግ አልቻለም..
.
.
.

..ይቀጥላል..

Aman YTZ
@amanYTZ23