2022-01-08 00:24:05
ጭንገፋው በቃ ተገኘ ምሕረት
በእህት ሰላም
ተንኮለኛው እባብ አዳምንና ሴትቱን ስላሳተ በተንኮል
በአንተና በሰትቱ መካከል በዘርሕና በዘርዋ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ ራስህንም ይቀጠቅጣል አንተም ሰኮናውን ትቀጠቅጠዋለህ ፤
እግዚአብሔር አምላክም አለ፦
እነሆ አዳም መልካሙንና ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ ከህይወት ዛፍ እንዳይበላ ለዘላለም ህያው ሆኖ እንዳይኖር አደረገው።
እግዚአብሔር አዳምን ከኤደን ገነት አወጣው
በአንተና በሰትቷ መካከል በዘርህና በዘርዋ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ እርሱም ራስህን ይቀጠቅጣል ብሎ ቀጠሮ ሰጠ እንጅ በል ተነሳና ቀጥቅጥ አላለውም
አዳምም ሆነ በሴትቱ የተወለዱ ልጆቻቸው
እነ ቃዬን እነ አቤል እባቡን ለመቀጥቀጥ አቅም ስለሌላቸው የእባቡን ጭንቅላ ልቀጠቅጡ አልቻሉም
እንድሁም ሙሴ ፌርኦንን አሸነፈ እንጅ
ከፌርኦን በስተጀርባ ያለውን ልያባርር አልቻለም
ዳውትም በ እግዚአብሔር ፍት እየሄደ አምላኩን አስደሰተው ደግሞም ፍልስጠማውያንን አተረማመሳቸው
ይሁን እንጅ አንድም ሴጣን አላወጣም
ገና ክፉ መንፈስ የገባበትን ሳኦልን ሸሸው
ኤልያስም ብሆን ሰማይ ያስከፍታል
እምነቱ ሀያል ነው ስያስፈልግ ያዘጋል
አምላኩን ይለምናል ድንቅ ታምራትን ይደርጋል
ይሁን እንጅ አንድም ሴጣን አላወጣም በፅዮን የምኖር
እልፍ አእላፍት የምሰግዱለት 24ቱ ሽማግሌዎች ከፍቱ ሳይርቁ የምሰግዱ ቀን ከሊቲ ያ ሁሉም ሆኖ ከእኛ ፍቅር ጋር ስላልተመጣጠነለት ሀያሉ ጌታ፦
ወገኔ በከንቱ ተወስዶአል አሁንስ በዝህ ምን አለኝ ብሎ
የእባቡ ጭንቅላት የመቀጥቀጡ ግዜ ደርሶ
መንፈስ የነበረው ስጋን ለብሶ የሴጣንን አናት መቀጥቀጥ የምችለው ጌታ ባልታሰበና ባልተጠበቀ መንገድ መጣ።
" እነሆ ድንግል ትፀንሳለች
ወንድ ልጅም ትወልዳለች
ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች "
የተባለው ይፈፀም ዘንድ የትንብቱ ቃል
እነሙሴ ስለ እኔ ፅፈዋል ስል የነበረው
በምድር ላይ ነግሳለሁ ብሎ ያሰበው
ወደ አለም ስመጣ ያ ሀያሉ ጌታ አለቀለት በቃ አጋንንት ተመታ ሰው መንገድ ማለፍ እስክሳነው ድረስ
እጅግ ክፉ የነበረው ያ ሌግዎን መንፈስ
"እየሱስ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ ከአንተ ጋር ምን አለኝ
ግዜው ሳይደርስ ልታሰቃየኝ ወደ እዝህ መጣህን" እያለ ጮኼ ።
ግጥም፦ #ጭንገፋው_በቃ_ተገኘ_ምሕረት
ሰይጣን ግዜውን ረስቶ
ሳአቱ መድረሱን አላወቀም ከቶ
እየሱስማ ግዜውን ጠብቆ ሰዐቱን አይቶ
የእባቡን አናት ልቀጠቅጥ ከዙፋኑ ተነስቶ
እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ እንዳይበላ
ባስቀመጠው ስፍራ ለዘላለም ህያው ሆኖ እንዳይኖር ከኤደን ገነት የወጣውን የአዳምን ዘር
ከተበታተኑበት ሰብስቦ ሀጥያታቸውን ይቅር ልል
አምላክ ስጋን ለብሶ ወደ ምድር መጥቷል/2*
አምላክነቱን ትቶ የባርያን መልክ ይዞ
ክብሩን ጥሎ ፍቅርን ይዞ
የልጆቼ እስራት በቃ ከእንግድህ ብሎ
ከራሱ ጋር ልያስታርቀን ራሱን አዋረደ
የተወለደው ህፃን ሆነ የአለም ብርሃን
በቤቴልሄም ተወልዶ በከብቶች በረት
መድሀንት ሆነ አመጣ ምሕረት
ምስጥሩ የገባቸው የህፃኑ ማንነት
አማኑኤል ነው አሉ ወድቀው ሰገዱለት
ሰባ ሰገዶቹ የዕጅ መንሻ አመጡለት
#ጭንገፋው_በቃ_ተገኘ_ምሕረት / 2*
አምላክ በስጋ የተገለጠበት ትልቁ አላማ
እኛን ለማዳን ነው ከእባቡ ግዛት
ሀሉን እየቻለ ሁሉ የዕርሱ ሆኖ
ፍቅር አስገድዶ አላስችል አለው
በእባቡና ጊንጡ ላይ ስልጣን ሰጠን
አጋንንት ምንቀጠቀጥበትን ስሙን አሳወቀን የምናሸንፍበትን መንገድ አሳየን የልጅነትን
ስልጣን መልሶ አወረስን
እባቡን ለመቀጥቀጥ አጋንንትን ለማውጥት
ስልጣን ሰጠን ወርዶ ከሰማያት
ቀድሞ ወገን ላልነበረን ወገን ልሆነን
በሽተኞች ሳለን መድሃንት ልሰጠን
በጨለማ ሳለን ብርሃን ልያበራልን
የምንሸሸውን ክፉ መንፈስ እንድንገስፀው
የእባቡን አናት እንድንቀጠቅጠው
ከኤደን ገነት የወጣነውን የአዳምን ዘር
ዳግም እንድንወለድ ከውሀና ከመንፈስ
#የሁሉ ቤዛ የሆነ መጣ እየሱስ /2*
በእ/ት ሠላም
join join join
&
@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH
711 views21:24