Get Mystery Box with random crypto!

#የልብስና_የአለባበስ_ነገር ( ለብዙዎች በረከት የሆነች ት/ት / #ልብስ ለሌላው ሰው መታየት | ይሰበካል የእዉነት ወንገል

#የልብስና_የአለባበስ_ነገር ( ለብዙዎች በረከት የሆነች ት/ት /

#ልብስ ለሌላው ሰው መታየት የሌለባቸው የሰውነት ክፍሎቻችንን ለመሸፈን እንዲሁም በልብሱ ዲዛይን ምክንያት የሚገኘውን ውበት ለመላበስ የሚለበስ ነው። ሌሎችም ብዙ ጥቅሞች ሊኖሩት እንደሚችሉ እሙን ነው። ሰዎች እንደየ አቅማቸው ያምርብኛል የሚሉትን ልብስ ገዝተው ወይም አሰርተው ይለብሳሉ! ሴቶችም ወንዶችም።

#አለባበስ ጋ ስንመጣ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸው የሚመለከታቸውን ሰው ወደሌላ ነገር(ምኞት) ይመራል በሚል እህቶች ላይ ቅሬታ ሲቀርብ ይስተዋላል! አንዳንድ እህቶችም "እህቴ እንዲህ ባትለብሺ ጥሩ ነው"የሚል ምክር ሲሰጣቸው ከመቀበል ይልቅ " ስለእከሌ ምን አገባኝ ደግሞስ ማን እየኝ አለው!" የሚል ከመፅሃፍ ቅዱስ እይታ ውጭ የሆነ መልስ ሲመልሱ ይስተዋላል።

#እህቴ የፈለግሽውን ልብ መልበስሽ መብትሽ ነው ነገር ግን ያ የለበስሽው ልብስ የሚያይሽን ሰው በውስጡ ስጋዊ ምኞት የሚፈጥርበት ከሆነ አንቺም ይህም ወንድም በጥፋት ውስጥ ትሆናላችሁ። ስለዚህ ነው የምትለብሺው ልብስ ውበትሽን ከመጠበቅና ሰውነትሽን ከመሸፈን አልፎ በተመልካች ልብ ውስጥ ኃጢአት እንዲወለድ የሚያደርግ ምኞት እንዲፀነስ እንዳያደርግ ነው አለባበስሽን ማስተካከል ያለብሽ

አንዳንድ እህቶች ጡታቸውን፣እምብርታቸውን፣ታፋቸውን፣ዳሌያቸውን የሚያሳይ ልብስ ይለብሳሉ። ብዙ ወንዶችንም ይስባሉ! እህቴ እርግጠኛ መሆን ያለብሽ ነገር ጡትሽን አይቶ የመጣ ወንድ አንቺን ፈልጎ ሳይሆን ጡትሽን ነው። #አንቺ_ደግሞ_ጡትሽ_አይደለሽም
አንዳንድ የሰውነታችን ክፍሎች በልብስ እንዲሸፈኑ የተደረጉት በቀላሉ እንዳይገኙና የፈለጋቸው አካል ዋጋ መክፈል እንዳለበት ለማሳወቅም ጭምር ነው። ገላለጥሽው ማለት ግን ዋጋውንና ዋጋሽን አሳጣሽው ማለት ነው።

#ወንድሞች

የአለባበስ ጉዳይ ብዙ ጊዜ እህቶች የሚወቀሱበት ነገር ቢሆንም አንዳንድ ወንድሞችም ስሜት ቀስቃሽና ፍኞት ፈጣሪ ልብስ ሲለብሱ ይስተዋላሉ!
ለምሳሌ:-
ከእህቶች ጋር ሲሆን የደረት ቁልፍ በመክፈት ደረትን ማሳየት(ጡትን ከፍቶ እንደማሳየት ይቆጠራል)
የብልትን ቅርፅ የሚያሳይ ሱሪ መልበስ ሴት ልጅ በጣም ስስ ታይት እንዳደረገች ያክል ነው።

በነገራችን ላይ እህቶችም ወንድሞችም አንድን ልብስ ስትለብሱ ያምርብኛል፣ሌሎች ወደኔ እንዲሳቡ ያደርጋል በሚል እይታ ስለሆነ ማማሩ የሚደገፍ ቢሆንም ልብሳችሁን አይቶ የመጣው ሰው በስሱ ወይም በግላጭ የሆነ ውድ ነገር ስላሳያችሁት እንጂ እናንተነታችሁን ፈልጎ ላይሆን ይችላል! ስለዚህ ውድ የሆነ ማንነታችሁን በተገላለጠ ልብስ አታሳንሱት!

ምርጥ አለባበስ ማለት ለራስ ውበት እያሰቡ ለሌላውም እያሰቡ ሲሆን ነው።
ክርስትና ለጌታም ለሰዎችም መኖር ነው! ክርስትና እንደፈለኩኝ ብሆን ሌላ ሰው ምን አገባው የሚባልበት አይደለም!

ክርስቲያን ነሽ/ህ አዎ ከሆነ መልሱ በአለባበስሽ/ህ ጌታን አ
ክብር/ር ለሰዎች ፈተና አትሁኚ/ን።

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

የመወያያ @Marantawoch