Get Mystery Box with random crypto!

@Yeihunetwongl #አላውቅም ምክንያቱ። አንተ ስትለየኝ ምድር ታስከፋኛለች እህል በትኜባት | ይሰበካል የእዉነት ወንገል

@Yeihunetwongl
#አላውቅም ምክንያቱ።

አንተ ስትለየኝ ምድር ታስከፋኛለች
እህል በትኜባት እሾህ ታበቅላለች

አንተ ስትለየኝ ሰው አይረዳኝም
በፊቱ እያነባሁ ዞር ብሎ አያየኝም

አንተ ስትለየኝ ተስፋ ከእኔ ይርቃል
ለስው እየበራ ለእኔ ይጨልማል

አንተ ስትለየኝ አጥብቄ ያሰርኩት በድንገት ይፈታል
ጨብጬ የያዝኩት ከእጄ ፈሶ ያልቃል

አንተ ስትለየኝ ፀሀይ ለእኔ አትወጣም
ለሊቱ ይረዝማል ለእኔ ቶሎ አይነጋም

አንተ ስትለየኝ አቅሜ ይከዳኛል
ቀላል ንፋስ ነፍሶ ገፍቶ ይጥለኛል

አንተ ስትለየኝ ዝም ብሎ ይከፋኛል
ሰው ሁሉ እየሳቀ እኔ እንባ ያንቀኛል

አንተ ስትለየኝ ከሰው ጋር አልገጥምም
ደስታ ከእኔ ይርቃል ሰላም አላገኝም

አንተ የልቤ ጌታ ከአፈር የፈጠርከኝ
አንተ ስትለየኝ እንዲህ ነው የሚያደርገኝ
ለአፍታ ስትለየኝ ፊትህ ከእኔ ሲዞር
የለም ወዳጄ ሆይ እኔ ያልሆንኩት ነገር

ፈጥነህ ካልደረስክልኝ ካላገኘኝ እጅህ
ባክኜ እጠፋለሁ እኔ ምስኪን ልጅህ

አንተ የነፍሴ አምላክ እባክህ እራራልኝ
ልብህ ለእኔ ይዘን ምህረትህን ላክልኝ
አንተ ስትለየኝ ሁሉን ነገር አወኩ
እኔ ያለ አንተ ምንም እንዳልሆንኩ

@yeihunetwongel