Get Mystery Box with random crypto!

ድንቅ ሕይወት ለመኖር እና ሕልምህን ለማሳካት፣ ማንም አንዳች ነገር እስኪያደርግልህ መጠበቅ የለብህ | የሕሊና እረፍት

ድንቅ ሕይወት ለመኖር እና ሕልምህን ለማሳካት፣ ማንም አንዳች ነገር እስኪያደርግልህ መጠበቅ የለብህም።

ሕልሙ ያንተ ነው፤ የታየህም ለአንተ ነው። ስለዚህ መከፈል ያለበትን ዋጋ መክፈል ያለብህ አንተ ራስህ ነህ።

አንተ ለሕልምህ ምንም ዐይነት ዋጋ ሳትከፍል፣ ሌሎች ሰዎች ለአንተ ሕልም ዋጋ እንዲከፍሉ መጠበቅ የለብህም። አንተ ለሕልምህ የመጨረሻውን ዋጋ እና አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ሁሉ ስትከፍል፣ ሌሎች ሰዎች ሊረዱህ ይችላሉ። ራስህን ስትቀይር፣ ሌሎች ሰዎችም ሊቀየሩ ይችላሉ። ራስህን ሕልሙን ማሳካት ወደሚችል ሰውነት ስትቀይር፣ በአካባቢህ ያሉ ሰዎችም ሕልምህን እንድታሳካ ሊረዱህ ይችላሉ። ራስህን ስትቀይር፣ ሁሉም ነገር መቀየር ይጀምራል።

ሕይወትህ፣ ቤተሰብህ፣ ሥራህ፣ ገቢህ፣ ጤንነትህ እንዲሁም የምትፈልገው ነገር ሁሉ እንዲቀየር፣ በመጀመሪያ አንተ መቀየር አለብህ። ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው። (ዳዊት ድሪምስ)

አሰተያየት ለመስጠት @Rawdaabas

ወደ ቤታችሁ ለመግባት https://t.me/yehelinairaft