Get Mystery Box with random crypto!

ባውንድሪ ማለት ጨዋነትና ሚዛናዊነት ማለት ነው! የአብዛኛው የግንኙነት ቀውስ የሚከተለው ሰዎች የ | የሀሳብ መንገድ

ባውንድሪ ማለት ጨዋነትና ሚዛናዊነት ማለት ነው!

የአብዛኛው የግንኙነት ቀውስ የሚከተለው ሰዎች የራሳቸውን ባውንድሪ (ቀይ መስመር) በሚዛናዊነት ሳያስክብሩ ሲቀሩና ሰዎች እንደፈለጉ እንዲያደርጓቸው ሲፈቅዱ ነው፡፡ እነሱም ቢሆኑ የሰውን ባውንድሪ ካላከበሩ ለግንኙነት ቀውስ ምክንያት መሆናቸው አይቀርም፡፡

የራሳችንን ባውንድሪ አስከብረንና የሰውን አክብረን ልኩን ያወቀ ሕይወት እንዳንኖር የሚያደርጉን ደግሞ በሕብረተሰቡ መካከል የሚዘዋወሩ አፈ-ታሪዎች ናቸው፡፡

አፈ-ታሪክ #1:- “የቀይ መስመር ወሰን ማበጀት ማለት ራስ ወዳድነት ነው”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የቀይ መስመር ያለው ሰው ራስ ወዳድ ሳይሆን ራሱን በሚገባና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የሚያከብር ሰው ነው፡፡

አፈ-ታሪክ #2:- “የቀይ መስመር ሲኖረኝ ከሰዎች ጋር ያለኝ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ እውነታው፣ የቀይ መስመሩን በተገቢው መልኩ ያሰመረ ሰው ከሚኖረው መርህ-ተኮር ግንኙነት የተነሳ በአካባቢው ያሉ ጤና-ቢስ ሰዎችን ምቾት ላይሰጣቸው ቢችልም ሁኔታ ግን ጤና-ቢሶቹን ሲያርቃቸው፣ ጤናማዎቹን ግን የበለጠ ሊያቀርባቸው ይችላል፡፡

አፈ-ታሪክ #3:- “የቀይ መስመር ሲኖረኝ በሰዎች እንድጠላ እሆናለሁ”፡፡
ትክክል ነው፣ የቀይ መስመርን ማስመር የአንዳንዶችን ፍላጎት ስለሚነካ እንድንጠላ ቢያደርገንም፣ የቀይ መስመራችንን በማስመራችን ምክንያት ይልቁንም የበለጠ የሚያከብሩን ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡

አፈ-ታሪክ #4:- “የቀይ መስመርን ማስመር የስሜት ቀውስን ይፈጥርብኛል”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የቀይ መስመርን በማስመር ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት መርህ-ተኮርና የጋራ የሆነ መከባበር የሞላው እንዲሆን ማድረግ በመጀመሪያ ምቹ ስሜት ላይሰጠን ቢችልም ብዙም ሳይቆይ ግን ለሕይወታችን ጤና-ቢስ በሆኑ ግንኙነቶች ላይ ለመሰልጠን እንድንችል ስለሚያበቃን ደስተኞችና የተረጋጋን እንሆናለን፡፡

አፈ-ታሪክ #5:- “የቀይ መስመር ማስመር የሚባለው ሃሳብ ድርቅና ይመስላል”፡፡
እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ የቀይ መስመር ሰው መሆን ማለት የመርህ ሰው በመሆን ከማን ጋር ምን አይነት መስመር ማስመር እንዳለብን ማወቅ ማለት ነው እንጂ ግትር፣ የማይደፈርና በአጥር የታጠረ ሕይወት መኖር ማለት አይደለም፡፡

@yehasab_menged
@yehasab_menged