Get Mystery Box with random crypto!

#ታካችነት_ኃይልህን_አሳልፈህ_የምትሰጠው_ጠላትህ_ነው 'ታካች ሰው። አንበሳ በሜዳ ነው ሲባል በ | የሀሳብ መንገድ

#ታካችነት_ኃይልህን_አሳልፈህ_የምትሰጠው_ጠላትህ_ነው


"ታካች ሰው። አንበሳ በሜዳ ነው ሲባል በመንገዱ ላይ እሞታለሁ ይላል።" (መጽሐፈ ምሳሌ 22:13)

የሆነ ሰው አእምሮህን በመጠቀም ከካንሰር ጭምር መፈወስ እንደምትችል ቢነግርህ፤ ታምነዋለህ ወይስ ትስቅበታለህ?

አእምሮ ሃይል አለው!!!

በጭንቀት፣ በስጋት ውስጥ ከቶ ከሰውነት ተራ እስክትወጣ ድረስ ያከሳሃል…

በተስፋ እና በሃሴትም ሞልቶ ህይወትህን ያበራልሃል።

የምትችላቸው እና የማትችላቸው ነገሮች ያሉት አእምሮህ ውስጥ ብቻ ነው።

በቀጣዮቹ ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ የምትችለውን ሁሉ አድርገህ አስር ሺ ብር ይዘህ ና ብልህ ‘አልችልም - ገንዘቡን ከየት ማምጣት እንዳለብኝ ምንም ሃሳቡ የለኝም’ ትለኛለህ።

ሆኖም በሳንቲሞች የተሞላ ካልሲ በእጄ ይዤ “አስር ሺ ብር ካላመጣህ፣ በዚህ እመታሃለሁ” ብዬ ባስፈራራህ እና መንገድ ለመንገድ ባሯሩጥህ፣ አማራጮችን ማሰብ ትጀምራለህ -

ምናልባትም ትበደራለህ፣

ምናልባትም ከቤትህ እቃ አውጥተህ ትሸጣለህ ወይም ለእርዳታ ትጣራለህ።

ሁሌም ቢሆን አእምሯችን አማራጮች አሉት፤ እኛ እንዳላየ ሆነን ማለፍን እንመርጣለን፣ ሃላፊነቶችን እንሸሻለን እንጂ ተአምረኛው አእምሯችንን በትክክል ከተጠቀምንበት ለእድገት የሚጠቅሙንን ነገሮች ሁሉ ለማቅረብ ዝግጁ ነው።

ከታካችነት ወጥታችሁ አእምሯችሁን ልትጠቀሙበት ዝግጁ ናችሁ?

#ከተአምረኛው_አእምሮህ መጽሐፍ የተቀነጨበ

@yehasab_menged
@yehasab_menged