Get Mystery Box with random crypto!

• በህይወቴ ዘመን ሁሉ ቤተሰቦቼ እንደ ልጅ ቆጥረዉኝ አያዉቁም፡፡ ጠንቋይ ቤት ሄደዉ ያላቸዉን ሀብ | የሀሳብ መንገድ

• በህይወቴ ዘመን ሁሉ ቤተሰቦቼ እንደ ልጅ ቆጥረዉኝ አያዉቁም፡፡ ጠንቋይ ቤት ሄደዉ ያላቸዉን ሀብት 'እኔ ላይ ካፈሰሱ ዉድቀትና ድህነት ቤታችን ዉስጥ እንደሚገባ ነገር ግን ወንድሜ ላይ ካፈሰሱ ቤታችን በበረከት እንደሚሞላ' ዘባረቀላቸዉ፡፡

ይህን ካዘዛቸዉ ቀን ጀምሮ እኔን እንደለማኝ ወንድሜን ደግሞ እንደንጉስ አሳደጉን፡፡ ወንድሜ 'አለ የተባለ ትምህርት ቤት' ሲያስገቡት እኔን ግን የመጨረሻ የድሃ ትምህርት ቤት ወረወሩኝ፡፡ ግን ምን እንደሆነ ልንገርህ ተከተለኝ...

• አስተማሪዎቼ ቤተሰቦቼን ጠርተዉ 'ደደብ ተማሪና ተደብዳቢ እንደሆንኩና ለዚህም እንደመቀጫ የትምህርት ቤቱን ሽንት ቤት ማፅዳት እንዳለብኝ' መወሰናቸዉን ነገሯቸዉ፡፡ ቤተሰቦቼ ደስ አላቸዉ...አዎ የወለዱኝ ቤተሰቦች!!

ስራ ስጀምር ከሽንት ቤት ማፅዳት መሆኑ ለኔ የኋላ ኋላ ለመልካም ሆነልኝ፡፡ ይኸዉ አሁን ከ 20 አመት በኋላ የትልቅ ካምፓኒ ባለቤት ነኝ፡ ይብላኝ ለነሱ! አሁንም ተከተለኝ...

• ከልቤ የማፈቅራት ሴት ‘አንተ እንኳን ለፍቅር ለጉርብትናም ትደብረኛለህ!’ ብላኝ ትታኝ ሄደች፡፡ ግን ከ 10 አመት በኋላ እሷ ካለችበት ኢኮኖሚ 10 እጥፍ 'ሀብታምና የተሳካለት ሰዉ' ሆኜ ከች አልኩ! እሷ ግን እንደማንም ተራ ሆና አሁንም አለች!

እኔን ጥላ በሄደችበት ጊዜ የዛኔዉ 'የልቧ ትርታ' አሁን ከሷ ጋር የለም...አዉላላ ሜዳ ላይ ‘አንቺን ብሎ ፍቅረኛ !’ ብሏት ላጥ! ገና አልጨረስኩም...

• የሆነ የህይወቴ አስቸጋሪ ሰአት ሁሉን ከስሬና ባዶ ሆኜ ስመጣ የተማመንኩባቸዉ ሰዎች በሙሉ ካዱኝ፡፡ ‘አቅሙን የማያቅ!’ ብለዉ ተዘባበቱብኝ!

ቀን ተገለበጠና እኔ ‘አንቱ’ የተባልኩ ሀብታም እነዛ ደግሞ 'ደፋ ቀና የሚሉ' የተለመደዉ አይነት ሆነዉ አሉ፡፡ ይኸዉ ነዉ የኔ ታሪክ!

ሰዎች ሲጎዱኝ፣ ሲጫወቱብኝና እጃቸዉን መቀሰር ሲጀምሩ ያንኑ የተሰበረ ስሜት ተጠቅሜ ወደ ስኬት እለዉጠዋለሁ፡፡ ዉስጤ በቁጭትና በታታሪነት ይሞላል፡፡ ከዛም በህይወቴ የሚገርም ለዉጥ አያለሁ! አንተስ እንዴት እየኖርክ ነዉ??

@yehasab_menged
@yehasab_menged