2022-06-28 21:15:16
#ሀያትና_የአይን_ፍቅር
#ክፍል_አንድ
አብዱ ኤምሬ
ዛሬ ከሀያት ጋር አንድ ላይ የምንተሳሰርበት የብዙ ጊዚያት ምኞቴ እና ጉጉቴ የሆነው የሰርጋችን ቀን ነው አዳራሹ በታዳሚዎች ተጨናንቆል የእኛን መግባት ሲጠብቁ የነበሩ የሰርጉ ታዳሚዎች በሙሉ የእኛን ወደ አዳራሽ መግባት ሲያዩ አዳራሹን በእልልታ እና በፉጨት አደመቁት ልቤ እንደ ዛሬ በሁለት ስሜት መሀል ሆኖ አያውቅም በጣም ከመፍራቴ የተነሳ ፊቴ ላይ የሚታየው ላብ ባልዲ ይሞላል በሌላ በኩል ደግሞ ከሀዩ ጋር በዚህ አይነት መልኩ በመዳሬ እና አብሮ የመኖር ጅማሬያችን መሆኑን ሳስብ የደስታ እንባ ይተናነቀኛል ዲጄው የነስሩ ከድርን <ባረከሏሁ> የሚለውን የሰርግ ነሸዳ ከፍቶ አዳራሹን አድምቆታል።
እናት እና አባቴ ከሀያት ወላጆች ጋር ከፊት ተቀምጠው ይታዩኛል በአይን ከነሱ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጥኩ ቡሀላ ወንድሞቼ እህቶቼ ወደ ተቀመጡበት ቦታ ዞርኩ እነሱ ላይ የሚታየው የደስታ ስሜት ሁሉ ነፍስን ሀሴት ይሞላል። የሚሆነው ነገር ሁሉ እውን አልመስል አለኝ ከሀዩ ጋር ስለሚኖረኝ የወደፊት ጣፋጭ ህይወት እና ልጆች እያሰብኩ... ሀዩን በእጆቼ ይዤ የሙሽራዎቹ ወንበር ላይ ለመቀመጣት ደረጃዎቹን በመውጣት ላይ ሳለሁ ድንገት... የስልኬ አላርም ጠራ.. በድንጋጤ ከመኝታዬ ስነሳ ለካ ያየሁት ነገር ሁሉ የእውነት ሳይሆን በህልሜ ነበር ፊቴ በላብ ተዘፍቋል... ስልኬን አንስቼ ስመለከት የሱቢህ(የንጋት) ሰላት(ስግደት) ሰአት ላይ እንዲቀሰቅሰኝ ብዬ የሞለሁት አላርም ነበር... በህልሜ ያየሁት ነገር በጣም አስደስቶኛል እውን ሆኗ ባየው ብዬ ተመኘሁ....
የሱብሂን ሰላት ከሰገድኩ ቡሀላ በህልም አለም ያየሁት ሁሉ በእውኑ አለም እንዲሆን አብዝቼ አላህን ከተማፀንኩ ከለመንኩ ቡሀላ... ከሱቢህ ቡሀላ የመተኛት ልምዱ ስለሌለኝ ዛሬ የቀኑ መጀመሪያ ስለሆነ ወደ ት/ቤት መሄጃ ሰአቴ እስኪደርስ የተከበረውን ቁርዐን: ወይም ሌሎች መፅሀፍትን አነባለሁ...
ሰኞ እና ሀሙስ ፆመኛ ስለሆንኩ ቁርስ ሳልበላ ነው ምወጣው ዩኒፎርሜን ከለበስኩ እና ቦርሳዬን ከያዝኩ ቡሀላ ከቤት ወጣሁ ሰፈራችን ላይ ከእኔ ጋር አንድ ት/ቤት የሚማር ስለሌለ ብቻዬን ነው የሚሄደው ደግነቱ ት/ቤቱም ከቤታችን ብዙ ስለ ማይርቅ ብቻዬን መሄዱ አይደብረኝም.. የት/ቤቱ ቅጥር ግቢ አከባቢ ስደርስ ሰሚር የሚል ድምፅ ሰማሁ ማንነቱን ለማረጋገጥ ስዞር...
ሰሚር እባላለሁ የምኖረው አዲስ አበባ ከተማ ነው ለቤተሰቤ አራተኛ ልጅ ነኝ ሶስቱ ወንድሞቼ ሙሀመድ:ነቢል:አህመድ ሁለቱ እህቶቼ ደግሞ ኑራ እና ሰብሪና ናቸው። ሙሀመድ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆን ተከታዩ ነቢል ቀጥላ ኑራ ከዛ እኔ ቀጥሎ አህመድ የመጨረሻዋ ደግሞ ሰብሪና ነች። አባቴ ነስሩ ከማል እናቴ ደግሞ ሰሚራ ሀሰን ይባላሉ። አጠቃላይ ቤተሰቦቼ ስምንት ነን ይህም በብዙ ፍቅርና እንክብካቤ እንዳድግ ረድቷኛል እናቴ ከሁሉም በላይ ለኔ ፍቅር አላት ሰሚር የሚለውንም ስም ያወጣችልኝ እሷ ነች። እናቴና አባቴ በመሀል ለሶስት አመት ያህል ተለያይተው ስለነበር እናቴ ወላጆቾ ጋር እኛ ሁላችንም ደግሞ ከአባታችን ጋር ነበር የምንኖረው አሁን ላይ ግን አባት እና እናቴ ታርቀው አንድ ላይ መኖር ከጀመርን አምስት አመት ሆኗል...
ሰሚር የሚል ድምፅ ሰምቼ ማንነቱን ለማረጋገጥ ስዞር አቡበከር ነበር። አቡኪ የልጅነት ጓደኛዬ እና አብሮ አደጌ ነው ብዙ ሰዎች ከመመሳሰላችን የተነሳ ከወንድምም አልፎ መንታ ናችሁ የሚል ጥያቄ ይሰነዝራሉ። አሁን ላይ ግን ሰፈራችንን ስለቀየርን ከት/ቤት እና ከመማሪያ ክፍል ውስጥ ውስጥ ሰፈርም ሆነ ሌላ ቦታ የመገናኘት እድሉ የለንም....
ከአቡኪ ጋር ቅዳሜና እሁድ ስላልተገናኝን በመነፋፈቅ ስሜት በደንብ ሰላም ከተባባልን ቡሀላ ወደ ት/ቤት ገባን...
ይቀጥላል.....
@YEFKIR_LEZA
@YEFKIR_LEZA
593 viewsAbdu Emre, edited 18:15