Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር አለም

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_alem — የፍቅር አለም
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefiker_alem — የፍቅር አለም
የሰርጥ አድራሻ: @yefiker_alem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.56K
የሰርጥ መግለጫ

❤ፍቅር_አለም❤
የፍቅር አለም መሬት አደለችም
የፍቅር አለም በፍቅር ውስጥ
የምትፈጠር ሌላ አለም ነች
ኑ በጋራ የፍቅር አለም እንገንባ

#ጾታ_አይመርጥም
👉cross ፈላጊዎች አናግሩኝ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@tru_fact22
@abrolovem
@yefiker_alem

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-24 21:31:37 ማነው ከሃዲ..?

ሁለት ፍቅረኛሞች እራሳቸውን ለማጦፋት ፈልገው፣ ከብዙ አስከፊ ጊዜያቶች በኋላ ከተራራ ጫፍ ላይ ዘለው ራሳቸውን ለማጥፋት ይወስናሉ። የተራራው ጫፍ ላይ ከደረሱ በኋላ ከአንድ እስከ ሶስት ቆጥረው ለመዝለል ይስማማሉ።

እናም ወንዱ ይዘላል፣ ግን እሷ አልዘለለችም። ቆማ ለ7 ሰከንድ ካየችው በኋላ ፓራሹት አውጥቶ እሱም ነፍሱን ያተርፋል።

አሁን ማን ነው ከሃዲው?

#share @yefiker_alem
319 viewsRoyal M, 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 20:38:19 እዴት ነው ትረካየ
256 viewsDay dremer, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 16:52:26 ሳታነሺው ሲቀር...

ፈገግታ ሳቅሽን ለመስማት ወድጄ
ከአንደበቴ ላይ የያዝኩት ሸምድጄ
ቀልድ አዘጋጅቼ ሳቅሽን ልገራ
ሳታነሺወሸ ሲቀር ስልኩ እየጠራ
ለራሴ ደግሜው ራሴው ሳኩበት
ብቻዬን ስስቅም እብድ ተባልኩበት
(ይሆን እንዴ እብደት?)

ድምፅሽን ለመስማት ላወራሽ ጓጉቼ
ዝርዝር ለቃቅሜ ካርዱንም ሞልቼ
ሳተነሺው ሲቀር ለብዙ አዋልኩት
ከጓደኞቼ ጋር እልፍ አወጋሁበት
ከዛም አልፎ ተርፎ ለሌላ ሰው ላኩኝ
ምስጋና፣ ምርቃት በብዙ አተረፍኩኝ!

በድምፅ ሳንረበሽ በምንም ሳንገታ
ላንቺ ለመደወል ከመረጥኩት ቦታ
ሳታነሺው ሲቀር ስልክሽ ተዘግቶ
አስተውል ጀመርኩ ያልታየኝን ከቶ
ፀጥታው ቢመቸኝ ግጥም ፃፍኩበት
የጥበብን ባህር በብዕር ቀዘፍኩበት!

ሳታነሺው ሲቀር ስልኩ ተከርችሞ
ንዴት ሊያበግነኝ ፊቴ ሳለ ቆሞ
ትርፌን አሰላሁት ካገኘሁት ጥቅም
በኢምንት ጊዜ ውስጥ ያለኝን አቅም

እናምልሽ ውዴ...

ሳታነሺው ሲቀር ልቤ ይህን አመነ
አንዳንዴም መገፋት ለራስ እነደሆነ።

#share @yefiker_alem
299 viewsRoyal M, 13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 16:22:24 #ስጀምር
ማፍቀር ምንማለት ነው እያልኩ የነበረ
በኔ ሲደርስብኝ ገባኝ እያደረ

ለካ ማፍቀር ማለት ስለሰው መኖር ነው
ከራስ ላይ ቀንሶ ለሰው መጨነቅ ነው

አይመስለኝም ነበር ተችሎ የሚኖር
የራስን ፍላጎት የትም ሚወረወር

ሳፈቅር ግን ገባኝ ላንቺ ብቻ ሳስብ
ማፍቀር እንደሚልቅ ከሰው አስተሳሰብ

አዎ ዛሬ አወኩኝ የፍቅርን ትርጉም
ለካ የተፈቃሪን ህመም ነው አብሮ መታመም

አሁን ግን ኮራሁኝ አፍቃሪ ስለሆንኩ
ለራሴ ብቻ ሳይሆን ለሰውም ስለኖርኩነው

#Hani

SHARE @yefiker_alem
SHARE @yefiker_alem
297 viewsRoyal M, 13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 20:29:48 የፍቅር አለም pinned a voice message
17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 18:29:15 ብሎ ቢቀርብን ይሻል ነበር።
የኔዎቹ ለልብስህ መግዣ ፣ ስጦታ ይሁንህ ምናምን እያሉ
ነዉ የሚልኩት። እኔ ሲጀመር ማለቃቀስ አይመቸኝም።
ጠብረር ስልባቸዉ ወደነሱ ለመሳብ ሲሉ የሆነ ነገር ይልካሉ።
አለቀ!
.
እኔ መኝታ ክፍል ተቀምጬ ፌስቡክ ላይ እጀናጀናለሁ።
እነእማዬ ደግሞ ሳሎን ቡናቸዉን እየጠጡ ይጨዋወታሉ።
መጀናጀን ከጀመርኩ ትንሽ እንደቆየሁ ሁሉም በአንዴ ፀጥ
አሉ። ጫጫታቸዉ ጠፋ። እማዬ ስታቃስት ሰማሁ። አምሪያ
"ሀቢብ!" ብላ ጮኸች። ከአልጋዉ ላይ ተስፈንጥሬ ተነስቼ
ወደ ሳሎን ተንደረደርኩ። እማዬ ፍራሹ ላይ ተዘርራ በእጆቿ
ሆዷን ጨምድዳ ይዛ እግሮቿን እያፋተገች ታቃስታለች።
ወይዘሮ ለይላ ተደናግጠዉ አንገቷን ደግፈዉ ይዘዉ ያዩኛል።
የማደርገዉን ነገር ነዉ ያጣሁት። አጠገቧ ተቀምጬ
አያታለሁ። ወይዘሮ ለይላ "አምሪ አባትሽ ጋር ደዉይለት!"
አሉ። አምሪያ ወዲያዉ አባቷ ጋር ደወለች። አላማዉ መኪና
ይዞ እንዲመጣ እና ሀኪም ቤት እንድንወስዳት ነዉ። ድንዝዝ
ብያለሁ! እማዬ እንደዚህ ስትታመም አይቼ አላዉቅም።
አንዳንዴ ያማት ነበር። ታይታዉ ጉበትሽ ላይ ነዉ ችግሩ
ብለዋት ነበር። ከዛ በኋላ ህክምናዉን የወሰደችም
አይመስለኝም። ግን አልፎ አልፎ ቢያማትም እንዲህ
እንደዛሬዉ አሰቃይቷት አያዉቅም። ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ነዉ
ቅይር ያለዉ።
ከአምስት ደቂቃ በኋላ የአምሪያ አባት ሀጂ ራህመቶ ደረሱ።
እማዬን መኪናዉ ዉስጥ አስገብተን ወደ ሆስፒታል ሄድን።
ለሚኪ የተፈጠረዉን ነገር ደዉዬ ነገርኩት። ሰፈራችን ያለ
አንድ የግል ሆስፒታል ነበር የሄድነዉ። ሀኪሞቹ እማዬን
አስገብተዉ ማከም ጀመሩ። እኛ ዉጪ ሆነን እንጠብቃለን።
ጭንቅ ብሎኛል። ሚኪ ሲከንፍ ደረሰ፤ የአምሪያ አባት ሀጂ
ራህመቶ አብረዉኝ አሉ። የሆነ የማላስበዉ ስሜት ዉርር
አደረገኝ። ተጨንቄ አላዉቅም! በጣም ጨነቀኝ።
.
ይቀጥላል...
እንደተለመደዉ #like & #share


የማይፋቅ ስህተት
ክፍል አምስት
(ፉአድ ሙና)
.
እማዬን ያስገባንበት የግል ሆስፒታል ዶክተሮች ይሯሯጣሉ።
ዶክተሯ አስጠርታ አየችኝና "ምኗ ነህ?" አለችኝ። ይሀ ስንት
ሴት እንደ ቅቤ የሚያቀልጠዉ ምላሴ እየከዳኝ "ልጇ!"
አልኳት። ፈገግ አለችና "ከቤተሰብ አባላችሁ ዉስጥ ካንተ
ከፍ ያለ ሰዉ አለ?" አለችኝ።
"ቤተሰብ እንኳ የለም ጎረቤት ግን አሉ።" አልኳት።
የተቀመጠችበትን ወንበር ወደ ጠረዼዛዋ እያስጠጋች "ስምህ
ማነዉ?" አለችኝ።
"ሀቢብ ከማል" አልኳት።
ዶክተሯ በረዥሙ ከተነፈሰች በኋላ እንግሊዘኛ የቀላቀለ
የረዥም ሰዓት ማብራሪያ መስጠት ጀመረች። እኔ ሀሳቤ
ብትንትን ብሏል። የምትለዉን ሁላ ማዳመጥ አልቻልኩም።
መጨረሻ ላይ "...ስለዚህ ሀቢቤ የእናትህ ጉበት አሁን
ባልኩህ መልኩ ለረዥም ጊዜ የቆየ ጉዳት ስላስተናገደ አሁን
ሙሉ ለሙሉ ፌል ወደማድረጉ ተቃርቧል። በቀዶ ጥገና
የቻልነዉን ለማድረግ እንሞክራለን። ሌላ ሰዉ ከሌለ አንተ
ትፈርምልናለህ።" አለችኝ። የሆነ ድንዝዝ ስል ይታወቀኛል።
ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ ወደ ዉጪ ወጣሁ። ኮሪደሩ ላይ
ሀጂ ራህመቶና ሚኪ ተቀምጠዋል። ከዶክተሯ ቢሮ ስወጣ
ሁለቱም ከመቀመጫቸዉ ብድግ ብለዉ ተጠጉኝ።
ሀጂ ራህመቶ "ምን አሉ?" አሉኝ። ዝም ብዬ መተላለፊያዉ
ላይ ያለዉ ወንበር ላይ ዘፍ አልኩኝ።
.
ሀጂ ራህመቶ ፈጠን ብለዉ እየተራመዱ ወደ ዶክተሯ ቢሮ
ገቡ። ሚኪ ከአጠገቤ እየተቀመጠ "ሀቢቤ ጠንከር በል እንጂ
ያንተ መፍዘዝ ችግር ሊፈጥር ይችላል።" አለኝ። እንባዬን
ለመቆጣጠር እየሞከርኩ "እንደመምከር ቀላል ቢሆን ጥሩ
ነበር።" አልኩት።
ሀጂ ራህመቶ ከዶክተሯ ጋር አንድ ላይ ሆነዉ ከቢሮ ወጡ።
ዶክተሯ እጇ ላይ ወረቀት ይዛለች። ከአጠገቤ ተቀመጠችና
"ዶ/ር ቀመሪያ እባላለሁ።" አለችኝ። ስገምት ሀጂ ራህመቶ
ብቸኛ መሆኔን ምናምን ነግረዋት መሆን አለበት።
ወረቀቱን እያስጠጋችልኝ "እኛ እናትህን ለማዳን የምንችለዉን
እናደርጋለን። አንተ ግን ፍቃድህን ልትሰጠን ይገባል።"
አለችኝ።
ሀጂ ራህመቶ "ሀቢቤ መቆየታችን ችግር ይፈጥራል። ቶሎ
ወረቀቱ ላይ ፈርምላት።" አሉኝ። እጄ እየተንቀጠቀጠ ወረቀቱ
ላይ ፈረምኩ። ወዲያዉ ሀጂ እና ዶክተሯ እየተጣደፉ ወደ
ፎቅ ወጡ። እኔና ሚኪ ተክዘን ተቀምጠናል። ክፍያዉን ሁሉ
የከፈሉት ሀጂ ራህመቶ ናቸዉ።
ሚኪ ስልኩ በተደጋጋሚ ይጠራል። ዞር ብዬ ሳየዉ በአንድ
እጁ የኔን ስልክ በሌላኛዉ እጁ የራሱን ይዟል። መች ስልኬን
እንደሰጠሁት ፈጣሪ ነዉ የሚያዉቀዉ። ትንሽ ቆይቶ የኔም
ስልክ ሲጠራ ሰማሁ። ሚኪ ወዲያዉ ዘጋዉ። ያዉ ፌቨን ናት
የምትሆነዉ። ምሽቱን ቻት ላይ ስጠፋ ጨንቋት መሆን
አለበት። አንገቴን እንዳቀረቀርኩ "ሚኪ ስንት ሰዓት ሆነ?"
አልኩት። "ዘጠኝ ከሩብ" አለኝ። የፈጣሪ ያለህ ፌቪ
እስከአሁን አልተኛችም።
"ከዚህ በኋላ ከደወለች አንሳና አናግራት።" አልኩት። ብዙም
ሳይቆይ ደወለች ሚኪ ከመቀመጫዉ ተነስቶ ወደ ታች
ደረጃዉን እየወረደ ማናገር ጀመረ።
.
ለሊቱን ይሀ የፈረደበት ወንበር ላይ እንደተቀመጥኩ
አነጋሁት። ሀጂ ራህመቶ ለሊቱን ሙሉ ሲሯሯጡ ቆዩ። እኔ
እንደሆነ ከመንቀሳቀሴ በቀር በድን ሆኛለሁ ብል ይቀላል።
ሚኪ ባይኖር ሀጂ በጣም የሚቸገሩ ይመስለኛል። ጎህ
እንደመቅደድ ሲል ሚኪ እና ሀጂ ራህመቶ ከላይኛዉ ፎቅ
ወረዱ። ሚኪ ከአጠገቤ እየተቀመጠ "ቀዶ ጥገናዉን
ጨርሰዋል።" አለኝ። ልቤ ትንሽ ሲረጋጋ ይሰማኛል። "እና
እማዬ ደህና ናት?" አልኩ። በስንት መከራ ከአፌ የወጣች ቃል
ነበረች። "ገና አልነቁም ግን ደህና ናቸዉ።" አለኝ።
ሀጂ ራህመቶ ለሊቱን ሙሉ ሲንቀጠቀጥ ያደረዉን
ወገባቸዉን ለማሳረፍ ቀስ ብለዉ ወንበሩ ላይ ተቀመጡ።
ሀጂ ፈገግ ካሉ በኋላ "ሀቢቤ አንተ ደክሞሀል አረፍ በል እኛ
እንቆያለን።" አሉኝ። የሚገርሙ ሰዉ ናቸዉ። ይሄን ያህል
ለሰዉ መኖር ማን ይሆን ያስተማራቸዉ? ምንም ቢደክመኝም
እናቴ ሆስፒታል ተኝታ እኔ ወደ ቤት መሄድ አልፈለግኩም።
ባይሆን እሳቸዉ አረፍ እንዲሉ ጠየቅኳቸዉ ግን አሻፈረኝ አሉ።
ወዲያዉ ዶክተሯ ቦርሳዋን ይዛ እየወጣች "እዚህ
ተቀምጣችሁ ምንም አትሰሩም። ከነቁ ነርሶቹ ስላሉ ችግር
የለም። እስከ አራት ሰዓት አረፍ ብላችሁ ተመለሱ።" አለችን።
ወዲያዉ ሀጂ ራህመቶ ሰዓታቸዉን ተመለከቱና "ዉይ አስራ
ሁለት ተኩል ሆኗል። እስከዛ አፋችን ላይ ምግብ ጣል አድርገን
እንመለስ።" አሉ። በሀጂ መኪና ሶስታችንም ወደነ ሀጂ ቤት
ሄድን።
.
እነሀጂ ቤት ስንደርስ ሁሉም ከእንቅልፋቸዉ ተነስተዋል። ቤቱ
ተሰነዳድቷል። በልቤ "ለሊቱን አይተኙም እንዴ?" አልኩ። ማታ
አምሪያና ወ/ሮ ለይላ አብረዉን ሊመጡ ሲሉ ሀጂ እኛ
እንበቃለን ብለዉ እንደመለሷቸዉ ትዝ አለኝ። ሀጂ መንገድ
ላይ ሆነን ደዉለዉ ስለነበር ይመስለኛል ገና እንደገባን
አምሪያ መጥታ ምንጣፉ ላይ የሚያምር ላስቲክ አነጠፈች።
ሚኪ በአይኑ "ምንድነዉ?" ብሎ ጠየቀኝ። ያዉ ምግብ
ሲቀርብበት ይገባዋል ብዬ ዝም አልኩት። ወዲያዉ አምሪያና
ወ/ሮ ለይላ ምግቡን አቀራረቡና መብላት ጀመርን። ወ/ሮ
ለይላ ስለ እናቴ ሁኔታ ጠየቁ። ሀጂ ሁሉንም በዝርዝር
አስረዷቸዉ። የአምሪያ ፊት ላይ የሀዘን ድባብ ይታያል።
ምግቡን በልተን እንደጨረስን እኔና ሚኪ እኛ ቤት ገብተን
አረፍ አልን። ወገብ ለማሳረፍ ያክል ነዉ እንጂ በወጉም
እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ትንሽ ካንገላታኝ በኋላ ግን
እንቅልፍ ይዞኝ እብስ አለ።
.
ከእንቅልፌ ስነቃ ሚኪያስ አጠገቤ የለም። ከአጠገቤ ስልኬ
ተቀምጧል። አነሳሁና ሰዓቱን ተመለከትኩት። ስድስት ሰዓት
ሆኗል። ደንግጬ ከአልጋዉ ላይ ተስፈንጥሬ ተ
382 viewsDay dremer, 15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 17:37:56 ሸጋው በአንተ ላይ
ይደረባል ወይ

#share @yefiker_alem
389 viewsDay dremer, 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 17:01:57 የፍቅር አለም pinned Deleted message
14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 14:40:17 የፍቅር አለም

አንቺ ከሄድሽ በኃላ

"መድሀኒትህ ነን" ያሉ ፤
ወደ 'ኔ ይመጣሉ መፈወሱን ትተው
በቁስሉ ላይ ፤ እንጨት ይሰዳሉ

አንቺ ከሄድሽ በኃላ

"ፀሀይህ ነን" ያሉ ፤ ወደ 'ኔ ይመጣሉ
ብርሃን ሳይሰጡ
ከፅልመት አኑረው፤ ጥለው ይሄዳሉ

ብቻ
ብቻ
አንቺ ከሄድሽ በኃላ

ነገር አለሙ እንደ ጥላ
ለኔ እየሸሸ የሚረግጠው ሌላ


┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄



   አሁኑኑ ሼር አድርጉ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌

#share @yefiker_alem
375 viewsRoyal M, 11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ