Get Mystery Box with random crypto!

ሳያልፍ በፊት ታገል፤ ካለፈ በኋላ አትጨነቅ! *** በአንድ ወቅት ቻርሊ ቻፕሊን በመድረክ ላይ አን | የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ሳያልፍ በፊት ታገል፤ ካለፈ በኋላ አትጨነቅ!
***
በአንድ ወቅት ቻርሊ ቻፕሊን በመድረክ ላይ አንድን ቀልድ ተናገረ።ሁሉም ሳቁ፤ እራሱን ቀልድ ለሁለተኛ ጊዜ ደገመው የተወሰኑት ሳቁ ፤ ለሶስተኛ ጊዜ ራሱን ቀልድ ደገመው የዚህን ጊዜ ግን አንድም የሳቀ ሰው አልነበረም።

የዚህን ጊዜ አንድ ድንቅ ንግግር ተናገረ:-
"ለተመሳሳይ ቀልድ ደጋግመህ አትስቅም! ታዲያ ተመሳሳይ ለሆነና ለሚያስጨንቅህ ነገር ለምን ደጋግመህ ታለቅሳለህ?"
ያለፈን ነገር ደጋግመህ እያነሳህ ማልቀስህ እምባህን ማባከን መቆዘምህም የፊትህን ውበት ማርገፍ ነው።
ሳያልፍ በፊህ ታገል ካለፈ በኃላ ግን አትጨነቅ!

“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
— ፊልጵስዩስ 4፥6

አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁ ሼር አድርጉት!

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch