Get Mystery Box with random crypto!

ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበ-ወለድ} @yebirihan_lijoch '''''''''''' | የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ዲና{DINA}
{ተከታታይ ልበ-ወለድ}

@yebirihan_lijoch

""""""""""""""""ክፍል """""""""""""""""

.....ልንቀላቀል ነው ዛሬ ማክሰኞ ነው እዩ የሚሄድበት ቀን ደሞ አዲስ አበባ ሄደሽ እንዳትደናበሪ እያለ ማቲ እያበሸቀው ነው ዝኑ በጣም ከፍቷታል እማስ ከአባታችን ጋር መኖር ጀመረች እንዳያስታውቅባት የውሸት ፈገግ ትላለች ብሩኬም አይከፋውም ሪቾ ስላለች
ዝንዬ ብሩኬ ማቲ እና እኔ አድርሰነው ማቲ ና ብሩኬ ተመለሱ ።

@yebirihan_lijoch

ምክኒያቱም ማቲ ሀሙስ አርባ ምንጭ ይሄዳል አባቢና ብሩኬ ስለሚያደርሱት ሁለቱ ተመለሱ እኔ ና ዝንዬ የዝኑ እህት ጋር አረፍን እሮብና ሐሙስና አርብን እዛ ቆየን የእዩ አክስት ልጅ አዲስ አበባን በጥቂቱም ቢሆን ሲያስጎበኘን ለሶስት ጥሩ ጊዜያት አሳለፍን እዩም እንደከፋው እርግጠኛ ነኝ ግን አማራጭ ስላልነበረን መለያየቱ ግድ ነው ቅዳሜን እየተረበሽኩ ከዝኑ ጋር ተመለስን ስሄድ አባቢ የለም ነገ ይመለሳሉ ማቲን ሊያደርሱት ከብሩኬ ጋር አርባ ምንጭ ሄደዋል ማቲም እዩም ገና ከአሁኑ እየናፈቁኝ ነው እሁድ እቃዎቼን ሳዘገጃጅ ዋልኩ አባቢና ብሩኬ ከምሽቱ 3:ሰአት መጡ ብሩኬን አድርሶት ተመልሶ መጣ ለማቲ ደውዬለት ረጅም ሰአት አወራን እሱም ሲመክረኝ እኔም ስመክረው ቆየን ቻው ተባብለን እንደ ዘጋሁት እዩ ደወለልኝ አንቺ ከአሁኑ ካድሽኝ ይሄን ሁሉ ሰአት መስመር ተይዟል የሚለኝ ማንን ብታወሪ ነው አለኝ ምን ባክህ አንዱ ከመቀሌ ደውሎ አትመጪም ወይ አላለም አልኩት ነው ማነኝ አለ አለኝ ባክህ እኔም አላውቀውም እሱ ነው ሚያውቀኝ አልኩት ነው በርቱ አለኝ አቤት እርርርር ድብን አደረኩሀ ባክህ ማቲ ነው አልኩት ድሮስ ከኔና ከማቲ ወጪ ሚደውልልሽ ሰውስ አለ ጉረኛ አለኝ ነው እሱን አብረን እናየዋእናየዋለን አልኩት እንዲሁ ስንዛዛግ 7:ሰአት ሆነ እንዴ ዲኑ ሰአቱን አየሽው ነገ መንገደኛ እኮ ነሽ በቃ ደህና እደሪልኝ ቻው አለኝ እውነትም ሳናውቀው ሰአት ሄዷል በቃ ቻው ብዬው ተኛው

@yebirihan_lijoch

በጠዋት ተነስተን እቃዎቼን ጫንን ዝኑ ና መአዚም በጠዋት መጥተዋል ቤቢዬም እማ የሞትኩ ይመስል ታለቅሳለች እያጎረሰችኝ ቁርስ በላሁ ና እማንም ዝኑንም መአዚንም ቤቢንም እቤት ውስጥ ያለችውን አመለ ን ዘበኛውንም ተሰናብቼ 2:ሰአት ሲል ጉዞ ጀመርን በነገራችን ላይ የድሮው ቤታችን ሰፈር ውስጥ ዋሮ ወጥራ የምትኖር 2ልጅ ያላት ሴት እንድትኖርበት ሱቁንም እንድትተዳደርበት ተሰጥቶአታል ለእማ ደግሞ ሱፐር ማርኬት ሊከፍትላት ተስማምተዋል አባቢ ብዙ ነገሮችን እየነገረኝ ከብዙ ድካም በኋላ ደረስን የአባቢ ሹፌር በፍጥነት ነበር የሚነዳው እንግዲ የማይቀረውን የጊቢ ህይወት ተቀላቀልኩ አባቢ ና ሹፌሩ እስከ እሮብ ተቀምጠው ሐሙስ ተመለሱ ......

..............ይቀጥላል...............

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch