Get Mystery Box with random crypto!

ዲና{DINA} {ተከታታይ ልበወለድ} @yebirihan_lijoch ========ክፍል(1 | የብርሃን ☀️☀️ ልጆች

ዲና{DINA}
{ተከታታይ ልበወለድ}
@yebirihan_lijoch

========ክፍል(14)=========

.....ይሄ ነገር ግራ እያጋባን ነው እንዲህ እንዲህ እያለ ወራት ተቆጠሩ ሰውዬው ስሙ ፈቀደ ነው ። ግን ሁሌ እያገኘን መልካም ነገር ከማድረግ ውጪ ለምን እንደሚፈልገን አይነግረንም አሁንማ ለምደነው ሳናገኘው ከቆየ ይናፍቀን ጀምሯል እዮባም ማቲም የሚነግሩኝ ነገር እንዳለ ነግረውኝ ነበር ስላልዘነጋሁት ለየብቻ ሳገኛቸው መጨቅጨቄን ተያያዝኩት ወደ ቤት ልንሄድ እዩና እኔ ማቲን ልንጠብቀው ዛፍ ስር ቁጭ አለን አንተ ደነዝ ግን እኔ ብጓጓ ምን ትጠቀማለህ በናትህ ዛሬ እንኳን ንገረኝ አልኩት ተይ ዲኑ እስቲ የፈቀደን ጣጣ እንጨርስና ብነግርሽ ይሻለኛል በዚህ መሀል ማቲ መጣ ቦርሳችንን አንስተን ከጊቢ ስንወጣ መኪናዋ ቆማለች አሁንማ ለምደነው የለ ገባንና እቤት ሄድን የሚገርመው ብሩክ እየተከተለን ነበር ዘበኛውና ጠባቂዎቹ አትገባም ሲሉት ወንድማችን ነው ብለናቸው እየተከተለን መጣ ገባንና ልጆቼ መጣቹ ብሎ አቅፎ ሰላም ሲለን ብሩክ ደርቆ ቀረ መንቀጥቀጥ ጀመረ ፈቀደም ቀና ብሎ ሲያየው ደነገጠ ምንድነው ትተዋወቃላችሁ አለ እዩ እኔና ማቲም ግራ ገባን አዎን ይሄን ነው መልካም ምትሉት ማቲ እናታችን ስትሞት ጥሎን የሄደው አባትህ መሆኑ ነው አለ እያለቀሰ ምን የማቲ አባት ነህ ስለው አዎን ልጄ የሱ ብቻ ሳይሆን የአንቺም አባት ነኝ እያለ ማልቀስ ጀመረ ምን እኮ ማቲ የኔ ወንድም ነው ምንድነው ምታወራው አልኩት እየጮኹኩ ፍሬ ማለትም ወጣቷ ሴት ስላችሁ የነበረችው አዎን እኔም አክስታቹ ነኝ ኸረ ድራማ ምንድነው ምትሉት አለ ማቲ ብሩክም ሚሰማውን ማመን እያቃተው እንዴት ነው ለሷ አባት የሆንከው ሲለው


@yebirihan_lijoch


አዎን የሁለቱም እናት አያውቁም ነበር ልክ የዲኑ እናት የሁለት ወር እርጉዝ እያለች የእናንተ እናት ባሏ ከሞተ በኋላ ሲቸግራት እኔ ጋር እየመጣች ገንዘብ ትጠይቀኝ ነበር በጣም ስለምታምር የዲኑ እናት በሌለችበት በገዛ ቤቴ ተሳሳትኩ ከአንድ ወር በኋላ አረገዝኩ አለችኝ በራሴ ስተት ስለነበር እየሄድኩ እጠይቃት ነበር የዛኔ ብሩክ ገና 14 አመቱ ስለነበር እኔ ነበርኩ ምንከባከባት ውብዬ ይህን ስትሰማ ጥላኝ ጠፋች እንባውን እንዴት ልግለፀው ሁላችንም እንደ ፊልም ተመስጠን እየሰማን ነው ብዙ ጊዜ አፈላለኳት ከ9ወር በኋላ በኔው ስተት ያረገዘችው እናታችሁ ማቲን ስትወልድ ሞተች ይህንን መቀበል ስላቃተኝ አሜሪካ ወዳሉት ዘመዶቼ አቀናሁ ከ3 አመት በኋላ ስመጣ ብሩክም ያለ እድሜው ስራ እየሰራ ነበር
ያላችሁበትን ሁኔታ ስሰማ ዲኑ አያቷ ጋር እንደሆነች ማቲም እንዳደገ በሩቁ አይቼው ተመለስኩ ወዲያው ፍሬ ብሩክ አስታወስክ የሆነ ጊዜ 5ሺህ ብር ሰጥቼህ የተሰወርኩብህን አለችው አንቺ ነበርሽ አዎን ፖስታ ሰጠሽኝ ከፍቼ እስካየው ተሰወርሽ አላት አዎን ውብዬ ጋርም ሱቋ ሄጄ እንዲሁ ነው ያረኩት ።

@yebirihan_lijoch
እና ማቲ ወንድሜ ነው እንባ እያነቀኝ ሁለታችንም ተያየን ማቲም አይኑ እንባ አቀረረ ይሄን ሁሉ ጊዜ የት ነበርክ የአንተን አባትነት ሳይሆን እሷም እናቷን እና አያቷን እኔም ወንድሜን ነው ምናውቀው ከዚህ በኋላ ልታገኘን እንዳትሞክር ብሎት ወጣ ማቲ ብሩክም ተከተለው እዩ ወይ 8ተኛው ሺ አምላኬ ፊልም ነው በለኝ እያለ ወጣ እኔም ተከተልኳቸው ፍሬ እጄን ይዛ ዲኑ ተረጋጊ አለችኝ ተይኝ ብያት ሄድኩ ውስጤ ተላወሰ እናቴ አሳዘነችኝ በ2 አመትሽ ጠፋ ያለችኝ በተረገዝኩ በ2ወሩ የተለያዩትን ነው ጭንቅላቴ ዞረ ማቲ የሚያለቅሰው እንባ እሮጬ ተጠመጠምኩበት ባሰበት አረጋግቼው የኔ ወንድም ተረጋጋ አልኩት ......
......... ይቀጥላል.......


@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch