Get Mystery Box with random crypto!

የዘመኔ በረከቶች (አልታየህ ኪዳኔ) * አዳምን አነብበዋለሁ። ለተውህቦው ፣ ለቋንቋው ጉልበት | የብርሃን መንገድ

የዘመኔ በረከቶች

(አልታየህ ኪዳኔ)

* አዳምን አነብበዋለሁ። ለተውህቦው ፣ ለቋንቋው ጉልበትና ርቅቀት ፣ ረቂቅ ስሜቶችን የሚገልፅበት መንገድ ይገርመኛል። ኢትዮጰያዊ ፍልስፍናን ከእንጀራ እየቀዳ ያለው አዳም የተለየ ከያኒ ነው።

* ሌሊሳን አነብበዋለሁ። ለሃሳቡ ጥልቀት። ነገሮችን የሚያይበት መንገድ ግሩም ነው። አጫጭር ታሪኮቹና ፍልስፍናዊ ወጎቹ የሚጠገቡ አይደሉም። ጥበብ ላይ ያለው መብሰልሰል ደግሞ የተለየ ነው።

* አለማየሁ ገላጋይን አነብበዋለሁ። ለማህበረሰብ ያለውን ተቆርቋሪነት ይገርመኛል። ቁጣው ያስቆጣኛል። ቁርፊያው ያስኮርፈኛል። አንደበቱ ይበረታብኛል። ድንቅ ብዕረኛና አንደበተርቱዕ ነው።

* በእውቀቱን አነብበዋለሁ። ለታሪክ አዋቂነቱ። ማህበራዊ ሂሶችን በቀልድ አዋዝቶ የሚያቀርብበት መንገድ ይማርከኛል። ግጥሞቹን ሳነብብ ደግሞ ቃላትን በማዘዝ አቅሙ እደነቃለሁ።

* እንዳለንጌታን አነብበዋለሁ። አጫጭር ታሪኮች መፃፍ ላይ የተለየ አቅምና ጉልበት ያለው ይመስለኛል። ያነበብኳቸው የእንዳለ አጫጭር ታሪኮች ምርጥ አጫጭር ታሪኮች ተርታ የማሰልፈው ነው።

* ዘነበን አነብበዋለሁ። Disciplined የሆነ የስነፅሁፍ ማንነቱ ይማርከኛል። የሚፅፋቸው መፅሀፎች የብዙ ጥረትና ድካም ውጤቶች ናቸው። ስነፅሁፋዊ ኮስታራነቱን አደንቃለሁ።

@yebirhan_fiker
@yebirhan_fiker