Get Mystery Box with random crypto!

(የኮከብ መጠሪያ ስም ቶረስ ሴት) የውልደት ቀን ከሚያዝያ 12 እስከ ግንቦት 12 | የብዕር አሻራ

(የኮከብ መጠሪያ ስም ቶረስ ሴት)

የውልደት ቀን ከሚያዝያ 12 እስከ ግንቦት 12


»» ቶረስ ሴት ትልቅ ሴት ናት፣ በህይወት ጎዳናዋ የሚጋረጥባትን ማናቸውንም ችግር ለመቋቋም የሚያስችል ውስጣዊ ሀይል አላት፣ የምድር ቅመም ናት።

»» እኔ ነኝ ያለውን ወንድ የምታርበደብድ ሀይለኛ ልትሆንም ትችላለች። ግን ያለ በቂ ምክንያት አትገነፍልም፣ ትግስተኛ ናት።

»» ለሷ ሴት መሆን ማለት የግድ ተሽኮርማሚ እና ደካማ መሆን ማለት አይደለም። የቅርብ ጓደኞቿን ትልቅ ትንሽ ብላ አታንገዋልልም፣ ጓደኛዋ ከሆነ ጓደኛዋ ነው፣ በድርጊቱ ብቻ ትፈርጀዋለች። በዛው ልክ ግን አፀፋውን በጣም ትፈልጋለች።

»» ቀጥተኛ፣ ሀቀኛ፣ ታማኝና ቅናት አልባ ነች። የጄሚኒ ተፅኖ ያለባት ከሆነ ግን ትንሽ ቸኮል ትላለች። ፅድት ያለች ስትሆን፣ መጥፎ ጠረን በሀይል ይረብሻታል።

»» ተፈጥሯዊ መኣዛዎች ይመስጧታል፣ ደማቅ ቀለም ይስማማታል፣ ሰማያዊ የሆነ ነገር ሁሉ ወክክ ያደርጋታል። ሮዝና ሃምራዊም ደስ ይላታል። ሙዚቃና ኪነጥበብንም ታደንቃለች።

»» ቶረስ ሴቶች ፣ "ሹራብህ ይቧጥጣል" የሚሉ አይነት ናቸው ። አይናቸውን ጨፍነው በመዳሰስ ብቻ የጨርቅ ቀለም መለየት ይዳዳቸዋል፣ ልስልስ ልብስ ውስጣቸው ነው።

»» ስትወድም ሆነ ስትጠላ ፊት ለፊት ነው፣ ግልፅና ቀጥተኛ ነች። ይቺ ሰው ትችት ስለማትወድ ችግር ይገጥምህ ይሆናል እና በፀባይዋ ተመቻት።

»» ቶረስ ሴት የህመምና የስቃይ ስሜቶችን ለመቋቋም ያላት ችሎታ የሚያስገርምና የስኮርፒዮ ሴትን ቻይነት እንኳን የሚበልጥ ነው።

»» በአጠቃላይ ግን ቶረስ ሴት መጀመሪያ ላይ እንዳልነው ትልቅና አስተዋይ ሴት ናት።
.
.
.የቀጣይ ወር ትንበያ ይቀጥላል....
.
.
.
.
ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @Yeberashara_bot ማድረስ ትችላላቹ


መልካም ቀን
የብዕር አሻራ
@Yeberashara
@Yeberashara
@Yeberashara