Get Mystery Box with random crypto!

> ውበትሽ አይደለም እኔን የማረከኝ ሁሉን ሴት አስትቶ አንቺን ያስወደደኝ ፀባይሽ አይደለም ከ | የብዕር አሻራ

<<<< ምስጢሩ >>>>

ውበትሽ አይደለም እኔን የማረከኝ
ሁሉን ሴት አስትቶ አንቺን ያስወደደኝ
ፀባይሽ አይደለም ከሌሎች የላቀው
እጅግ ብዙ እንስቶች ውብ ፀባይ አላቸው
ቁመትሽ እንዳልል አውቃለሁ መለሎ
ቀልብን የሚሰርቅ ልብንም አማሎ
አይንሽን እንዳልል ጥርስሽን እንዳልል
ም/ትም አይሆንም ብዙ እንስቶች በሱም ተክነዋል
ብቻ ምን አለፋሽ የመዋደዳችን ምስጢሩ የሆነው
ግራ ጎኔ ሆነሽ በመፈጠርሽ ነው።

(መላኩ ወ/ሰንበት)

ሼር•••
ለመቀላቀል @Yeberashara