Get Mystery Box with random crypto!

2.ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ዮሐንስ ሀገሩ ገሊላ አውራጃ ሲሆን ከወንድሙ ከቅዱስ ያዕቆብና ከአ | የአባቶቼን ርስት አልሰጥም

2.ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ
ቅዱስ ዮሐንስ ሀገሩ ገሊላ አውራጃ ሲሆን ከወንድሙ ከቅዱስ ያዕቆብና ከአባቱ ከዘብዴዎስ ጋር ዓሳ ያጠምድ ነበር፡፡ ማር 1÷19-20 ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ እመቤታችንን እንዲያገለግላት አደራ የተሰጠው ለዮሐንስ ነው፡፡ ዮሐ 19÷26 ጌታ ይወደው የነበረው ዮሐንስ በፍልስጥኤምና በሌሎች ቦታዎች ክርስትና እንዲስፋፋ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በመተባበር አስተምሯል፡፡ ሐዋ 4÷1-22 ፣ 8÷14 ከኢየሩሳሌም ወደ ኤፈሶን በመሄድ በታናሿ እስያ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት በማስተማር ሲያገለግል ቆይቶ በድምጥያኖስ ዘመነ መንግስት ወደ ደሴተ ፍጥሞ ተሰዶ በግዞት ሳለ ራዕየ ዮሐንስን ጽፏል፡፡