Get Mystery Box with random crypto!

#ስም_ብቻ_ምን_ሊጠቅመኝ መጠሪያ ብቻ ከሆነኝ -- እኔ ክርስቲያን መባሌ በግብሬ ካላሳየሁት -- | የአባቶቼን ርስት አልሰጥም

#ስም_ብቻ_ምን_ሊጠቅመኝ

መጠሪያ ብቻ ከሆነኝ -- እኔ ክርስቲያን መባሌ
በግብሬ ካላሳየሁት -- ካልተዋሐደ ከአካሌ
በጨለማ መቅረዝ ሆናኝ-- እግሬን ከእንቅፋት ካላዳነ
ጌታዬ በኔ ካልከበረ -- ስሙ በኔ ካልገነነ
ሻማ ሆኜ ካላበራሁ -- ጨለማ ለዋጠው ወገኔ
ስሙ ብቻ ምን ሊጠቅመኝ -- ምን ሊሠራልኝ ነው ለኔ?
በአርባ ቀኔ ስጠመቅ -- ክርስቲያን ተብዬ ልጠራ
በእምነት ዳብሬ እንዳድግ -- መልካም ፍሬን እንዳፈራ
ሥነምግባር መጠመቄን-- እንዲያሳየኝ አጉልቶ
ክርስትናዬን እንዲናገር -- በደረስኩበት ሁሉ ገበቶ
የተቀበልኩት ልጅነት -- በእኔነቴ ዙርያ አብርቶ
ለዚህ ነበረ ምክንያቱ -- የጥምቀት ክርስቲያን መሆኔ
በጸበሉ ነጽቼ -- ልጁ የተባልኩ እኔ
በአነጋገር በሥራዬ -- ክርስትናዬን ካላሳየሁ
ጌታዬ በሰጠኝ መክሊት -- አትርፌበት ካልተገኘሁ
እንደተዘናጋሁ ካለቀ -- ከተጨረሰ ዘመኔ
ክርስቲያን መባሌ ምን ሊረባኝ -- ምን ሊጠቅመኝ ነው ለ'ኔ?