Get Mystery Box with random crypto!

መፍቀሬ– ሙፍቲዎቹ ዲያቆናት ★★★// //★★★ (በዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ) ዲያቆናቱ ብሔራቸው | ለማስታወስ ብቻ !!

መፍቀሬ– ሙፍቲዎቹ ዲያቆናት
★★★// //★★★

(በዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ)

ዲያቆናቱ ብሔራቸው የዛሬው አ§ማራ ባይሆኑኳ ዐም–ሓራ ናቸው። ለዚያ ነው ኦሮሞዎቹን ኤርሚያስ ለገሰን፣ ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴን፣ ፈንታሁን ዋቄን ከጎንደሬ በላይ አ§ማራ ሆነው የምታገኛቸው።

ዛሬ የሚያበሳጩህ ፖለቲከኛ፣ አክቲቪስት፣ ጋዜጠኛ፣ ምሁራን ዲያቆናት ትናንት የኦርቶ—ዐም—ሓራን ሔጅሞኒ ስርዓት ለመመለስ በገዥው ንዑስ ብሔርተኛውም ፓርቲ (ለምሳሌ ኤርሚያስ ለገሰ)፣ በተቃዋሚውም ፓርቲዎች (ለምሳሌ ዲ/ን ሀብታሙ አያሌው፣ እሰክንድር ነጋ ወዘተ)፣ በቤተ ክህነት ፖለቲካም (ለምሳሌ ዘመድኩን በቀለ፣ ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)፣ በጋዜጠኝነት፣ በምሁርነት ወዘተ ከቤተ–ክህነቷና ከደሴቷ የፖለቲካ ማዕከል ስምሪት ተሰጥቷቸው በሁሉም ቦታ የነበሩ ተናበው የሚሰሩ ኤጀንቶች ናቸው።

የአብዛኞቹ ፖለቲካዊ አሰላለፋቸው "ኢትዮጵያዊ" ብሔርተኛ ነው። አሀዳዊ ነው። የተቀሩት pseudo federalist ነው። የኢትዮጵያ ብሔርተኛ ስንል የየትኛዋ ኢትዮጵያ ብሔርተኛ ማለታችን ነው? የደሴቷ፣ የኦርቶ—ዐም—ሓራዋ ኢትዮጵያ ብሔርተኛ ማለታችን ነው።

የኦርቶ—ዐም—ሓራዋ ኢትዮጵያ መገለጫዎች እነኚህ ናቸው።

ሃይማኖቷ ኦርቶዶክስ የሆነ፣ ራሷ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን የሆነች ናት። ዜጎቿ —በክርስትና ሀርነትን የተጎናፀፉ፣ በእግዜር የተመረጡ ናቸው። ስርዓቷ—ሰለሞናዊ የሆነ፣ ህግ አውጪዋ የኢት/ኦ/ቤተ ክርስቲያን፣ ህግ አስፈፃሚዎቿ ከንጉሥ ሰለሞንና ንግስት ሳባ (አዜብ፣ ማክዳ) የተወለዱ፣ በክብረ ነገሥት፣ በፍትሐ ነገሥትና በኢ/ኦ/ቤተ ክህነት ህግ የተዳኘች ነች።

ታሪካዊ(ነባር) ጠላቶቿ:— የኦርቶ—ዐም—ሓራዋ ኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ተፃራሪ የሆኑ ኃይሎች። በሃይማኖት እስላሞች፣ በነገድ ኦሮሞዎችና ብሔር ብሔረሰቦች።

ቅድመ ማንነታቸው:— በሴኪዩላር ስም በተለየ ተልዕኮ በተደራጁ ኦርቶ—ሀገራዊ ፓርቲዎች አባልና አመራር በመሆን ፀረ ኦርቶ—ዐም—ሓራ ናቸው ያላቸውን ንዑስ–ብሔርተኞችን (ኢህአዴጋውያንን) ሲታገሉ የነበሩ ናቸው።

በአሃዳዊው የኦርቶ–ዐም–ሓራ ብሔርተኛውና በንዑስ ዘውጋዊው ብሔርተኛ ኃይል መካከል ለባለፉት ሰላሳ ዓመታት በነበረው የሃይል ፉክክርና መነጣጠቅ ትግል ሒደት ድህረ 1997 የማይቀመስ የማይነካ የሆነባቸውን የኢህአዴግ መንግሥት አቅም በቅጡ ባለመረዳት አንዋር መስጅድ ሆኖ ማስጨነቅ የያዘውን እስላም (ታሪካዊ ጠላታቸው) ታክቲካሊ በመደገፍ በእስላሙ ተጋፋጭነት የኢህአዴግን ውድቀት ለማፋጠን ካልኩሌት አድርገው የሙስሊሙ ወዳጅ መስለው ከቀረቡ ኃይሎች መካከል የነበሩ ናቸው።

እነ ዲያቆን ዛሬ:—

ለሰላሳ ዓመታት ኦርቶ—ዐም—ሓራው ሀገራዊ ብሔርተኛ ኃይል የትኛውንም መንገድ ተጠቅሞ ንዑስ ብሔርተኛ ያለውን (የዘውግ ብሄርተኛ) ሥርዓት አጥፍቶ የአባቶቹን ስርዓት ለመመለስ በኢትዮጵያ ስም ሲምል ሲገዘት የነበረው የሀሳዊው ኢትዮጵያዊነት (ዐምሓራዎች "ት§ግሬና ዐ§ማራ") ብሔርተኞች እንቅስቃሴ ለሰላሳ ዓመታት ብዙ ውጣ ውረድ አይቶ፣ ብዙ ሃብትና ትውልድ ሰውቶ ሲጠብቀው ነበረው የድህረ ኢህአዴግ ውድቀት አብዮት ፍሬ ድንገት ባልጠበቀው መልኩ በንዑስ ብሔርተኛው ኃይል በተለይም በኦሮሞ ብሔርተኛውና በፕሮቴስታንቱ ኃይል ጥምረት ሲጠለፍ የታሰበው የተናፈቀው ሁሉ ተስፋው ሁሉ አፈር ዴቼ በላ።

ያኔ በሃሳዊው ኢትዮጵያዊነት ሽፋን ይንቀሳቀስ የነበረው ኢትዮብሔርተኛ ኃይል ሁሉ ቀድሞ በንዑስ ብሔርተኛው (በፌደራሊስቱ ኃይል) ይጠረጠርበት ወደ ነበረው የህዝብ፣ ተቋምና የኢዶሎጂ መሰረቱ ወደ ቤተክህንትና ዐ§ማራ ክልል ጠቅልለው መሸጉ። ተሰደዱ! የዐ§ማራ ብሔርተኝነትም ዋና መጠለያ ሆናቸው።

የህዝብ መሰረት ወደ ሆነው የዐ§ማራ ህዝብ ሲሰደድ በሃሳዊ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ስም ለዘለዓለም አገሪቱን ቀይደው የያዙባቸውን ትርክቶች፣ ተቋማት፣ አሰራር፣ ባህሪና ኦ/ቤተ ክርስቲያንን ጭምር ይዘው ወደ ዐማ§ራ ክልል ይዘው በመሰደድ ከዚያ ተስፈንጥረው ለመምጣት መከራውን የሚያየው ኃይል የአ§ማራ ክልል ስቴት ተክለ ቁመና ምቹ ሆኖ ጠበቀው። ቤተክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበህ የምትመክረውና አማራ ክልል ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ፣ ክልሉ ተቋማት ውስጥ ሆነህ የምትመክረው አንድ እሰኪሆን ድረስ ክልሉ ምቹ ሆኖ ጠበቃቸው።

የእነ ዲያቆን ታሪካዊ ጠላት እስላም ነው። አረብና ቱርክ ነው። ኦሮ—ጴንጤው ኃይል ሌላ ትኩሳት ዘመንኛ ጠላታቸው ነው። ለግራኝ ሺ አመት የተሰላ የጦር ታክቲክ ለኦሮ–ጴንጤው ኃይል አይሰራምና እንደ አጤ ሚናስ መደናገጣቸው አይቀሬ ነው። የእስላምና የአረብ ቱርክ ጭራቅ ተረክ በክልሉ ፍሬ አፍርቶ ከሞጣ እስከጎንደር በምርቱ ተደስተዋል።

ታሪካዊ ጠላታቸውን ለማዳከም ሱልጧኔቶቹ መውደም አለባቸውና ቴዎድሮስን ሆነው ማመዶች ስርዎመንግስት ይኖርህ ዘንድ በፍፁም አይፈቅዱልህም። ከቻሉ እንደ ቴዎድሮስ ሰባት ጊዜ ዘምተው መጅሊስህን ያፈርሱታል። ካልቻሉ ንዋዬ ክርስቶስ ሸኽ ዘከርያን (በሱፊ ስም ዛሬ እየተንቀሳቀሰ ያለውን አረም ኃይል) ልከው ያወድሙሃል! ለዚያ ነው መፍቀሬ— ሙፍቲ ሆነው የተገኙት።

ወዳጄ ታሪካዊ ጠላታቸው ሆነህ ሳለ፣ ተቋም ሳይኖርህ እየዋጥካቸው ተቋም ኖሮህ፣ ተደራጅተህ፣ በተቋም ታግዘህ ምን ልታደርጋቸው እንደምትችል የማያስቡ ቂሎች አይደሉምና እንኳን መፍቀረ ሙፍቲ ሆነው ሙፍቲህም ሆነው ከቻሉ ይመጡልሃል ስራቸውን እየሰሩ ነው። አትገረም

በየቀኑ ተገርመህ ደንግጠህ ትችለዋለህ? የቤት ሥራህን ሥራ

https://t.me/abduljelilshekhalikassa