Get Mystery Box with random crypto!

ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (ረሂመሁላህ) በ | Yasin Muhammed - Official Channel✔

ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (ረሂመሁላህ) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦
"ያ አባ ኢስሐቅ! አላህ ለምኑኝ እቀበላችሁለሁ አለ ነገር ግን ዱዓ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣን" የሚል ጥያቄ ጠየቋቸው...

እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "ቀልባችሁ በአስር ነገሮች ሞታለች" አሏቸው።
እነሱም፦ "ምን ምንድን ናቸው?" የሚል ጥያቄ አነሱ። እሳቸውም፦
❶ኛ) አላህን አውቃቹት ሐቁን አልተወጣችሁም።
➋ኛ) ቁርኣንን አነበባችሁት፣ አልሰራችበትም።
➌ኛ) ነቢዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፣ ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።
➍ኛ) የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።
➎ኛ) ሸይጣን ጠላታችን ነው ብላችሁ ከሱ ጋር ገጠማቹ።
➏ኛ) ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ ሚሆን ስራ አልሰራችሁም።
➐ኛ) የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።
➑ኛ) ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።
➒ኛ) ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፣ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።
➓ኛ) ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።
ታዲያ እንዴት ይቀበላችሁ
ﻓﻜﻴﻒ ﻳﺴﺘﺠﺎﺏ ﻟﻜم؟
ምንጭ:- ጃሚዑል በያን አልዒልሚ ወፈድሊሂ (2/12)

አላህ ዱዓ አድርገው ዱዓቸውን ከሚቀበላቸው ባሮቹ ያድርገን