Get Mystery Box with random crypto!

አክሲዮን ያድናል! የሁሉ ትራንስፖርትና ቱሪዝም አ.ማ ******* የአንድ አክስዮን መደበኛ ዋጋ | Yalelet Wondye

አክሲዮን ያድናል!
የሁሉ ትራንስፖርትና ቱሪዝም አ.ማ
*******
የአንድ አክስዮን መደበኛ ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ሲሆን የሚከፈል የስራ ማስኬጃ እና የአገልግሎት ክፍያ 10% ነው፡፡

ዝቅተኛ የአክስዮን መጠን ብዛት 50 የማይነጣጠሉ ተራ አክስዮኖች ወይም አንድ ዕጣ ሆኖ በብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ሲሆን የአክሲዎኑን 50% ማለትም 25 አክስዮኖች በብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ) ቅድሚያ በመክፍል ቀሪውን 50% በፊርማ ቃል የሚገባ ሆኖ ድርጅቱ ስራ በጀመረ በስድስት ወር ጊዜ የሚከፈል ይሆናል፡፡

ከፍተኛ የአክስዮን መጠን ብዛት 5000 ተራ አክሲዮን ወይም 100 እጣዎች ሁኖ 5,000,000(አምስት ሚሊዮን) ብር ሲሆን (10% የስራ ማስኬጃ እና የ አገልግሎት ክፍያ ጨምሮ ብር 5,500,000 (አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) በመግዛት የ ‘’ የሁሉ ትራንስፖርትና ቱሪዝም አክስዮን ማህበር’’ መስራች አባል መሆን ይቻላል።