Get Mystery Box with random crypto!

ህዝብ ቋሚ ጥቅም ነው! ******* በፖለቲካ መስመር እና አመለካከት መስማማትም ሆነ አለመስማማት | Yalelet Wondye

ህዝብ ቋሚ ጥቅም ነው!
*******
በፖለቲካ መስመር እና አመለካከት መስማማትም ሆነ አለመስማማት ከህዝብ ህልውናና ጥቅም ጋር የሚያገናኘዉ አንዳችም ምክንያት የለውም። ህዝብ ሁሌም ቋሚ ጥቅም ነዉ።

ፖለቲከኞች በአመለካከትና በአሰላለፍ ልዩነት (የተለያዩ ፓርቲዎች ስር ሆኖ መታገል፣ ገለልተኛ መሆን ወዘተ) የህዝብን ጥቅም ማስከበር ከተሳናቸዉ፣ ቀድሞዉኑ የሥልጣን ጥም እንጂ ሕዝባዊ አላማ (የሕዝቡን ማህበረ–ፖለቲካዊ ጥቅም የማስከበር ዓላማ) አልነበራቸዉም ማለት ነዉ።

በተለያየ እሳቤ ውስጥ ያሉ፣ የፖለቲካ ሃይሎች በህዝብ ቋሚ ጥቅም ዙሪያ፣ ተመሳሳይ አቋም ከያዙ ግን የፖለቲካን ምንነት በዉል ተረድተዉታል ተብሎ ይወሰዳል። አንዳንድ ግዜ በፖለቲካ ሃይሎች መካከል አለመግባባት የሚፈጠረዉ፣ በህዝብ ጥቅም ዙሪያ የነጠረ አቋም ባለመያዛቸው ሳቢያ ነዉ።

በዚህ ግዜ መወነጃጀል፣ ሴራ መጎንጎን፣ አድርባይነት፣ ጥሎ ለማለፍ የሚደርግ ቡድንተኝነት የአመራሮቹ የዕለት ተዕለት ሥራ ይሆናል። ህዝብ ሙሉ በሙሉ ይረሳል። በሌሎች (በተደራጁ ሃይሎች) አጀንዳ የሚሳብ አመራር ይበረክታል። ህዝብ እንደ ህዝብ ተቅበዝባዥ፣ የተበታተነ እና በሞራል የተዳከመ ሆኖ፣ መፃኢው እድል በሌሎች ይሁንታ ላይ የተመሠረተ ይሆናል።

በዚህ ግዜ መፍትሔው፣ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ ይሆናል። በሕዝብ ጥቅም ዙሪያ ተፃራሪ አቋም ያላቸውን ሃይሎችን፣ በተደራጀ የህዝብ ግኑኝነት ሥራ (political indoctrination)፣ ከምልዐተ ሕዝቡ የመነጠል፣ ፖለቲካዊ ቅቡልነታቸዉን የማዳከም፣ ማህበራዊ ትስስራቸውን ማላላት ቀዳሚ ተግባር ይኾናል።
ይህንን ለማድረግ ደግሞ የበቃ ፖለቲካዊ ባሕሪ መላበሥ ያሻል።

Workayehu Chekole Desta