Get Mystery Box with random crypto!

ኦሮሚያ የምትባል ሉአላዊት አገር በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ለመገንባት የኦሮሞ አመራሮች ምን አሉ? | Yalelet Wondye

ኦሮሚያ የምትባል ሉአላዊት አገር በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ለመገንባት የኦሮሞ አመራሮች ምን አሉ?
********
ኦህዴዶች (የኦሮሞ ብልፅግና) በተለይ አማራውን "ጫጫታቸው ከሳምንት አያልፍም ሥራችንን አጠናክረን እንስራ" ይላሉ፡፡ እኛም በእነሱ ግምት ልክ ሆነን እንገኛለን፡፡ አሁንም የወለጋ ጉዳይ ነገ በሌላ አጀንዳ ይወረሳል፡፡ እስከነ አካቴው በሌላ ይተካል፡፡

የኦሮሞ ብልፅግና አመራሮች ከተናገሯቸው፣ ከሳምንት ጫጫታ በኋላ የተረሱ የተወሰኑ ንግግሮችን እናስታውስ

1
“ሰዎቹ (የአማራ ፖለቲከኞች) የሚችሉት ሶስት ነገር ብቻ ነው:- ጩኸት፣ ለቅሶና ስም ማጥፋት። ለአልቃሻ ብትችሉ መሀረብ (ሶፍት) ማቀበል እንጂ ምን አስጨነቃችሁ? ያልቅሱ ተዋቸው። እኔ የሚያስጨንቀኝ ዝም ሲሉ፣ ሳይነፋረቁ ሲቀሩ ነው። ዝም አሉ ማለት እኔ እነሱን እያስደሰትኩ እንደሆነ ይሰማኛል...!”
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
=========•••••••=============

2
“የተሳፈርነው አንድ ላይ ነው ወራጅ የለም”
አዲሱ አረጋ ቄጢሳ፣ የጃዋርን እና የሽመልስን አብዲሳ ለጥፎ አንድነታቸውን የገለጸበት
=========•••••••=============

3
“ትናንትና ያዋረደንን፣ አዋርደነዋል፤ ትናንት የሰበረንን ሰብረነዋል። ትናንትና አትወጡም አትገቡም ብሎ አጥር ያጠረብን ዛሬ ወጥቶ መግባት ከእኛ ፍቃድ ውጭ አይችልም፡፡”
በወልመል የግድብ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ በኦሮምኛ ያደረጉት ንግግር
=========•••••••=============

4
“የኦሮሞ ሕዝብ እዚህ ነበር የተሰበረው፤ እዚህ ነበር መዋረድ የጀመረው፤ እዚህ ነበር ቅስሙ የተሰበረው፡፡ ቱፋ ሙናን ፣ የዚያን ዘመን ታጋዮች የነፍጠኛ ስርዓት እዚህ ነበር የሰበራቸው፡፡ ዛሬ የሰበረንን ሰብረን ፣ ከመሰረቱ ነቅለን፣ ኦሮሞ በተዋረደበት ቦታ ተከብሮ ይገኛል፡፡”
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
=========•••••••=============

5
“…እኔ እና ኢ/ር ታከለ ኡማ ጠዋትም ማታም ሻይ አብረን ስንጠጣ፣ የኦሮሞን ጥቅም አዲስ አበባ ውስጥ ለማስጠበቅ፣ በተለይም ከአሁን ቀደም ተገፍቶ ከዐዲስ አበባ ሲወጣ የነበረውን አርሶ አደርና፣ ኦሮሞነት ከከተማ ውጭ እንዳይሆን ከፍተኛ ሥራ እየሠሩ ነው፡፡”
አቶ አዲሱ አረጋ ቂጢሳ
=========•••••••=============

6
“ከሶማሌ የተፈናቀሉትን አምስት መቶ ሺህ በላይ ሰዎችን፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ እና አዲስ_አበባ ውስጥ አስፍረናል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ስድስት ሺህ ሰዎችን አስገብተናል”
አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት
=========•••••••=============

7
“አዲስ አበባ ላይ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጀምሮ ሠፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። የዛሬ ሦስት ዓመት በዋቆ ጉቱ እና በታደሠ ብሩ ስም ትምህርት ቤቶች ከፍተን የሚማርልን ተማሪ አጣን። ስለዚህ ተማሪ ከቡራዩ እየጫንን እናመጣ ነበር። አምና የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትሩ ዶ/ር ዐብይ በሰጡት ውሳኔ መሠረት በሁሉም ትምህርት ቤቶች አስጀመርን፡፡ ከ5,700 በላይ መምህራን አዲስ አበባ ውስጥ አስገብተናል።
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
=========•••••••=============

8
“የኦሮሞ ትግል ማዕከል አዲስ አበባ እና አዲስ አበባ ብቻ ናት”
የወቅቱ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ
=========•••••••=============
9
“ጠላት ነው ሰው እየሞተ ችግኝ አይተከልም የሚለን ፤ጠላት ነው እንዳትሰሙ፡፡ ሰው እየሞተ የሞተበት ቦታ ችግኝ እንተክላለን ቢያንስ አስከሬኑ ጥላ እንዲኖረው፡፡”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
=========•••••••=============

10
“አባይን ተሻግረን ባህርዳር ድረስ ሄደን ግማሹን Convince ገሚሱን Confuse አድረገን ቁማር ቆምረን ቁማሩን በልተን ተሳክቶልን ተመልሰናል፤ እንዴት አደናበራችኋችው ነው የምትሉን? ምን አገባችሁ?”
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
=========•••••••=============

11
“ታስሮ ጀግና ለመሆን የሚሯሯጥ ጋዜጠኛ አለ…. ምርጫ ሳታሸንፍ ባለአደራ ምናምን የሚባል ጨዋታ ውስጥ የምትገባ ከሆነ ግልጽ ጦርነት ውስጥ እንገባለን፡፡ ይህ መታወቅ አለበት፡፡”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ
=========•••••••=============

12
“ዐዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን ህዳሴ ግድቡን ኦሮሞ መቆጣጠር እንዲችል ቤንሻንጉልጉምዝ ውስጥ ኦሮሞዎችን በማስፈር ዲሞግራፊውን እየቀየርነው ነው! ክልሉ ውስጥ ኦሮሞ 37% ደርሷል፡፡”
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
=========•••••••=============

13
“ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናት፡፡ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆኗን ተከትሎ የኦሮሚያ መዝሙር በት/ቤቶች መሰጠቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
=========•••••••=============

14
“ብልጽግናን የሠራነው ለእኛ እንዲመች አድርገን ነው። ብልፅግና የኦሮሞ ነው። ብልፅግናን ኦሮሞ ወይንም ኦሮሞ የፈቀደለት ብቻ ነው የሚመራው። ……አምስት ቋንቋ የመረጥነው ለእነሱ አስበን አይደለም። ለኦሮምኛ ብለን ነው። አማርኛ እየደከመ ነው፣ እየቀነሰ ነው። ኦሮምኛ ከአማርኛ በላይ እየተነገረ ነው።”
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
=========•••••••=============

15
“ለዐዲስ አበባ ብዙ መፍትሔ አለ። አንደኛው በሕገወጥም ሆነ በህጋዊ መንገድ ሰው ማስገባት ነው። ሌላኛው አዲስ አበባን የማትጠቅም ከተማ ማድረግ ነው። አራት አምስት የፌደራል ከተማ እንመሰርታለን። ድንበር የመካለያ አዋጁ ወጥቷል። ለስሙ ነው እንጅ ይጸድቃል።”
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
=========•••••••=============

16
“በቄሮ ትግል ፌስታሉን ይዞ ከእስር ወጥቶ ሲያበቃ ዛሬ 'ባለደራ መንግሥት' ብሎ ራሱን መሾም አልያም 'ባላተራ መንግሥት' ብሎ ለውጥን ማጣጣል በምንም ስሌት ተቀባይነት የለውም። መንግስታችንን ለመፈታቱን ባለተራ ባላደራ እያለ የሚያላዝነውን ወደ ትክክለኛ መስመር ለመመለስ እንሰራለን ።"
አቶ አዲሱ አረጋ ቂጢሳ
=========•••••••=============

17
ህወሓት ኢህአዴግን የፈጠረው ለራሱ ጥቅምና ፍላጎት ነው እኛም ብልፅግናን የመሰረትነው ለማንም ሳይሆን ለራሳችን እንዲመች አድርገን ነው። ከዚህ በኋላ እንደ ኦሮሞ እኛ ሳንፈቅድ እንኳን ፌደራል ላይ ክልል ላይ አንድ ሰው ወደ ስልጣን አይወጣም።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ
=========•••••••=============
18
የአዲስ አበባ ጉዳይ የ20 ዓመታት የትግላችን ውጤት ነው። የባለቤትነት ጉዳይ መልስ እንዲያገኝ ነበር ትግላችን። ትልቁ ድላችን ይህ ነው የፊንፊኔን ጉዳይ መልሰናል።
ዐብይ አህመድ አሊ
=========•••••••========