Get Mystery Box with random crypto!

➭ በገነት ያሉ ሦስቱ አስደናቂ ነገሮች አንድ አባት ወደ ገነት ከገቡ በኋላ ለሌላ አባት | ያህዌ ንሲ (እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው)

በገነት ያሉ ሦስቱ አስደናቂ ነገሮች

አንድ አባት ወደ ገነት ከገቡ በኋላ ለሌላ አባት በህልም እንዲህ ሲሉ ነገሩት።
ወደ ገነት በገባሁ ጊዜ ሦስት ነገሮች አስደነቁኝ።

➻ የመጀመሪያው ገነት ውስጥ ይገኛሉ ብዬ ፈጽሞ የማልጠብቃቸው በእኔ ዓይን ኃጢአተኞች የሆኑ ሰዎችን በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው።

➼ ሁለተኛው በገነት እንደሚኖሩ በ እርግጠኝነት የምገምታቸውን ጻድቃን መስለው የታዩኝን ሰዎች በገነት ውስጥ አለማግኘቴ ነው።

➼ ከሁሉም በላይ ያስደነቀኝ ግን እንደኔ ዓይነቱን እጅግ ኃጢአተኛ ሰው በገነት ውስጥ ማግኘቴ ነው አለ።

▸ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው "እውነት እላችኋለሁ ቀራጮች እና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል" ማቴ ፳፩፥፴፩
#ሼር እያረጋቹ

@ORTODOX_RINGTONES