Get Mystery Box with random crypto!

#ውስጣዊው #ሰው ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡ይህ ጀግና | Living Dream

#ውስጣዊው #ሰው

ባንተ ውስጥ ያንቀላፋ ምንም ነገር ማድረግ የሚችል ጀግና ሰው አለ፡ይህ ጀግና ገራሚ ሐይል ነው፡ይህንን ሐይል ማድመጥ ጀምር፡የስንፈናን አቅምና ሐይል ከውስጥህ ነቅሎ ይጥለዋል፡፡

ሰነፉ ማንነትህ ፈሪ ነው፡ ጀግናው ማንነት #አማኝ ነው፡፡
ሰነፉ ማንነትህ ሰነፍ ነው፡ ጀግናው ማንነትህ #ለፊ ነው፡፡
ሰነፉ ማንነትህ "ሰው ምን ይለኛል?" ይላል፡ ስህተት ይፈራል፡ ፍጹም መስሎ ለመታየት ይሞክራል፡፡

ጀግናው ማንንትት ግን "እኔ ራሴን ምን እላለሁ? ፈጣሪስ ምን ይለኛል?" ይላል ፡ፍጹም መስሎ የመታየት ምኞት የለውም፡፡እሱ የህይወት ዘመን ተማሪ ነው፡ ሰነፉ ማንነትህ ጊዛዊ ደስታን ብቻ ይፈልጋል፡ ጀግናው ማንነትህ ግን ረጅሙን የውስጥ ሰላም፣ ፍቅር፣ ወሳጣዊ ደስታና ስኬት ይሻል።#ይህ ጀግናው ማንነት = ውስጣዊ ማንነትህ ነው

ሰነፉ ማንነት =ውጫዊው ማንነትህን ይወክላል፥ ማየት ፤መታየት፤ ፍረሀት፤ማስመሰል፤የማይፀናና የሚናወጥ መንነትህ ነው ይህ ፈርው መንነትተህን አትስማው
#ውስጥህ ያለውን ሰው አድምጠው ጀግናው ማንነትህን መኖር ጀምር ፤ መሆን የምትፈልገውና የሆንከው የተለያዩት፣ መኖር የምትፈልገውና አሁን የምትኖረው ህይወት ያልተገናኙት፣መሄድ የምትፈልገው ጎዳናና አሁን የቆምክበት ቦታ የተራራቁት፣ እርግጠኛ ሁኜ የምነግርክ በውስጥህ ያለውን ጀግና ማንቃት አልቻልክም።ውስጥህን አድምጠው በገደል ጫፍ ላይ ቆማ በየግዜው ንፋስ ወደገፋት አቅጣጫ እንደምታጎነብስ ዛፍ አትሁን ሰው ስላደረገው ወይንም ባጋጣሚ ጎረቤት ጓደኛ ሰለመከረህ ብቻ፣ ወደዛ አታዘምብል ምክንያቱም ይሄንን አጋጣሚ ጉዞ ሌላ አጋጣሚ ልገታብህ ይችላል።

ውስጥህ ያለው ሌላ የምትኖረው ሌላ፤ ራዕይክ ዓላማክ ሌላ አንተ የምትሆነው ሌላ አሁን ራስህን መጠየቅ ጀምር???
???ለምን?? ??

ድንቅ ምሽት ተመኜሁ
በቅንነት #ሼር ያድርጉ


@ww1dreamers
@ww1dreamers