#እግዚአብሔርን_ማወቅ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን #ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።” — ዮሐንስ 17፥3 “እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል #እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ።” — ፊልጵስዩስ 3፥10-11 “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም #ማወቅ ማስተዋል ነው።” — ምሳሌ 9፥10 “እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ #ታውቁ ዘንድ በግብፃውያን ያደረግሁትን ነገር ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጅህ በልጅ ልጅህም ጆሮች ትነግር ዘንድ፥ ይህችንም ተአምራቴን በመካከላቸው አደረግ ዘንድ የእርሱን የባሪያዎቹንም ልብ አደንድኜአለሁና ወደ ፈርዖን ግባ አለው።” — ዘጸአት 10፥1-2 “እግዚአብሔርን #ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤” — ሮሜ 1፥28 “አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ #አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው።” — ዘጸአት 33፥13 “መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች #ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።” — ዮሐንስ 10፥14-15 “...ነገር ግን አምላካቸውን #የሚያውቁ ሕዝብ ይበረታሉ፥ ያደርጋሉም።” — ዳንኤል 11፥32 “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን #በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።” — ኤፌሶን 1፥17 “#እንወቅ፤ #እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ እንደ ዝናብም ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ መጨረሻ ዝናብ ይመጣል።” — ሆሴዕ 6፥3 3.6K views▮E-benezer▮, 19:55