Get Mystery Box with random crypto!

ጊዜው ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ፈሪሳውያንን የተቸበት እና የተቃወመበት ዋነኛው ምክንያት እነ | WORD OF GOD

ጊዜው
ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ፈሪሳውያንን የተቸበት እና የተቃወመበት ዋነኛው ምክንያት እነሱ የሰማይን መልክ እያዩ ዛሬ ይዘንባል አልያም ዛሬ ሞቃት ይሆናል እያሉ ሲናገሩ እንዳሉትም እየሆነላቸው ሳለ ነገር ግን ዘመኑን መመርመር እና ማወቅ ባለመቻላቸው ኢየሱስ ነቅፏቸዋል። እንደ ይሳኮር ልጆች ዘመኑን የሚረምሩ ብልሆች መሆን ሲገባቸው ቅዱስ ቃሉ በእጃቸው እና በአይምሯቸው እያለ፥ ለዘመናት መሲሑን እየተጠባበቁት ኖረው መሲሑ ሲመጣ ግን ለሞት አሳልፈው ሰጡት።
ዛሬም በዚህ ዘመን የምንገኝ ቅዱሳን ሁሉ ዘመኑን እና ጊዜው በእግዚአብሔር ቃል መነፅር እና በመንፈስ ቅዱስ አብርሆት ልንመረምር ደግሞም ልንነቃ ያስፈልገናል። ልክ እንደ ፈሪሳውያን ለዘመናት መሲሑን ጠብቀን መሲሑ ሲመጣ ለሞት አሳልፈን እንዳንሰጥ እንጠንቀቅ።
ጊዜውን በደንብ ላስተዋለ ይህ ጊዜ የዘመን ፍጻሜ ነው። አለም ልትጠቀለል እና የእግዚአብሔር ፍርድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊዘንብ አኮብኩቦ ያለበት ጊዜ ሲሆን ግን እግዚአብሔር ከቁጣው በፊት ምሕረቱን ያስቀድማልና ምድራችንን በቁጣው ከመጎብኘቱ በፊት ሪቫይቫልን ለምድራችን ይልካል። የሚመጣው መከራ እና ቁጣ አለም አቀፍ እንደመሆኑ የሚመጣውም ሪቫይቫል አለም አቀፍ የሚሆን ይሆናል።
ሪቫይቫል እየመጣ በደጅ ነው። ሁሉም ሰው ሊነቃ ያስፈልጋል። በቅዱስ ቃሉ እና በቅዱስ መንፈሱ ሁሉን እየመረመርን ራሳችንን ለሚመጣው ሪቫይቫል እናዘጋጅ። የእግዚአብሔር ጉብኝት ለዓለም ሁሉ እየመጣ ነውና በደንብ ነቅታችሁ ተዘጋጁ።
ኢየሱስ በእርግጥ ይመጣል!!!!!

Join us @
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival