Get Mystery Box with random crypto!

ጭር ያለ ቦታ እንገናኝ ብዙ ወጣቶች በወሲባዊ ሃጢያት #ለመውደቃቸው እንደ ምክንያት የሚያቀር | Virtuous women💃💃let's learn

ጭር ያለ ቦታ እንገናኝ

ብዙ ወጣቶች በወሲባዊ ሃጢያት #ለመውደቃቸው እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት ከፍቅር ጓደኛቸው ወይም ከተቃራኒ ፆታ ጓደኛቸው ጋር ሰው የሌለበት ፣ ጭር ያለ ፣ ጨለም ያለ ቦታ መገናኘታቸው እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡

"ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።"
              (የዮሐንስ ወንጌል 3:19)

ጥንዶቹ ሳያስተውሉ አልያም ደግሞ ከሁለቱ አንዳቸው በሌላኛቸው ተታለው ወይም #ተገፍተው ሊሆን ይችላል ጭር ወዳለ ቦታ የሚሄዱት ፡፡

መፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ ሰው እጅግ አፀያፊና ህይወትን ከሚያመሰቃቅል ከዝሙት ሃጥያት ማምለጥ የሚችለው #በመሸሽ ብቻ እንደሆነ ይናገራል ፡፡

ስለዚህ የእጮኝነት ጎዳና ውስጥ ለመግባት ብቁ የሆናችሁ ወጣቶች ከእጮኛችሁ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የግድ ነው ነገር ግን ጊዜ ለማሳለፍ ጨለማንና ጭር ያለ ቦታን መምረጥ የለባችሁም ፡፡ እንደ ካፌ እና ሰዎች የሚንቀሳቀሱባቸው መናፈሻዎችን መጠቀም ይገባችኋል ።

           SHARE    SHARE 


@biblicalmarriage
@biblicalmarriage