Get Mystery Box with random crypto!

ውድ የዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች በሙሉ የወሎ ዩኒቨርስቲ ደሴ ካምፓስ በጎ አድራጎት ክበብ ነገ በ | Wollo University Dessie Campus

ውድ የዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርስቲ ደሴ ካምፓስ በጎ አድራጎት ክበብ ነገ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የእናቶች ቀን በማስመልከት በግቢያችን ያሉ በተለያዩ ስራዎች ወገባቸውን እየሰበሩ የሚያገለግሉንን እናቶችና እህቶች በሚሰሩባቸው ዘርፎች በጉልበት የምናገለግልበትና አለንላችሁ የምንልበትን ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅቷል።

በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ ለመሆን የምትፈልጉ በጎ ልብ ያላችሁ ተማሪዎቻችን በሙሉ ነገ ከጠዋት 4:00 ጀምሮ በግቢያች በሚከወኑ ልዩ ተግባራት ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።

ቀን - እሁድ ግንቦት 6 / 2015
ሰአት - 4:00
የኦርየንቴሽን ቦታ - LH block 24

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ

ተማሪ ሽመልስ  +251930509086
ተማሪ ሃብታሙ  +251919717841