Get Mystery Box with random crypto!

እውነት እና ፍልስፍና? እውነት ምንድነው?እውነት ማነው?እውነት የት ነው?ፍፁም ወይስ አንፃራዊ ወ | ፍልስፍና

እውነት እና ፍልስፍና?

እውነት ምንድነው?እውነት ማነው?እውነት የት ነው?ፍፁም ወይስ አንፃራዊ ወይስ የለም?እውነት ምንድነው ብሎ መጠየቅ በእርግጥ አስፈላጊ ነው?ለምን እንጠይቃለን ግን?¿......እነዚህን መሰል ጥያቄዎች ፈላስፎችም ሆኖ ተመራማሪዎች የሚጠይቁት ነው ይዘቱ ይቀያይር እንጂ! ከዘመን ዘመን እየተጠየቀ 'መልስ' ተብለው የተሰጡትን ሀሳቦች ችግሩን እየነቀፈ እና እያረቀቀ ያለንበት የእውነት 'ጥያቄ መልስ' ላይ ደርሰናል።ከዚህ በኋላስ ግን..?

በሰዎች የየለተለት እንቅስቃሴ ውስጥ እውነት እንደብርቅ እየተቆጠረች እና እየደበዘዘች ጉዞዋን በዝግመት እየቀጠለች ላለችው እውነት ትጠፋ ይሆን? ማለት ተገቢ ጥያቄ ነው! ለምን እውነት መናገሩ ሆነ ማሰቡ ከበደን?እነዚህን የማህበረሰብ የእውነት 'ቀውስ' ለመፈተሽ መጀመሪያ <<እውነት ምንድነው?>> የሚለው የጲላጦስ ጥያቄ በፈላስፎቹ ሀሳብ ማወቅ እና ማሸት ያስፈልጋል።ሌላውስ?

ከፍልስፍና መንደር ስንዘልቅ "የመጀመሪያዎቹን" የግሪክ ጠበብቶች እናገኛለን።ብዙዎቻንን እውነት ምን እንደሆነ በፍልስፍና ለማወቅ የተነሳን ጊዜ የጥንት እሳቦቶቹን ሰምተን ወይም አንብበን ስለሆነ እውነትን ከዘመናዊው ፍልስፍና አንፃር መቃኘቱ የተገባ እንደሆነ እሙን ይመስለኛል።

እውነት ከዘመናዊነት ፍልስፍና ማለትም ከፈረንሳዊው ሬኔ ዴካርት ፍልስፍናዊ አቅጣጫዎች በፊት በመካከለኛው ዘመን በእግዚአብሔር መኖር ጋር የተገናኘ ባህሪ ተሰጥቶት ፍፁማዊነትን የተላበሰ የእውነት ትርጓሜ ነበር ከእሱ በፊት በጥንቱ ደግሞ አንፃራዊ እና ፍፁማዊነትንም የያዘ የነበረው እውነት በጥንቱ በእነፊሮ፣በመካከለኛው በቶማስ አኳይነስ እንዲሁም በዘመናዊው ደግሞ በሦስት ታላላቅ ፈላስፎች የስህተት ችግርን በመተቸት እየረቀቀ መጥቶል።

እውነት ከድህረ ሶቅራጠስ እስከ ድህረ ዘመናዊነት(Post-modernism) ዘመን ድረስ በፈላስፎቹ የህይወት ምልከታ ጉዞ የተቃኘ ነበር(ነውም!)። በዘመናዊው ፍልስፍና እውነት የመፈተሽ ጉዞ በእነኒቼ፣በርትናንድ ረስል፣ ኢማኑኤል ካንት፣ እንዲሁም ሌሎች ታላላቅ አሳቢያን አስተሳሰቦቹ ስያሜዎች እየተሰጣቸው እና እየረቀቁ ያደጉት በዘመናዊ(Modern Philosophy) ዘመን ነበር።በእርግጥም በቀደሙት ጊዜያት ስያሜ ቢኖረው እንደዘመነኛው የእውነት መልስም ሆነ ጥያቄ ረቀቀ ያለ አልነበረም።

በዋናነት በ3ት ፅንሰሀሳቦች ይመደባል፦

1)Correspondens(ህገ-መጣጣም)

፦ይህም እውነት የእውነት ፅንሰሀሳብ ዘረፍ የሚለው ነገር ነገሩ በገሀዱ አለም ካለው ነገር ጋር ሲመሳሳል ነው ማለትም አንድ ነገር እውነት ነው የምንለው ከነገሩ ጋር የሚገናኝ ሌላ እውነት የሆነ ነገር ሲኖር ነው።ለምሳሌ"ወተት ነጭ ነው"መሆኑን እውነት እንደሆነ ለማረጋገጥ ወተት በራሱ ቀለሙ ምን እንደሆነ "ነጭ ነው" ያልነው ሀሳብ ይደግፍልና እንደማለት ነው።በህገ-መጣጣም ውስጥ ቃሉ በሌላ ቃል ስለተደገፈ ወይም ስለተገናኘ ብቻ እውነት ነው ማለት አይቻልም(correspondence is not a word by word connecting of a sentence to its reference.)።
በዚህ የእውነት ዘርፍ ተጠቃሽ ፈላስፎች ጆን ሎክ፣ በርትናልድ ራስል ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

2)Coherence Theories(ህገ-መስማማት)

:-ይሄኛው ከህገ-መጣጣም(Correspondence) ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸው ልዮነታቸው የጎላ ነው።በህገ-መስማማትእውነት ነው ብለን የምናምነው ነገር በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ካለው ነገር ጋር ሲጣጣም ነው።ለምሳሌ Elephants are gray (ዝሆን ግራጫ ነው!)

3)Pragmatism(ተግባራዊነት)
፦ በ19 እና 20ኛ ክፍለዘመን የተጀመረ የአሜሪካ ፍልስፍና እሳቦት ነው።ከስነ-ምግባር ፍልስፍና ስናየው እንደውጤት ተኮር ስነ-ምግባር አስተምህሮ(Consequence Ethics theory) ነገሩን በውጤቱ ላይ ተመርኩዘን እውነት መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን የሚለው ነው።

ሌሎችም አሉ ለምሳሌ..
1]Deflationary Theories
2]Semantic Theory

አሁን ያለንበት ድህረ-ዘመናዊነት (Post-Modernism) ስለእውነት ያለው እሳቤም "የጋራ የሆነ የእውነት መለኪያ ከለሌ እውነት አንፃራዊ ነው" አንድ መነሻ እና መፈረጃ መንገድ እስከሌለ እውነት የግል ምልከታ ነው'።ታዋቂ ድህረ ዘመናዊው ፈላስፎች መካከል አንዱ ሊዪታርድም እንዲህ "የራሳችን እውነት የምንለው ነገር በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲሆን መጠበቅ የለብን!"ይለናል።በድህረ ዘመናዊው አለም ያንተ/ያንቺ እውነት ለሌላው እውነት ላይሆን ይችላል።

ከፓለቲከኛ ፈላስፎች መካከል አንዱ ፋኮ ነው!ፋኮም እውነትን እንዲህ ይገልፀዋል<<እውነት ሁሌም ሀይል ባለው ዘንድ ተሰርቶ ይቀርባል>> በእርግጥ ይሄ ሀሳብ በጀርመናዊው ፍሬድሪክ ኒቼ "power of well" ጋር ተመሳሳይነት ይታይበታል ኒቼ እውነትን በThe spake of Zarathustra መፅሀፉ በኩል እንዲህ ይለዋል<<እውነት ባለበት ሀይልን አገኘሁት፣ሀይል ባለበት ሁሉ እውነት አገኘው!>>ቀጥሎም<<ሁሉን የሚያስማማ አንድ እውነት የለም>>አለ።ይሄ በእርግጥ ለዘመናዊው የእውነት ጥያቄ ርዮት ራሱን የቻለ ደጋፊ ሀሳብ ነበር።

<<.....እውነት ምንድነው?.....>>
ጲላጦስ

ተፅፈ በይሁዳ

@Wisdom_Wisdom
@Wisdom_Wisdom