Get Mystery Box with random crypto!

አራቱ ልዕልናዎች (The Four Cardinal Virues) *** ልዕልናዎች (Virtues) አመክ | ፍልስፍና

አራቱ ልዕልናዎች (The Four Cardinal Virues)
***
ልዕልናዎች (Virtues) አመክንዮ ላይ የተመሰረቱ የአእምሮ ባህርያት ሲሆኑ እነዚህም ልዕልናዎች የሰውን ልጅ ደስታ እንደሚያጎናፅፉ ይታመናል፡፡ በታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ መሠረት ደስታን የሚያጎናፅፉ የህይወት ልዕልናዎች አራት ናቸው፤ እነሱም፣
1) Ann (Wisdom/Prudence) - ለትክክለኛ ድርጊት ትክክለኛ ጊዜና ትክክለኛ ቦታ ማወቅ፣ ‹‹ምን?እንዴት? መቼ? የት? ማን?›› የሚሉትን ጥያቄዎች የማቀናጀት ችሎታ፤ ይሄ እሴት በተለይ ህዝብን ለሚመሩ ሰዎች እጅግ የሚያስፈልግ እሴት ነው እንደሆነ ይታመናል፤
***
2) ታጋሽነት (Temperance/Moderation) | ስሜትን የመቆጣጠርና የመግራት ችሎታ፤ ይህ ልዕልና ለሁሉም የህብተሰብ ክፍል አስፈላጊ ቢሆንም፣ በተለይ ግን ለአምራቹ የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ነው፤
***
3) ጉብዝና/ደፋርነት (Courage) ፍርሃትን ማሸነፍ፣ በአስቸጋሪ ጊዜ መፅናት፣ አቋም ያለው፣ በወቅታዊ ማዕበል በቀላሉ አለመናወፅ፤ ይሄ ደግሞ ለወታደሮች እጅግ ጠቃሚ የሆነ እሴት ነው፡፡

4) ፍትሐዊነት (Justice) ፍትሐዊነት ለአንድ የህብረተሰብ ክፍል ተለይቶ የሚሰጥ እሴት ሳይሆን፣ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚመለከት ነው፡፡
***
አሪስቶትል እነዚህን የፕሌቶ አራት ልዕልናዎች ይቀበልና እንደ "ጓደኝነት" ያሉ ሌሎች ልዕልናዎችንም ይጨምርበታል፡፡ ቶማስ አኳይነስ ግን እነዚህን የፕሌቶና አሪስቶትል ልዕልናዎች ‹‹የዚህ ምድር ልዕልናዎች ናቸው›› ይላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን፣ ያሉን ልዕልናዎች እነዚህ ምድራዊ ልዕልናዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ሦስት የሰማያዊው ዓለም ልዕልናዎችም እንዳሉነ ቅዱስ ጳውሎስን በ1ቆሮ 13:13 ይጠቅሳል፡፡
በዚህም እምነት፣ ተስፋና ፍቅር – faith hope and love በአኳይነስ አመለካከት ዘላለማዊ ህይወትና ደስታን ለመጎናፀፍ እነዚህን ሦስት ሰማያዊ ልዕልናዎች የግድ ማሟላት እንዳለብነ ይነግረናል፡፡

@Wisdom_wisdom