Get Mystery Box with random crypto!

ምሳሌዎች ሁሉ እዉነትን ቢገልጡም፥ እዉነት ሁሉ ግን በምሳሌ አይገደብም፥ ስለሆነም እዉነቱ እና ምሳ | ሰማያዊ ጥበብ 🌞🌞🌞🌞 ⛪

ምሳሌዎች ሁሉ እዉነትን ቢገልጡም፥ እዉነት ሁሉ ግን በምሳሌ አይገደብም፥ ስለሆነም እዉነቱ እና ምሳሌዉ ሳይጋጭ ለመከተል ሞክሩ፥ በነገራችን ላይ የክርስቶስ ህይወት ከቀን ወደ ቀን እየገባን ሲመጣ፥ ዋጋዉም በዚያኑ ልክ እየጨመረ ይሄዳል፤ አስበነዉ ይሆን?፥ ቅድም ወይም አሁን በተረፍነዉ ልክ እግዚአብሔር ነዉ ማለት ግን አይደለም፥ ትላንት እስከምን ያክል እንዳወቅነዉ ያለን ስዕል፥ ዛሬ ከአይምሮ በላይ በሆነ ጭማሬ ያሻቅባል፥ ግን አሁንም ያ ብቻ አይደለም፤ እንኪያስ ይሄ የሚሆነዉ የተለወጠ መዳን ኖሮ ነዉን? በፍፁም! ያ ሊሆን አይችልም ነገር ግን የተለወጠ ማንነት እኛ ዉስጥ ስለሚፈጥር ነዉ።

ተስፋን የሰጠ ዳግም የሚመጣዉ፥ አማንያን ከሩቅ የተሳለሙት፥ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ ነዉ፤ ነገር ግን እኛም ከእንግዲህ በሩቅ እንዳንገኝ፥ የሚያፀናዉን፦ ስለተስፋዉ የሚናገረዉን ከመንፈስ ቅዱስ እንሰማ ዘንድ በቀረዉስ ህብረትን አደረግን፥ ስለዚህ በአብ የተተመነዉ ዋጋ፥ ክርስቶስ ኢየሱስ ነዉና፥ ያ አብ ያወጣዉ ተመን ላይ እስክንደርስ ድረስ፥ ስለክርስቶስ የሚመሰክር ቅዱስ መንፈስ፥ በእኛ ዉስጥ ይኖራል፤ ከላይ ባየነዉ ክፍል ዉስጥ "...እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ" የሚል ቃል እናገኛለን፥ ለምን?፥ እነዚህ ሶስቱ ፀንተዉ ይኖራሉ ተብሎ ከተፃፉት መካከል አንዱ "ተስፋ" ነዉ!፤ በመሆኑም እኛም መልሰን በምስክርነታችን እንፀናለን!
#ሰማያዊ_ጥበብ

#ጌታ_እየመጣ_ነዉ!

ይህንን አገልግሎት ለመቀላቀል

                    @wisdom3in1
                    @wisdom3in1
#ተባረኩ