Get Mystery Box with random crypto!

በቅዱስነታቸው ጉዞ በተፈጠሩ ችግሮች ዙርያ የተሰጠ መግለጫ። (ኢኦተቤ ቴቪ ሐምሌ ፳ ቀን ፳፻፲፬ ዓ | የእንጦጦ መ/ስ/ቅ/ሥ/ቤ/ክ ዉሉደ ብርሃን ሰ/ት/ቤት

በቅዱስነታቸው ጉዞ በተፈጠሩ ችግሮች ዙርያ የተሰጠ መግለጫ።
(ኢኦተቤ ቴቪ ሐምሌ ፳ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም )
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጉዞ ላይ ባጋጠማቸው እክሎች ዙርያ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላላ ድ/ቤት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ;ብፁዕ ዶ/ር  አቡነ ጴጥሮስ የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፤ መልአከ ሕይወት ቆምስ አባ ኃ/ገብርኤል የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጸሐፊ  በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል::
በመግለጫውም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክነት በቃለ ወዋዲው እና በሕገ ቤተክርስቲያን  የተረጋገጠ መሆኑን ተገልጿል።
ከቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለሕክምና ከሀገር ውጪ እንደሚሄዱ ሐምሌ ፲፭ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ባስታወቁት መሠረት በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ለህክምና ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዘዋል። ጉዞውም ሕጋዊና ምክንያቱ የሕክምና ክትትል ለማድረግ መሆኑን የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች የሚያውቀት መሆኑን ተናግረዋል ::
ቅዱስነታቸው በሕገ ቤተ ክርስቲያን ባላቸው ሥልጣን  ታቦት የመባረክ;  የአብያተ ክርስቲያናትን ቡራኬ ማከናውን አንዱ መሆኑ በመግለጫው የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስነታቸው ሊወስዷቸው የነበሩ ታቦታት በቤተክርስቲያኗ እውቅና ቅዱስ ፓትር ያርኩ በሰጡት  መመሪያ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላላ ጽ /ቤት ትዕዛዝ በቅርፃ  ቅርፅ ክፍል ተዘጋጅቶ ይዘውት እንዲሄዱ የተዘጋጀ የተለመደና ሕጋዊ አሠራርን የተከተለ መሆኑን ገልጸው በጉዞው ወቅት ቅርጻ ቅርጽ  የሚለውን "ቅርሳ ቅርስ" መባሉ አግባብ አለመሆኑን ገልጸዋል ::
በመግለጫው በየምክንያቱ የቤተክርስቲያንን ክብር መንካት በየተቋማቱ እየታየ በመሆኑ የቤተ ክርስቲያኗን ጥንታዊነት ለሀገር ያበረከተችውን አስተዋዖ በማስብ ክብር ሊጠበቅ
እንደሚገባ ተነግሯል።
EOTC TV
++++++++++++++++++++++++++++++++
የወቅታዊ መረጃ ከትክክለኛው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልሳን ለማግኘት ተከታዮን የዩቲዩብ የፌስ ቡክ ቴሌግራም እና ኢንስታግራም ሊንኮች በመጫን ሰብስክራይብ እና ላይክ ያድርጉ፡፡ ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡
የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel